www.maledatimes.com መድረክ በማኒፌስቶው ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነች አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መድረክ በማኒፌስቶው ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነች አለ

By   /   March 27, 2013  /   Comments Off on መድረክ በማኒፌስቶው ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነች አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 26 Second

በዘሪሁን ሙሉጌታ

ሰንደቅ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫ ያለውን ባለ 12 ገፅ ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ። በማኒፌስቶውም ላይ ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗንም አመልክቷል።

ትናንት የመድረክ አመራሮች በጽ/ቤታቸው በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በተዘጋጀው ማኒፌስቶና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ትኩረት ስቦ የነበረው ‘‘ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች’’ የሚለው ርዕሰ ጉዳይ በመሆኑ የግንባሩ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የግንባሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ማኒፌስቶው ያለፉትን 21 አመታት በሙሉ የዳሰሰ፣ በውስጡ ያሉትን ችግሮች ለይቶ ያስቀመጠና ለቀጣዩ ጉዞ የመነሻ አዋጅ መሆኑን ካብራሩ በኋላ በሀገሪቱ በርካታ ችግሮች ከመስፈናቸው አንፃር በመስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ በበኩላቸው በሀገሪቱ እስካሁን ያሉትን ችግሮች በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ በኢትዮጵያ ፍፁማዊ አምባገነናዊ ስርዓት መስፈኑ በመግለፅ ሀገሪቱ ወይ ይሄንኑ አምባገነናዊ ስርዓት ይዛ መቀጠል አለበለዚያ ደግሞ ይህንኑ ስርዓት መቀየር በሚገባት መስቀለኛ መንገድ ላይ መገኘቷን አመልክተዋል።

አቶ ገብሩ አስራት በበኩላቸው መድረክ እስካሁን ድረስ የተደራጀ ማኒፌስቶ እንዳልነበረው አስታውሰው፤ አሁን ግን የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮችን ጨምቆ የያዘ፤ ከመድረክ ፕሮግራም ጋር የተናበበ ማኒፌስቶ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ማኒፌስቶውም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች ከነመፍትሄዎቻቸው ይዞ መቅረቡንም አመልክተዋል።

‘‘ሀገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነች’’ መባሉን በተመለከተ አቶ ገብሩ ሲያስረዱ፤ ‘‘ቃሉን መስቀለኛ እንበለውም ሌላ ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ነው ያለችው። እንኳን እኛ ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ በጉባኤው ላይ ትክክለኛ መፍትሄ ባያመጣም ሀገሪቱ በችግር ላይ መሆኗን ገልጿል። የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን ለመፍታት ውጤት ተኮር፣ ቢፒአር፣ ካይዘን ወዘተ ቢልም ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ችግር መፍትሄ ማምጣት እንዳቃተው የሚያሳይ ነው። ኢህአዴግ በሙስና ተዘፍቋል። ይሄንን እነሱም ያውቁታል። እኛም እናውቃለን። ከዚህ መውጫ መንገድም አላገኘም። ከዚህ ችግር መውጫ መዋቅራዊና የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። በመተካካት የሰው ለውጥ በማድረግና ለሕዝቡ ተስፋ በመስጠት ብቻ ለውጥ አይመጣም’’ ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው ማኒፌስቶው ብሔራዊ መግባባት መፍጠር በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ሀገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ስለመሆኗም ዶ/ር መረራ ሲናገሩ ‘‘ሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ አደጋ አለ። በተለይ ወጣቱ ላይ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነው። ሌላው የሙስሊሞች ጉዳይ ነው። ኢህአዴግ ብዙ ችግሮች እያለብን ሌላ ጣጣ ለምን እንደጨመረብን አላውቅም። በቀበሌ ውስጥ ወዳጆቹን እንደለመደው እንደሚያስመርጠው ቤተ እምነት ውስጥ ገብቶ ወዳጆቹን በዛው መንገድ ለማስመረጥ እጁን መንከር በሌለበት የሃይማኖት ጉይ ውስጥ ገብቷል። መዘዙ ደግሞ ለሁላችንም የሚተርፍ ነው’’ ብለዋል።

ኢህአዴግ ‘‘መተካካት’’ የሚለውን አካሄድ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መቅዳቱን በመጠቆም አሮጌው አመራር ለአዲሱ አመራር እየሰጠ፣ ጭንቀት ሲመጣ ደግሞ አሮጌው አመራር እየተመለሰ እየቀጠለ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር መረራ መተካካቱ ግን የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት የተቀመጠ የመፍትሄ አቅጣጫ አይደለም ብለዋል።

‘‘መተካካት የሚያስፈልገው የፖሊሲ የአሰራርና የአቅጣጫ ለውጥ ጋር ነው። አለበለዚያ ሐጎስን በፈይሳ በመተካት ሰሜንን በደቡብ መተካት ለውጥ የለውም’’ ሲሉ ዶ/ር መረራ የኢህአዴግን የመተካካት ወይም አቅጣጫ አጣጥለውታል።

ኢህአዴግ የአስተሳሰብ ጉዞውን ጨርሷል ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ‘‘አፄ ሚኒልክም ከሞቱ በኋላ ከሁለትና ሦስት አመት በላይ ገዝተዋል። ይህም የሸዋ መኳንቶች ሲጨንቃቸው ያደረጉት ነገር ነው። ኢህአዴግ በጭንቀት ላይ ስለሆነ ‘‘ሌጋሲ’’ እያለ ሀገር እየገዛ ነው’’ ያሉት ዶ/ር መረራ ‘‘ኢህአዴግ ባሉት መሪዎች አስተሳሰብ ደረጃ ቆሟል’’ ሲሉ ተናግረዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 27, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 27, 2013 @ 1:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar