www.maledatimes.com ባለሥልጣናት “ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው” በማለት በማስፈራራት ላይ ናቸው -ኢህአዴግ ብቻውን እየተወዳደረም አልመረጥም ብሎ ሰግቷል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ባለሥልጣናት “ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው” በማለት በማስፈራራት ላይ ናቸው -ኢህአዴግ ብቻውን እየተወዳደረም አልመረጥም ብሎ ሰግቷል

By   /   March 25, 2013  /   Comments Off on ባለሥልጣናት “ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው” በማለት በማስፈራራት ላይ ናቸው -ኢህአዴግ ብቻውን እየተወዳደረም አልመረጥም ብሎ ሰግቷል

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 56 Second

በተለያየ የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ ተቀምጠው ያሉ ካድሬዎችና ደህንነቶች ሠራተኞችንና ነዋሪዎችን በየቀበሌው  እንዲሁም በተለያዩ አዳራሾች እየሰበሰቡ ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ እንደሆነ ከዛቻና ከማስፈሪያ ጋር መመሪያ እየሠጡ መሆናቸውን ምንጮቻችን ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪዎች እንዲሰበሰቡ ካስደረጉ በኋላ ስብሰባው የተጠራበትን አጀንዳ በመተው “ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ ነው፤ ኢህአዴግን አለመምረጥ ፀረ ህዝብነት ነው፡፡” የሚሉና ሌሎች ማስፈራሪያዎችን እየሰጡ ነው ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህራንና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር መጋቢት 11 ቀን 2005 ዓ/ም ነዋሪዎችን ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚናገሩት ምንጮቹ “ስብሰባ የተጠራነው ስለአካባቢያችን ልማትና መልካም አስተዳደር ላይ ለመወያየት ተብለን ነው፡፡ ስብሰባውን  የመሩት የወረዳው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው  አቶ አሰግድ (የወረዳው ኢህአዴግ ኃላፊ ናቸው፡፡) በስብሰባው ላይ ኢህአዴግን  መምረጥ ግዴታ ነው፡፡ በሚል መንፈስ ዛቻና  ማስፈራሪያ ሲናገሩ ውለዋል፡፡” ብለዋል፡፡ ምንጮቻችን አክለውም “ተሰብሳቢው  በበኩሉ በየሠፈሩ ያሉትን ችግሮች እያነሳ  ተናግሮአል፤ አንዳንዶቻችን እኛ ጥያቄአችን  ምርጫ ሳይሆን የእለት ዳቦ ነው ብንልም  ሰብሳቢው ተገቢ ያልሆነ መልስ ሰጥተውናል” በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም የመዝናኛ  ክበባት ሠራተኞች በክፍለ ከተማ ደረጃ  ስብሰባ ተጠርተው ነበር፡፡ ከስብሰባው  በኃላ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት  “የተጠራነው አገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ  ለመወያየት ተብሎ ነው፡፡ ነገር ግን  ኢህአዴግን መምረጥ ግዴታ እንደሆነ መመሪያ ተስቶናል፡፡ የፈለግነውን መምረጥ  እንደምንችል ወይም ማንንም አለመምረጥ  ህገ መንግስታዊ መብታችን መሆኑን  ሊረዱልን አልቻሉም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮ ምርጫ ነዋሪነታቸው ያልተረጋገጠና  የቀበሌ መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች ሁሉ በግዳጅ እንዲመዘገቡና ካርድ እንዲያወጡ  ተደርጓል፡፡ የሚል ቅሬታዎች ሲናገሩ  መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ በመንግስት  ደመወዝ እየተከፈላቸው ሙሉ ጊዜያቸውን  የፓርቲውን ሥራ የሚሠሩና በመንግስት  የሥራ ሰዓት ሠራተኛቸውን ለፓርቲው  ሥራ የሚያውሉ የመንግስት ባለሥልጣናት  በሙስና ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል የሚሉ  አስተያየቶችም እየተሰጡ ናቸው፡፡
በመጪው የአካባቢና የአዲስ አበባ መስተዳድር  ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ገዢው ፓርቲ  ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ላልመረጥ እችላለሁ በሚል ስጋት ነዋሪዎችንና ሰራተኞችን  በስብበሳ ማዋከቡ ብዙዎችን እያስገረመ ነው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 25, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 26, 2013 @ 12:02 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar