www.maledatimes.com እውነቱ ይደረሰው ከተስፋዬ ዘነበኖርዌይ(በርገን) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እውነቱ ይደረሰው ከተስፋዬ ዘነበ ኖርዌይ(በርገን)

By   /   March 30, 2013  /   Comments Off on እውነቱ ይደረሰው ከተስፋዬ ዘነበ ኖርዌይ(በርገን)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 13 Second

 

እኛ እኳ ነፃ ነን፣ ነፃነት የምናውቅ፣

በነፃነት ወልደው፣ያወረሱን ሰንደቅ፡፡

ልምዳችን እኳ ነው፣ መሞት ለነፃነት፣

ብዙ አባቶች አሉን፣ የሆኑ መስዋት፡፡

ብዙ ጀግኖች አሉን፣ ነፃነት የሰጡን፣
        ሃገርን እንደ ሃገር፣ በክብር ያወረሱን፡፡

ታላቅ ታሪክ አለን፣ የሶስት ሺህ ዘመን፣

እውነት የሚናገር፣ ጠብቆ ያቆመን፣

አንድ ሆነን እንድንቆይ፣ በምግባር ያነፀን፡፡

ድንቅ ነን ፈርጥ ነን፣ የአፍሪካ ጮራ፣

የነፃነት ቀንዲል፣ ከሩቅ የሚያበራ፡፡

ታዲያ በዚህ ዘመን፣ በቅሎ አራሙቻ፣

ታሪክን የሚንድ ሃገር የሚይጠፋ በባንዳ ዘመቻ፡፡

እውነት ሽሮ፣ ሀሰት ፈጥሮ፡፡

ይነግሩናል ታሪክ፣ የነሱን ፈጠራ፣

ትውልድ ሊያመክኑ ሃገር ሊበትኑ በተራ በተራ፡፡

ይነግሪናል ታሪክ፣ ውሃ የማይቋጥር፣

አንድነት የሚያፈርስ፣ የሚይሳጣን ፍቅር፡፡

በሌለ ልማት ስም፣ በደል ሲያጣ ድንበር

እስኪ ሃቁ ይግባው፣ በሆዳም በባንዳ ድርሻው፣

ተቀማቶ ጎዳና የሚያድረው፡፡

እናድርስ እውነቱን፣ የበደሉን አይነት፣

የግፍ ቀንበር ከብዶት፣ ነብሱ ለምትቃትት፡፡

መናኙ መነኩሴ፣ በዘር ተለክቶ፣

ከገዳም ሲባረር፣ በባንዳ ተገፍቶ፡፡

ጉራፈርዳ አማራው፣ሃብት ንብረቱን ትቶ፣

ከስፍራው ሲሰደድ በዘረኞች ብትር በሃይል ተገፍቶ፡፡

ሙስሊሙ ወገኔ፣ ተዉ እምነቴን ባለ፣

ሲታሰር ሲገረፍ፣ አንድ አመት ዘለለ፡፡

አባቶች ተዋግተው፣ ያስወጡትን ጠላት፣

በገመድ ለክተው፣ እርስት ሲሰፍሩለት፡፡

ወገን ሲፈናቀል፣ ከሰፈር ከቀዬው፣

የበደል መስፈርቱ፣ መለኪያው ምንድን ነው፡፡?

እናድርስ እውነቱን፣ የበደሉን አይነት፣

የግፍ ቀንበር ከብዶት፣ ነብሱ ለምትቃትት፡፡

ኢሳት እስትንፋስ ነው፣ የህዝብ ልሳን አንደበት፣

ሃቁን የሚያሳየን፣ የሚዘግብ እውነት፡፡

ሁሉም ጋር ይዳረስ፣ ይሂድ ከአፅናፍ አፅናፍ፣

እውነት የተጠማ፣ ልቡ በሱ ይረፍ፡፡

ሁሉም እጁን ይፍታ፣  ኢሳት የደጉም፣

ትግሉ እንዲፋጠን፣ የሕዝብ እንባ እንዲቆም፡፡

ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!

ሞት ለወያኔና ከፋፋዮች!!!            ለአስተያየቶ-ftih_lewegen@yahoo.com.

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 30, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 30, 2013 @ 3:30 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar