www.maledatimes.com አንድነት ፓርቲ መድረክን ሊገመግም ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድነት ፓርቲ መድረክን ሊገመግም ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

By   /   March 27, 2013  /   Comments Off on አንድነት ፓርቲ መድረክን ሊገመግም ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 56 Second

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መደረክ (መድረክን) እንቅስቃሴ ሊገመግም ነው።

አንድነት ፓርቲ መድረክን እንዲገመግም ውሳኔ የተላለፈው የፓርቲው ሁለተኛው ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው ብሔራዊ ም/ቤት ባለፈው እሁድ መጋቢት 14 ቀን 2005 ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው።

የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ጉዳዩን በማስመልከት ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው እንደመለሱት አንድነት የመድረክን አጠቃላይ አካሄድ ለመገምገም መገደዱን ገልፀዋል። ብሔራዊ ም/ቤቱ በስድስት አጀንዳዎች ላይ መምከሩን የገለፁት ሰብሳቢው ከአጀንዳዎቹ መካከል ከ2004 ዓ.ም ሰኔ ወር ጀምሮ የመድረክ እንቅስቃሴ ይገምገም የሚል ውሳኔ በብሔራዊ ም/ቤቱ ቢወሰንም እስካሁን ውሳኔው ተፈፃሚ ባለመሆኑ አምስት አባላት ያሉት ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ በአንድ ወር ጊዜያት ውስጥ የግምገማውን ሪፖርት ለም/ቤቱ እንዲያቀርብ መወሰኑን አመልክተዋል።

በአንድነት በኩል የመድረክ እንቅስቃሴ እንዲገመገም ፍላጎት ጠንካራ ቢሆንም ጉዳዩ ሲንከባለል ቆይቷል። የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ የተሰጣቸውን ይህንኑ ተልዕኮ በጊዜ ባለመፈፀማቸው ም/ቤቱን ይቅርታ ጠይቀዋል። ብሔራዊ ም/ቤቱም አጀንዳውን እንደገና በመውሰድ ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም ኮሚቴው በአንድ ወር ውስጥ ሪፖርት እንዲደረግ አዟል።

በዚህ መሠረት አቶ በላይ ፈቃዱ፣ አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ስዩም መንገሻ እና አቶ ብሩ ብርመጅህ ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን እንዲጀምር ተደርጓል።

አንድነት መድረክን የመገምገም ተልዕኮና መብት አለው ወይ ተብለው አቶ ዘካሪያስ ከሰንደቅ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ‘‘አንድነት የመድረክ መስራች አባል ነው። ስለዚህ መድረክ የተቋቋመለትን አላማ ጠንቅቀን እናውቃለን። በመሆኑም ግምገማው መድረክ የተቋቋመበትን አላማ በሚገባ እያሳካ ነው ወይስ አላሳካም፣ እንቅስቃሴው በሚፈለገው ፍጥነት እየሄደ ነው ወይስ አይደለም’’ የሚለውን የመገምገምና አቋም የመያዝ መብት አለው ሲሉ መልሰዋል።

እንደ አቶ ዘካሪያስ ገለፃ አብዛኛዎቹ የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት አባላት እምነት መድረክ ባለው ቁመና ልክ እየተንቀሳቀሰ አይደለም የሚል መሆኑንም ጠቁመዋል። በመሆኑም የመድረክ እንቅስቃሴ ተብትቦ የያዘው ነገር ምንድነው በሚል መንፈስ ግምገማው ተካሂዶ መፍትሄውንም ጭምር የማፈላለግና መድረኩን ወደተሻለ እንቅስቃሴ የማስገባት ጉዳይ ነው ብለዋል። ከአንድ ወር በኋላ የሚቀርበው ሪፖርት የአንድነት አባላት በመድረክ እንቅስቃሴ መጓተት ጋር ያለውን የቅሬታ ጉምጉምታ በወሳኝ ደረጃ ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት የፓርቲውን ፕሬዝዳንት የሶስት ወራት መደበኛ ሪፖርት አድምጦ ማፅደቁን፣ እንዲሁም በፓርቲው የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በመጪው ሰኔ 2005 ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራ ስለሆነ ለዝግጅቱ የሚያግዙ የኮሚቴ አባላትን አቋቁሟል። ፓርቲው በ2007 በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለውን አመራር ለመምረጥ መደበኛ ጉባኤው መጥራት ካለበት አንድ አመት አስቀድሞ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው ሰኔ ወር ይጠራል።

የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት በተጨማሪ ከፋይናንስ አሰባሰብ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ችግሮች ዙሪያ መምከሩም ታውቋል። በዚህ በኩል ያሉበትን ድክመቶች ለመቅረፍ ምክክር አድርጓል። አቶ ስዬ አብርሃ ከፓርቲ የመራቃቸው ጉዳይ ግን በም/ቤቱ አባላት ዘንድ አለመነሳቱም ታውቋል።

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት 45 ቋሚ እና 15 ተለዋጭ እንዲሁም አምስት የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት ያሉበት ከጠቅላላ ጉባኤው በመቀጠል ከፍተኛው የፓርቲው የስልጣን አካል ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 27, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 27, 2013 @ 1:41 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar