www.maledatimes.com እነ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ረቡዕ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እነ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ረቡዕ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

By   /   March 25, 2013  /   Comments Off on እነ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ረቡዕ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 9 Second

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ ም/ሊመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት ወጣቱ ፖለቲከኛው አንዱዓለም አራጌና ዓለም አቀፍ ተሸላሚው ታዋቂው ጋዜጠኛና ፓለቲካ ተንታኝ እስክንድርነ ነጋን ጨምሮ ስድስት እስረኞች መጪው ረቡዕ ለውሳኔ 6 ኪሎ የሚገኘው የፌዴራሉ ጠ/ፍ/ቤት ለፍርድ ውሳኔ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል ወጣቱ መምህር ናትናኤል መኮንን፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/መኢዴፓ/ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ፣ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ አንዱዓም አያሌውና የባህርዳሩ ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለምን ጨምሮ ስድስት ፍርደኞች ረቡዕ የሚቀርቡት ከዚህ ቀደም  የከፍተኛው ፍ/ቤት በፈረደባቸው ፍርድ ቅር በመሰኘታቸው ይግባኝ ጠይቀው ነው፡፡ ይግባኙን የተቀበለው ጠ/ፍ/ቤት መሠረትዊ  የህግ አተረጓጎም ስህተት ተፈጥሮአል የተባበትን ጭብጥ ክርክር አድምጧል፤ የዐቃቤ ህግን መልስም ሰምቷል፡፡ በመጨረሻም ክርክሩን ያደመጠው ፍ/ቤት የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የቀጠረ  ቢሆንም በየቀጠሮዎቹ መዝገቡ ተመርምሮ  ባመጠናቀቁ በሚል ለ3ኛ ጊዜ መጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ/ም ሊቀጥር ችሏአል፡፡ በቀጠሮው መሠረት መጪው ረቡዕ  የይግባኙ የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ  ይጠበቃል፡፡ አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋን  ጨምሮ ታሳሪዎቹ የኢህአዴግን መንግስት የሰብአዊና ሌሎች ጥሰቶች ሲተቹ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 25, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 25, 2013 @ 11:29 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar