www.maledatimes.com ናትናኤል መኮንን ቤተሰቡ እንዳይጎበኙት ተከለከለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ናትናኤል መኮንን ቤተሰቡ እንዳይጎበኙት ተከለከለ

By   /   March 26, 2013  /   Comments Off on ናትናኤል መኮንን ቤተሰቡ እንዳይጎበኙት ተከለከለ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 56 Second

የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትና በቃሊቲ ቂሊንጦ ልዩ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ናትናኤል መኮንን ከሐሙስ መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ምክንያቱ ባልተገለፀበት ሁኔታ ከወዳጅ ቤተሰብ እንዳይገናኝ መከልከሉ ተረጋገጠ ፡፡ይህንንም የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ ከባለቤቱ ወይዘሮ ፍቅርተ ጋር በመሆን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2005 ዓ.ም እዛው ቃሊቲ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በአካል በመሄድ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
አቶ ናትኤል መኮንን በምን የህግ አግባብ ለአንድ ወር ከወዳጅ ቤተሰቦቹ በተለይም ዘወትር ከሚጠይቁትና ስንቅ ከሚያመላልሱለት ባለቤቱና ልጁ እንዳይገናኝ እንደተደረገ የፍትህ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑትን አቶ ደሳለኝ ታረቀኝን የጠየቅናቸው ሲሆን እሳቸውም “ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ የሚያዝ ህግ የለም በይበልጥ የማረሚያ ቤቱን ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው መኮንን መልስ
ይስጧችሁ” በማለት መርተውናል፡፡
ኮማንደር አስቻለው በበኩላቸው “በርግጥ እስረኛ የማረሚያ ቤቱን ስነምግባር ከጣሰ በማረሚያ ቤቱ አሰራር መሰረት ቅጣት ይኖራል፤
ነገር ግን የሚፈፀመው የማረሚያ ቤት ቅጣት ምክንያቱን ቤተሰቡና ታራሚው እንዲያውቁ ስለሚደረግ ማነጋገር ትችላላችሁ” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡
የወህኒ ቤቱ ጥበቃዎችና በዕለቱ ያሉ የኃላፊዎች ግን ስንቅ ይዘው ሊጠይቁ የሄዱትን የናትናኤልን ቤተሰቦች መገናኘት እንደማይችሉና ያዙትን
ምግብ ይዘው እንዲመለሱ ከማዘዝ ውጭ የክልከላውን ምክንያት አልተናገሩም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ “ማረሚያ ቤቱ የራሱ አሰራር ስላለው አይደለም የፍትህ ሚኒስቴርና ኮማንደር አስቻለው ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢመጡ አያገባቸውም” ሲሉ በወቅቱ ስማቸውን ለማወቅ ያልተቻለ የዕለቱ የጥበቃ ኃለፊና ሁለት የጥበቃ አባላት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 26, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 26, 2013 @ 12:21 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar