www.maledatimes.com ዘመን ባንክ ለጨረታ ያቀረባቸው የሆላንድ ካር ንብረቶች እንዳይሸጡ ታገዱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዘመን ባንክ ለጨረታ ያቀረባቸው የሆላንድ ካር ንብረቶች እንዳይሸጡ ታገዱ

By   /   March 24, 2013  /   Comments Off on ዘመን ባንክ ለጨረታ ያቀረባቸው የሆላንድ ካር ንብረቶች እንዳይሸጡ ታገዱ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 0 Second

-    ለጨረታ የቀረቡት ሕንፃዎችና ማሽነሪዎች ነበሩ 

ዘመን ባንክ ለብድር መያዣነት ይዟቸው የነበሩትን የሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የግል ማኅበር ንብረቶች ለመሸጥ አውጥቶት የነበረው ጨረታ ተግባራዊ እንዳይሆን ፍርድ ቤት አገደ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አምስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት መጋቢት 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላይ ጥር 7 ቀን 2005 ዓ.ም. የመክሰር ፍርድ ተላልፎበታል፡፡ ለንብረቱ መርማሪ ዳኛና ንብረት ጠባቂ እንዲሾም ውሳኔ መስጠቱን አስታውሶ፣ መክሰሩ ተረጋግጦ በቅድሚያ መፈጸም ያለበት ተግባር ሳይፈጸም፣ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ወይም ዕዳው መኖሩ ሳይታመንና ሳይረጋገጥ የሆላንድ ካር ንብረቶችን መሸጥ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ዘመን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ለጨረታ ያቀረባቸው የሆላንድ ካር ንብረቶች፣ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎችና ሰባት የተለያዩ ማሽነሪዎች ሲሆኑ፣ ጠቅላላ መነሻ ዋጋቸው 14,387,779 ብር ነበር፡፡ ነገር ግን ሆላንድ ካር የተለያዩ የቤት መኪናዎች ሠርቶ ለማስረከብ ሙሉ ክፍያ ካስከፈላቸው ደንበኞቹ መካከል ሲስተር አሻ ከተቦ የተባሉት ደንበኛ፣ በጠበቃቸው በአቶ አዳሙ ሽፈራው አማካይነት በመሠረቱት የፍትሐ ብሔር ክስ፣ ፍርድ ቤቱ የኪሳራ ውሳኔ በመስጠቱ፣ ዘመን ባንክ ንብረቶቹን አጫርቶ መሸጥ እንደማይችል ፍርድ ቤቱ በድጋሜ አስታውቋል፡፡

የንግድ ሕጉ ‹‹ከስረናል›› በሚሉ ድርጅቶች ላይ የኪሳራ ውሳኔ የሚሰጥበት ምክንያት ራሱን የቻለ ዓላማ እንዳለው ፍርድ ቤቱ በሰጠው እግድ ላይ አብራርቷል፡፡ የመክሰር ፍርድ በምን ሁኔታና መቼ መሰጠት እንዳለበት ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የመክሰር ፍርድ ከተሰጠ በኋላም እያንዳንዳቸው ተግባራት እንዴት መከናወንና በማን መከናወን እንዳለባቸውም በዝርዝር ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ተግባራቱ በሕጉ መሠረትና የሕጉንም ዓላማ ሊያሳኩ በሚያስችላቸው ሁኔታ መሆን እንዳለባቸው አብራርቷል፡፡

የመክሰር ውሳኔ መስጠት የሚያስፈልግበት ዋናው ምክንያት አንድ ነጋዴ ሆን ብሎ ንብረቱን እንዳያባክን፣ ለሚፈልጋቸውና ለሚመርጣቸው ባለገንዘቦች ንብረቱን አስቀድሞ በመስጠትና በማሸሽ፣ በሌሎች ገንዘብ ፈላጊዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል መሆኑን የትዕዛዝ ውሳኔው ይገልጻል፡፡ ሌላው ጥቅም ደግሞ የከሰረው ድርጅት ንብረት በአግባቡ ተጠብቆና ተይዞ በሕግ የቀዳሚነት መብት የተሰጣቸው ገንዘብ ጠያቂዎች፣ በሕጉ መሠረት እንደየድርሻቸው ተካፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑንም ፍርድ ቤቱ አሳውቋል፡፡

ዘመን ባንክ እንዳደረገው ሁሉ የመክሰር ፍርድ ከተሰጠ በኋላ እያንዳንዱ ገንዘብ ጠያቂ በገዛ ፈቃዱና ምርጫው ንብረቱን የሚይዝና በንብረቱም የሚያስፈጽም ከሆነ፣ የሕጉን ዓላማ የማያሳካ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ንብረቱ በተወሰኑ ሰዎች እጅ ያላግባብ እንዲገባ፣ ሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው እንደሚያደርግ ውሳኔው ያብራራል፡፡

የመክሰር ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ክስ መቅረብ ካለበት በንግድ ሕጉ መሠረት መሆን እንዳለበት የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ከዚህ ውጭ የከሰረ ሰው ወይም ድርጅት በቀጥታ ሊከስ እንደማይችል በዘመን ባንክ ላይ የተሰጠው የትዕዛዝ ውሳኔ ያስረዳል፡፡ የከሰረ ሰው ወይም ድርጅት ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው የኪሳራ ውሳኔ የተላለፈበትን ድርጅት እንዲያጣሩ ለተሾሙት ዳኛና ንብረት ጠባቂ ብቻ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

የመክሰር ውሳኔ ከተሰጠበት ጥር 7 ቀን 2005 ዓ.ም. በኋላ የተጀመሩ አፈጻጸሞችና ንብረትን የመያዝ ተግባር (የሆላንድ ካር ንብረት) ሊቆም እንደሚገባና የታገዱ መሆኑንም ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ዘመን ባንክ የሆላንድ ካር ንብረትን ለጨረታ ማቅረቡ ተገቢ ባለመሆኑ ታግዶ እንዲቆይ አዟል፡፡

Source  ER

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 24, 2013 @ 10:51 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar