www.maledatimes.com የኢንተርኔት አገልግሎት አቅም በግማሽ መቀነሱን ኢትዮ-ቴሌኮም ገለፀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢንተርኔት አገልግሎት አቅም በግማሽ መቀነሱን ኢትዮ-ቴሌኮም ገለፀ

By   /   March 27, 2013  /   Comments Off on የኢንተርኔት አገልግሎት አቅም በግማሽ መቀነሱን ኢትዮ-ቴሌኮም ገለፀ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 31 Second

በመስከረም አያሌው

በባህር ጠለቅ የፋይበር ኬብል ላይ በደረሰ ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት የሀገሪቱ ጠቅላላ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅም 50 በመቶ መቀነሱን እና በመላው ሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት መጨናነቁን ኢትዮ-ቴሌኮም ገለፀ።

ድርጅቱ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስረዳው አፍሪካን፣ መካከለኛው ምስራቅንና እስያን ከአውሮፓ ጋር በሚያገናኘውና በሜዴትሪኒያን ባህር ውስጥ በሚያልፈው ኦፕቲካል ፋይበር ኬብል ላይ መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የተነሳ በኢንተርኔት ኮኔክሽን ፍጥነት ላይ ተፅእኖ አስከትሏል። ይህን የደረሰ ጉዳት ለመጠገን ሲኮም (SEACOM) የተባለው የቴሌኮም ኩባንያ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆንም የጥገና ስራው መቼ እንደሚጠናቀቅ ግን በእርግጠኛነት ለማወቅ አለመቻሉ ተገልጿል።

ኢትዮ- ቴሌኮምም የደረሰው ጉዳት በፍጥነት እንዲጠገን ካልሆነም ተጨማሪ የኔትወርክ አቅም በመፍጠር የተከሰተው የኢንተርኔት መጨናነቅ እንዲሻሻል ከሲኮም የቴሌኮም ኩባንያ ጋር ጥረት እያደረገ መሆኑ እና የተከሰተው ችግር እስከሚስተካከል ድረስም ደንበኞች በትእግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።¾

(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 394 መጋቢት 18 ቀን 2005)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 27, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 27, 2013 @ 1:42 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar