www.maledatimes.com ምኒልክ በዳላስ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ምኒልክ በዳላስ

By   /   July 24, 2012  /   Comments Off on ምኒልክ በዳላስ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second

ዳግማዊ ምኒልክ ክቡር ያ’ገሬ ሰው

የነጻነት ካባ ጥቁርን ያለበሰው

እንደገና መጣ አሁንም ጥቁር ሰው

ቤቱ ሲፈርስ አይቶ መልሶ ሊያድሰው

በባለጌ ከሳሽ ሲከሰስ ሲወቀስ

በካድሬ ጸሃፊ ታሪክ ሲደመሰስ

ምኒልክ ብቅ አለ ጥቁር ሰው በዳላስ

ንጉሱ በገና ጨዋታ ይወዳል

የፖለቲካ ወግ ጭምት ያሳብዳል

የእግር ኳስ ጨዋታ ምንጩና ፍጥረቱ

በእንግሊዝ ወታደር በጦር ነው ውልደቱ

ስፖርት ነጻ ነው ፖለቲካ አያውቅም:;?

የዞረ ድምር ነው አያነቃንቅም።

ፌዘኛ ተራቢ ብቻውን አይስቅም

የደስታ ብዛት የመንፈላሰስ

ዳንስ ገጥሞ አየነው ጥቁር ሰው ዳላስ

ስፖርት ድንቅ ነው ፖለቲካ ቅመም

በእስክስታ አስወጣሁት የያዘኝን ህመም

ምኒልክ ከአድዋ አሜሪካ መጥቷል

ምዕት አመት አልፎ እንደገና ታይቷል

የጥቁር ሰው መንፈስ ፍቅር ነፍስ ዘርቷል

ቴዎድሮስ ካሣሁን አመሰግናለሁ

ታሪኩ ባይሞላም ይትባረክ ብያለሁ

workeshet@bellsouth.net

ወርቅእሸት ቸርነት

ሓምሌ 2004 ዓ/ም.

ለጥቁር ሰው ከያኒ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዝግጅቱ ለተሳተፉ  እና ለሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 24, 2012 @ 3:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar