www.maledatimes.com በሳኡዲ አራቢያ ጂዳ ወጣቱ በአረቦች ተገደለ የወጣቱን አስከሬን ለመስጠት መንግስት ፈቃደኛ አልሆነም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሳኡዲ አራቢያ ጂዳ ወጣቱ በአረቦች ተገደለ የወጣቱን አስከሬን ለመስጠት መንግስት ፈቃደኛ አልሆነም

By   /   March 30, 2013  /   Comments Off on በሳኡዲ አራቢያ ጂዳ ወጣቱ በአረቦች ተገደለ የወጣቱን አስከሬን ለመስጠት መንግስት ፈቃደኛ አልሆነም

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 21 Second

6788_10151553222719743_2060450314_nበሳኡዲ አረቢያ በአቋራጭ ጎዳና በመሰደድ አስከፊ ህይወታቸውን ለመታደግ ብሎም ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ደፋ ቀና እያሉ ከአገራቸው ዳር ድንበር እየተሰደዱ የሚገኙት ወጣቶች ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን የደረሰን ዜና ዘገባ ያመለክታል ። በዚህ ባሳለፍነው ረቡእ ማታ ከለሊቱ አምስት ሰአት ገደማ በአረቦች ተገደለ የተባለው ወጣት ።በሳኡዲአረቢያ ሊያኖረው የሚችል ፈቃድ ስለሌለው ብቻ እንዲገደል ማድረጋቸውን እና አስከሬኑ ወደ ሃገሩ ይላክ ሲባልም ህገወጥ የገባ ስደተኛ ስለሆነ ልንሰጣችሁ አንችልም በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ወገኖቻችን ገልጸዋል ። እንደ ህበረተሰቡ አገላለጽ ከሆነ ልጁን እኛ አልገደልነውም እያሉ ይዋሹናል የገደለው መብረቅ ነው ብለው እያሉ እኛንም እያስፈራሩን ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል ። በወቅቱም ምንም የአየር መዛባትም አልነበረም ዝናብ የለም ወቅቱ ሞቃታማ አየር የነበረው ምሽት ላይ ነው የተገደለው በማለት ይናገራሉ ።የተገደለው ልጅ ስሙ ወጣት አውራሪስ ተሾመ የሚባል ሲሆን ትውልዱም በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሃገር በኤፍራታና ጅሌ ወረዳ የካራቆሬ ከተማ ተወላጅ እንደሆነ እና አባቱም በካራቆሬ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፣የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እና መነኩሴ የነበሩ ሲሆን ይህወታቸውን በሙሉ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ህይወታቸው እንዳለፈ የተጠቆመ ሲሆን ይህ ልጃቸውም የመጨረሻው የአብራካቸው ክፋይ ነበር ሲሉ  ካገኙት የመታወቂያ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል ።  በወቅቱ ታላቅ ወንዱም ራቅ ብሎ በሚገኝ በዚያው ጅዳ የሚኖር መሆኑን የገለጹት የማለዳ ታይምስ ምንጮች  ወንድሙን ብስራት ተሾመን በማነጋገር አስፈላጊውን ድርጊት ለማድረግ ቆረጠው መነሳታቸውን ተናግረዋል። የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በአሁን ሰአት በጂዳ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለማነጋገር እና የዚህን ሟች አስከሬን ወደ ትውልድ አገሩ የሚላክበት ዘዴ ይፈጥር ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን ። እንዲህ አይነቱ ችግር ሲፈጠር ማናቸውም ግለሰቦችም ቢሆኑ በግላቸው ጥረት በማድረግ አስፈላጊውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳይታቀቡ የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ያሳስባል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በአረብ አገር ላይ እየተሰደዱ በሚገኙት ወጣቶች ላይ የድብደባ እና ግድያ ወንጀል መበራከቱን ባሳለፍነው ሳምንታት ያቀረብናቸው የምስል ቅንብሮች ማስታወስ የሚቻል ነው ። ማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለወላጅ ቤተሰቦቹ መጥናናትን እየተመኘ ለእልፈተ ህይወቱም የሰላም እረፍት ነፍስን በገነት ያኑርልን ይላሉ ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 30, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 31, 2013 @ 1:32 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar