www.maledatimes.com በአለም ዙርያ ለሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ የተጠራ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአለም ዙርያ ለሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ የተጠራ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013

By   /   March 24, 2013  /   Comments Off on በአለም ዙርያ ለሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ የተጠራ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 24 Second

በአለም ዙርያ ለሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች

ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ የተጠራ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ

በዋሽንግተን ዲሲ፤ ጁላይ፣ 2013

በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠይቀዉ አንድ ጥያቄ ነዉ። ይህም የአንድነትና ተባብሮ የመስራት ጥያቄ ነዉ። ይህንንም ጥያቄ ህብረተሰቡ በተገኘዉ መድረክ ላይ ሁሉ ሳያሰልስ እያነሳዉ ይገኛል። ከዚህ አኳያ ለዚህ ህዝባዊ ጥያቄ ሁሉም በጉዳዩ ያገባኛል የሚሉ ወገኖች ሁሉ ጊዜ ሳይሰጡ በመገናኘትና በዚህ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ላይ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዉ ሊወያዩበትና ሊመክሩበት አልፎም መፍትሄ ማስቀመጥና ይህንኑም ለማስፈጸም በጋራ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤትም ከተነሳለት ህብረተሰቡን የማስተባበር አላማ በመነሳት ከተባባሪ አዘጋጅ አካላት ጋር በመሆን፤ ለህብረተሰቡ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቆራጥ ምላሽ ለማሰጠት፤ ያለዉን ስርአት በማስወገድ ሂደትና ስርአቱም ከተወገደ በሗላ ስለሚተካበት ሁኔታ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካሎች አማራጮቻቸውን የሚያቀርቡበት “ትግሉም የጋራ ድሉም የጋራ” በሚል መርህ ዙርያ ታላቅ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በጁላይ ወር 2013 (እኤአ) በዋሽንግተን ዲሲ ላይ እየተሰናዳ ይገኛል።

የጉባኤዉ አላማ

 

ጉባኤዉ በሀገራችን ያለውን ጸረ-ኢትዮጵያ፤ ጸረ-ህዝብና፤ ጸረ-ዴሞክራሲ የሆነውን የሕወሓት/ኢህአዲግ ስርአት አስወግዶ ወደ ዲሞክራሲያዊ  ስርዓት ስለመሸጋገር የሚመክር፡ አለማቀፍ ህዝባዊ ጉባኤ ነዉ።ከአለም ዙርያ የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያዉያንና ድርጅቶች ያሏቸዉን የመፍትሄ ሀሳቦችና አማራጮች በጉባኤው ላይ የሚያቀርቡበትና የጋራ ምክክር በማድረግ (national dialogue) የብሄራዊ ስምምነት(Consensus Building) ባህልን በመጀመር፤ ብሎም ሁሉን-አቀፍ ሕዝባዊ የሽግግር መንግስት ከስርአቱ ዉድቀት በሗላ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚቋቋምበትን ቅድመ-ሁኔታዎችን በጋራ የሚያመቻች ጉባኤነዉ።

በጉባኤዉ የሚዳሰሱ አጀንዳዎች

 

  1. የህወሀት/ኢህአዴግን ስርአት በተቀነባበረ ትግል ስለ ማስወገድ
  2. አብዛኛዉን ወገኖችን ሊያስማሙና በጋራ ሊያሰሩ የሚችሉ የትግል መስኮችን መለየት
  3. መላዉን ህብረተሰብና ባለድርሻዎች (stakeholders) ማስተባበር
  4. የህወሀት/ኢህአዴግን በማስወገድ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ማቋቋም
  5. ስርአቱን በመተካት ሂደት ከሁሉም ባለድርሻዎች (stakeholders) የሚቀርቡ አማራጮች
  6. የአለማቀፍ ድጋፍ እንዴት ይሰባስባል
  7. ለትግሉ የሚያስፈልገዉን አቅም መገንባት
  8. የሚጀመረዉን የምክክር ሂደት በዘላቂነት ስለማስቀጠል

 

የጉባኤዉ ዉጤት

 

ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ እጅግ ከፍተኛ ዉይይቶች ተከናዉነዉ በጉባኤዉ ማገባደጃ የሚከተሉት ዉጤቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

  1. ሁሉንም የጉባኤ ተሳታፊዎች ሊያስማሙ የሚችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች በመዘርዘር ተለይተዉ ይወጣሉ
  2. ስምምነት በተደረሰባቸዉ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ይወሰዳል
  3. የጉባኤ ተሳታፊዎች በሁሉም ነገር ላይ በጋራ ለመስራት ባይችሉ እንኳን ስርአቱ እሰኪወገድ ድረስ እርስ በእርስ ላለመጋጨት የጋራ ስምምነት ያደርጋሉ
  4. በሃገር ቤት ዉስጥ ትግል ከሚያደርጉ አካላት ጋር ትግሉ የሚቀናጅበትን ዘዴ (mechanism) ይፈጠራል
  5. የሽግግር ሂደት እቅድ ይሰናዳል ለማናቸዉም አጋጣሚ ቅድመ ዝግጅቶች መደረግ ይጀምራሉ
  6. ምክክር ሂደቱን በቀጣይነት ለማካሄድ ስምምነት ይደረሳል

 

 

 

የጉባኤዉ ተሳታፊዎች

 

ይህ ታላቅ ሀገራዊ ራእይንና መፍትሄ ይዞ የተነሳ እቅድ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንዲያሳትፍ ከፍተኛ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገርን ጥፋት የመከላከል ሀላፊነት አለበት ከሚለዉ መርህ በመነሳት ማናቸዉም ሀገሬን አወዳለሁ የሚል ወገን ሁሉ በስብሰባዉ ላይ በመገኘት ለሀገራችን ችግር አለኝ የሚለዉን መፍትሄ ለዉይይት እንዲያቀርብ ተጋብዟል። ማቅረብም ይጠበቅበታል። በዚህም መሰረት ለሁሉም

 

  1. የፖለቲካ ድርጅቶች
  2. የሲቪክ ማህበራት
  3. ከሀገር ቤት የሚጋበዙ ድርጅቶችና እንግዶች
  4. የሃይማኖት ድርጅቶች
  5. የሜድያ ተቋማት
  6. በየከተማዉ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበራት
  7. የሴቶች ማህበራት
  8. የወጣቶች ማህበራት
  9. የሙያ ማህበራት
  10. ሀገር ወዳድ የንግድ ድርጅቶች
  11. ምሁራን
  12. ታዋቂ ግለሰቦች
  13. ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን
  14. አለማቀፍ ድርጅቶች
  15. የዉጭ ሀገሮች እንግዶች

 

ጥሪያችቸንን እያስተላለፍን ለጉባኤዉ መሳካት ሁሉም እዉነተኛ ሀገር ወዳድ ወገን ሁሉ ድጋፍ እንዲሰጥ በማክበር እንጠይቃለን። በጉባኤዉም ተሳታፊ ለመሆን ድረገጻችንን www.etntc.org  በመጎብኘት እንዲሁም በኢሜይላችንcontact@etntc.org በመላክ በተጨማሪም በስልክ ቁጥሮች 001-202-735-4262 እና +44-7958-487-420 በመደወል እንዲመዘገቡ እንጋብዛለን። ጉባኤዉን በተመለከተ በአለም ላይ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩባቸዉ ከተሞች ሁሉ ተከታታይ ስብሰባዎች በማከናወን ወገኖቻችንን በማወያየት ሁሉም ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የጉባኤ ተሳታፊዎች እንዲልኩ እንጋብዛለን።

 

አንድነት-ነጻነት!!!!!!!

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 24, 2013 @ 8:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar