www.maledatimes.com ሀሞትን ከጀግና (በይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሀሞትን ከጀግና (በ ይግዛው እያሱ)

By   /   March 25, 2013  /   Comments Off on ሀሞትን ከጀግና (በ ይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 37 Second
ጓዶች ነብሩ አሉ ሀሞትና ጀግና
ድሮ በዚያ ዘመን ገና ድሮ ገና::
ሀሞት እንደድፍረት ሞልቶ እንዳልፈሰሰ
ጀግናም በየጊዜው ፈጥኖ እንዳልደረሰ
ጊዜም አለፈና መድፈር ተረሳና
ባገሩ ባድባሩ ፍርሀት ነገሰ::
ሀሞት ፍርሀት ሆኖ እንደጅረት ሲፈስ
ፈሪም መንጋ ሆኖ ባገር ሲተራመስ
ዓመታቶች አልፈው እዚህ ላይ ደርሰናል
ጀግኖች በድን ሆነው በሙት ታውከናል::
ፍርሀትን ተሸክመው ፍርሀትን ወለዱ
አንዱ አንዱን ለመቅደም እየተራመዱ
መውጫ ጠፍቶባቸው የኋሊት ነጎዱ::
ጓዶች ነበሩ አሉ ሀሞትና ጀግና
ድሮ በዚያ ዘመን ገና ድሮ ገና::
ያ ሁሉ ቀረና ዝምድና ጠፋና
ተበታተኑ አሉ ሀሞትና ጀግና::
የውላጅ መፈንጫ ሳይሆን ሀገር ምድሩ
የባንዳ ግልምጫ ሳያይ ሕዝብ አድባሩ
ሀሞትና ጀግና ወዳጆች ነበሩ::
ተስፋዬን ሳልቆርጥ ፈለግሁ ስመ ጥሩ
ብራመድ ብኳትን ብዞር በመንደሩ
ጀግና የወለደው ነጻነት የጠማው አጣሁኝ ባገሩ::
በፍጹም ሳልታክት ደጋግሜ ወጣሁ
ነጻነት ፍለጋ አሻግሬ እያየሁ
ጀግና ባግኝ ብዬ ደግሜ ተመኘሁ::
እኔም ከጀግና ጎን አብሬ ልሰለፍ
አጋር አሻ ልቤ በእውነት ለማሸነፍ::
ከገጠሙ ወዲያ ትግል ያለዳኛ
ቢሸሹም አይለቅም የከፋው አርበኛ::
ሀሞትና ጀግና መቸ ሰነፉና
ላይደጋገፉ እየተገፋፉ
ካገሩ ጠፍተዋል
ከትመው አድፍጠዋል::
ተስፋ ያልቆረጠው ያ አንድ ለናቱ
ዝም አለ አሉኝ ቴዲ ተያዘ አንደበቱ::
መጠጡን ጨለጠ ለብቻው ነጎደ
በልቡ ተራግሞ ሞት አስተናገደ::
ውርደትን ላያያት በጀግንነት ሄደ::
ተጋፍጦ ተጋፍጦ ክብርን ያስተማረን
ለመዳን አይደለም የጠጣው ጥይቱን::
ዘለቅሁ ወደ ጎጃም ላገኘው በላይን
አልሞ ተኳሹን አትንኩኝ ሚለውን::
ደርሸ ከቀየው ብጠይቅ አጥብቄ
በሰማሁት ነገር እጅግ ተጨንቄ
ዝናሩን ከማማ ጣልሁለት አውልቄ::
ወሬ አይደበቅም ድንቅ ነገር ሰማሁ
ሀምትና ጀግናን ሊያስማማ እንደወጣ
በመሀል አራዳ በንጉሱ ጓዳ
ድግስ ደገሰና አበላ አጣጣና
ነጻነት ሰጠና
ለራሱ ሳይበላ ለራሱ ሳይጠጣ
ሳይሰስት አካፍሎ እድሩን አወጣ::
አሉና ነገሩኝ እርሜን እንዳወጣ::
ትውልድ ያሳዝናል
ትውልድ ያሳፍራል
ትውልድ ይጀግናል
ትውልድም ይፈራል
የአሁኑ ትውልድ ግን
ዝም ብሎ ይሞታል::
ሀሞታና ጀግና የተባበሩባት ይባል እንዳልነበር
ማንም አይደፍራትም ሲባል እንዳልነበር
ትናንት አልፎ ዛሬ
ነገም ሌላ ወሬ
ወሬን እየዋልን
ወሬን እያደርን
በወሬ ተፈታን::
ትውልድን አፍርተን
ትውልዶች አጠፋን::
ጀግኖችን ፈሪ አርገን
ጠላትን አበዛን
ጠላትን አጀገን
በባንዳ ተገዛን::
ፈርተን ተንበርክከን
ተደብቀን ጠፋን
አጎንብሰን ሄድን
ወጥተው ጋለቡብን
ጡት ነካሽ ነከሰን
ሀሞታችን ፈሶ ፈርተን ተቀመጥን::
ወይ ፈርተን አልፈራን
ጀገን ብለን ዘርተን
ፈሪዎች ወለድን::
ጀግና ጠልተን ኖረን
ፈርተን እያስፈራን
ሀሞትና ጀግናን
አለያይተን ቀረን::
ጓዶች ነበሩ አሉ
ሀሞታን ጀግና
ድሮ በዚያ ዘመን
ገና ድሮ ገና::
በ ይግዛው እያሱ
 
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar