www.maledatimes.com ቀጣዩ የጭቆና ዜና ስንቶችን ያስደንቅ ይሆን? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቀጣዩ የጭቆና ዜና ስንቶችን ያስደንቅ ይሆን?

By   /   March 25, 2013  /   Comments Off on ቀጣዩ የጭቆና ዜና ስንቶችን ያስደንቅ ይሆን?

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 34 Second

ሰዎች ስለመንግሥትና ስለሰራው አንድ ጭቆና ሲናገሩ “አሁንስ አበዙት” ወይም “የዛሬውስ በዛ” በማለት ሲደነቁ መልሶ ይደንቀኛል። ልክ ከዚህ በፊት ከዚህ የባሰ ግፍ ተፈጽሞ የማያውቅ ወይም ገዢዎቻችን ድንገት ከጥሩነት ወደመጥፎነት የተቀየሩ ይመስል….።

መገረምና መደነቅ የፖለቲካ ብሂል ሲሆን ማየት ያሳዝናል። ተገርሞና ተደንቆ ያልጨረሰ ሰው የያዘውን ጉዳይ በስክነት ወደ መመርምር ለመሔድ ጊዜ ይፈጅበታል። በጭቆና የደነዘዘ ማኅበረሰብም እንዲሁ ነው፤ እያንዳንዱ የአፈናና የግፍ ተግባር እንደ አዲስ ይገርመዋል፤ ይደንቀዋል። ጭቆናው የገዢዎቹ ባህሪይ ሳይሆን ድንገት የተፈጸመ የሚያስመስል ቅዠት ብጤ የሚከጅለውም አይጠፋም። በአንዱ ግፍ ተገርሞ ሳይጨርስ፣ በሌላ የጭቆና ዜና ድንቅ ይጠመዳል….ሲገረም፣ ሲደነቅ ይኖራል።

ስብሰባ ተከለከለ፣ መገረም። የግራዚያኒን የመታሰቢያ ሃውልት ለመቃወም የወጡ ሰዎች ታሰሩ፣ መደነቅ። ጋዜጣ ተዘጋ፣ ጋዜጠኛ ተከሰሰ..እንደገና መገረም። ዜጎች በብሔር ማንነታቸው ተጠቃሚ ሆኑ ወይም ተጎዱ…በየቀኑ እንደአዲስ መደነቅ። ታሰሩ፣ ተሰደዱ፣ ተፈናቀሉ፣ ተበደሉ፣….በየቀኑ፣ በእያንዳንዱ የጭቆና ዜና ነገሩ ሁሉ ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ ይመስል፤ ወይም አዲስ የተባለው የጭቆና ዜና ሊሆን እንደሚቸል አስቀድሞ በቂ ምልክት እንዳልተሰጠን፣ ጭቆናው የማይቀር መሆኑ እንዳልተነገረን፣ ጨቋኙ የተፈጠረበትን እያከናወነ እንዳልሆነ ሁሉ ደርሶ እንደአዲስ መደነቅ! ጭቆናውና መገለጫው የሆኑት ድርጊቶች መዘገባቸው፣ መጋለጣቸውን መቃወሜ አይደለም። ዜናዎቹን የምናስተናግድበት መንገድ ግን መጨረሻ የሌለው አጃጃይ መገረምና መደነቅ መሆን የለበትም።

በጭቆና ዜና ከመገረምና ከመደነቅ ወጥትን ስለጭቆናውንና ስለጨቋኙ ወደ ማሰላሰል፣ ወደማሰብ…. “እንዲህማ አያረጉም” ብሎ ራስን ለሌላ ዙር መደነቅ ከማዘጋጀት ይልቅ አምባገነኖች ማንኛውንም አይነት የግፍ ተግባር ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ ራስን ማሰመን ቢያንስ ጊዜ ይቆጥባል። ሰዎቹ ሥርዓታቸውን ለማሰንበት በሚያደርጉት ነገር የሕግም፣ የባህልም፣የፖለቲካም ሆነ የሞራል ልጓም የላቸውም፤ ልምዳችን ይህን ያረጋግጣል። ቀጣዩ የጭቆና ዜና ስንቶችን ያስደንቅ ይሆን?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 25, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 25, 2013 @ 9:05 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar