www.maledatimes.com በጋምቤላ በሳዑዲ ስታር ኩባንያ ላይ ጥቃት ያደረሱ የሽብር ተጠርጣሪ 14 ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጋምቤላ በሳዑዲ ስታር ኩባንያ ላይ ጥቃት ያደረሱ የሽብር ተጠርጣሪ 14 ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

By   /   March 27, 2013  /   Comments Off on በጋምቤላ በሳዑዲ ስታር ኩባንያ ላይ ጥቃት ያደረሱ የሽብር ተጠርጣሪ 14 ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 37 Second

በአሸናፊ ደምሴ

ሰንደቅ

ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በማሰብ ራሱን የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል በመሆን፣ ስልጠና በመውሰድና በመቀስቀስ ከውጪ በሚገኝ ገንዘብ በመታገዝና የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በዜጐች ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ሲል ዐቃቤ ህግ ክስ በመሰረተባቸው አስራአራት የጋምቤላ ወጣቶች ላይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት  ትናንት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጠ።

የፌዴራሉ ዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ በዝርዝር እንደሚያስረዳው ከሆነ ወጣቶቹ ወንድሞቻን ነፃ ሊያወጡን በጫካ እየታገሉ ነው ልንረዳቸው ይገባል በሚልና፤ የጋምቤላ ክልል የጥቁር ህዝቦች መሬት ብቻ መሆን አለበት በሚል አላማ በመንቀሳቀስ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ ጥቃት መሰንዘራቸውን ያትታል።

በዚህም በጋምቤላ ክልል በተቋቋመው የሳዑዲ ስታር የእርሻ ልማት ማህበር ግቢ “GRC” ውስጥና በርካታ ሰዎችን በጫነ መኪና ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት አራት ፓኪስታናውያንን ጨምሮ 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ስድስት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ያስረዳል። በዚህ የሽብር እንቅስቃሴ ውስጥም በተለይ 1ኛ ተከሳሽ ኡመድ ኡከር፣ 2ኛ ተከሳሽ ኡጁሉ ገመቹ፣ 3ኛ ተከሳሽ ፖል ኡመድ፣ 4ኛ ተከሳሽ ኡመድ ኡመድ እና 5ኛ ተከሳሽ ኡመድ ኡካች በድርጊቱ በስፋት መሳተፋቸውን ዐቃቤ ህግ ሲያስመሰክር እነርሱም ለፖሊስ በሰጡት ቃል ጭምር ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው አምነዋል ሲል ፍርድ ቤቱ በንባብ አስደምጧል።

በሌላ በኩል 6ኛ ተከሳሽ ሆኖ የቀረበው ዋና ሳጅን ኦኬሎ ኡጁሉ እና 7ኛ ተከሳሽ ሆኖ የቀረበው አዋኘንግ ኡሎንግ ወንጀሉን አለመፈፀማቸውን በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል በማስረዳታቸው ፍርድ ቤቱ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው እንዲያስደምጡ ቢያደርግም ምስክሮቹ የሰጡት ቃል ተከሳሾችን ክስ ማስተባበል ሳይቻል እንደቀረ ተገልጿል። በሌላ በኩል 11ኛ ተከሳሽ አቦቦ በተሰኘ ኬላ ላይ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሁለት የፖሊስ አባላት ህይወት እንዳያልፍ ማድረጉንም ዐቃቤ ህግ አስረድቷል።

ዐቃቤ ህግ በክስ መዝገቡ የጋምቤላ ክልልን ከፌዴሬሽኑ በኃይል ለመገንጠል በማሰብ በተለያዩ ቦታዎችና ጊዜያት የሽብር ጥቃት ፈፅመዋል፤ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት አድርሰዋል፤ ጋምቤላ የጥቁሮች ብቻ ናት የሚል መርህን አንግበዋል እና የጋምቤላን ህዝብ ነፃ እናወጣለን በሚል ከውጪ የሚመጣላቸውን የገንዘብ አቅርቦትና ስልጠና ተቀብለው የጦር መሳሪያ አንግበው ለአላማቸው መሳካት ሲሰሩ ነበር ባላቸው 14 ሰዎች ላይ 69 የሰው ምስክሮችን ሲያሰማ፤ ከቀረቡት ምስክሮች ውስጥም በሽብር ወንጀሉ ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ፣ በሽብር ጥቃቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውንና ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁት መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል። በሌላ በኩልም 17 የሰነድና በቪዲዮ የታገዙ መረጃዎችን አቅርበው ለፍርድ ቤቱ ያሳዩ ሲሆን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችንም በኢግዚቪትነት እንዳሉ አመላክቷል ይላል።

በዕቅድ አውጪነት በአመራርነትና በውሳኔ ሰጭነት የሽብር ቡድኑን ሲመራ ነበር የተባለው 8ኛ ተከሳሽ ኡመድ አዴል ከመንግስት የፀረ-ሽብር ሃይል ጋር በተደረገ ውጊያ መገደሉን ያስታወሰው ፍርድ ቤቱ፤ ክሱ መቋረጡንም አስታውቋል።

በመሆኑም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን፤ በተለያዩ የትራንስፖርት መገልገያዎችና በኬላዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የግድያና የአካል ማጉደል ወንጀል መፈፀማቸውንና ከውጪ ሀገርም ገንዘብ መቀበላቸውን በመረጃ አስደግፎ ማየቱን በመግለፅ ከ6ኛ እና ከ7ኛ ተከሳሾች ውጪ ሁሉም (በአካል ቀርበው ጉዳያቸውን የተከታተሉትም ሆነ ያልተከታተሉት) ጥፋተኛ ያላቸው ሲሆን፤ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ግን በ2ኛ ክስ ብቻ ለሽብር ቡድኑ ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ጥፋተኛ ናችሁ ብሏቸዋል።

በአጠቃላይም ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ በሚገኙት ስምንት ተከሳሾች ላይ የቅጣት አስተያየቶችን አድምጦ ቅጣት ለመወሰን ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 27, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 27, 2013 @ 1:38 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar