www.maledatimes.com ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠመግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

By   /   March 30, 2013  /   Comments Off on ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 45 Second

በተደጋጋሚ ፓርቲያችን እንደሚገልፀው አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና 
የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣
ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡
ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ
ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣
ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ
የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡
የከዚህ በፊቱን የማፈናቀል ግፍ ትተን በቅርቡ እንኳ በጉረፈርዳና በሌሎች አካባቢዎች በቀጥታ በክልሉ ባለስልጣናት በተፃፈ ደብዳቤ ይሄ
ሀገራችሁ አይደለም ተብለው፣ ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎ፣ የወለዱ አራሶች እንኳን የማገገሚያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ደማቸውን እያዘሩ ሲባረሩ
ከመንግስት የተሰጠው ምላሽ ‹‹ሞፈር ዘመቶች ናቸው (ማረሻውን ብቻ ተሸክሞ ወደ ሌላ ሀገር የሚሰደድ ለማለት ይመስለናል)›› የሚል ነበር፡፡
ይሄም ቢሆን የማንኛውም ዜጋ መብት ነው፡፡ መንግስት እነዚህ ዜጎች ‹‹ሃገራችን የት ነው?›› በማለት ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ የለውም፡፡
ገዥው ፓርቲ ሃላፊነትን መዘንጋትንና ስህተትን በማረም ፈንታ አፋፍሞ በመቀጠል ዜጎች ሃብትና ንብረታቸው እየተዘረፈ
መባረራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይህም በጋምቤላና ቤኒሻንጉል በከፋ መልኩ ቀጥሏል፡፡ በተለይ ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ተወላጅ
የሆኑትን ዜጎች የዘመናችን ሹመኞች ከኢ-ሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ ከእቃ ለሚሰጥ ክብር ባነሰ ሁኔታ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ
በጅምላ እየተጫኑ መጣላቸውን ቀጥለዋል፡፡ በርካታ ህፃናትም የዚህ ግፍ ሰለባ ሆነዋል፤ እየታፈኑ የሚሞቱትም ቁጥራቸው በርካታ
ነው፤ በጣም የሚያሳቅቀው ደግሞ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት 59 ሰዎች ሞት ጉዳይ ነው፡፡ ካላግባብ በጭካኔ ለብዙ ዓመታት
ከኖሩበት፣ ከወለዱበትና ከከበዱበት ስፍራ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እንዲወጡ በማድረግ ገደል ውስጥ
ገብተው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ዜጎችን ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረገውም በቸልታ እየገዛ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ነው፡
፡ መንግስት በነዚህ ዜጎች ላይ ለደረሰው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትና ህይወት ማጣት ተጠያቂ ነው በማለት ፓርቲያችን ያምናል፡፡
ፓርቲያችን አንድነትም ጥያቄ ያነሳል፡፡ ለውጭ ዜጎች እንዲበለፅጉበት በትንሽ ሳንቲም፤ ግልፅነት በጎደለውና በሙስና በተተበተበ አሰራር
ለቻይና ኩባንያዎች፣ ለህንድ ኩባንያዎች፣ ለሳዑዲ አረቢያ ኩባንያዎች ወዘተ ለዜጎቻቸው ቀለብ እንዲያመርቱበት በገመድ እየተለካ የሚሰጠው
የአዲስ አበባን ስፋት አምስት ጊዜ የሚበልጥ መሬት እንዴት ለዜጎቹ ይነፈጋል? ለምንስ ኢትዮጵያውያን ተዘዋውረው በኩርማን መሬት
ላይ ሃብት የማፍራት መብታቸውን ተነፈጉ? ይህንን ኢሰብኣዊነት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን
ሁሉ እንዲያውቁት እንፈልጋለን፡፡ ኢህአዴግንንና በእሱ የሚመራውን መንግስት ታሪክና ሕዝብ ይፋረደዋል፡፡ ይህንንም በደል እያዩና
እየሰሙ ዝም ማለት የወንጀሉ ተባባሪ መሆን ማለት ነው፡፡ ዛሬውኑ ተቃውሞአችንን፣ ጩኸታችንን እናሰማ፤ በደል ሰቆቃ በቃ እንላለን፡፡
በአቋማችንም፡-
1.ለዚህ ሁሉ አገራዊ ቀውስ ተጠያቂው መንግስት መሆኑን
2.ዜጎች እንዲሞቱ፣ እንዲጎሳቆሉና እንዲሰደዱ ያደረጉ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ
3.የሴቶችና ህፃናት መብት እንዲከበር
4.ማፈናቀሉ አሁኑኑ እንዲቆም
5.ተጎጅዎችም ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን፡፡
አንድነት ፓርቲ በዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና መባረር
የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
መጋቢት 20 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 30, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 30, 2013 @ 9:47 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar