www.maledatimes.com የጋናው ፕሬዘዳንት በድንገት ሞቱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጋናው ፕሬዘዳንት በድንገት ሞቱ

By   /   July 24, 2012  /   Comments Off on የጋናው ፕሬዘዳንት በድንገት ሞቱ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 36 Second

ከሁለት ወራት በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜጋዊ ጋር በአሜሪካ በተደረገው እና ጠቅላይ ሚኒስትራችንን አበበ ገላው ባስደነገጠበት ስብሰባ ላይ ተካፍለው የነበሩት እና የውስጥ ድንጋጤአቸውን በፈገግታ የመለሱት የጋናው ፕሬዘዳንት በዛሬው እለት ድንገት መሞታቸውን ሮይተርስ በድረ ገፁ ገልጾአል።

የጋናው ፕሬዝዳንት ጆሃን አታ ሚልስ ስድሳ ስምንት አመታቸው ሲሆን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ ዲሞክራት መሪ ከመሆናቸውም በተጨማሪ፤ሀገራቸው ሁለት ዲጂት እድገት እንድታመጣም ያደረጉ መሆናቸው ተነግሮላቸዋል። በሌላም በኩል አገራቸው በአለም በሁለተኛ ደረጃ የኮካዋ አምራች አገር መሆኑዋ ይታወቃል ። በእውነቱ ያልተጠበቀ እና ልብ የሚነካ አሳዛኝ ዜና ስንነግራችሁ ልባችን በሃዘን ተሰብሮአል ያሉት የመንግስት መስሪያቤት የቃል አቀባይ ቡድን እውነትም ሰአቱ እና ጊዜው ባልተጠበቀ ሁኔታ ማለፋቸው ክፉኛ አሳዝኖናል ብለዋል። ከመንግስት ምክር ቤት በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት ሰኞ እለት የህመም ስሜት እንዳለባቸው የገለጹ ሲሆን ማክሰኞ ማለዳ ህይወታቸው ተከትሎ ማለፉን ዜናው ያትታል። ሚል የነዳጅ አምራች አገር እንድትሆን የሚመኙላትን አገራቸውን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደነበር ገልጾ ባለፉት ጥቂት ወራት ለህክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ በማምራት የጤንነታቸውን ጉዳይ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኙ እንደነበር አጣርተው ተመለሰዋል ሲል ዘገባው ጠቁሞአል

ፕሬዝዳንቱ ለሞት ያበቃቸው ድንገተኛ ህመም እንደሆነም ዜናው ያትታል።

የኛስ ጠቅላይ ሚኒስትር የት ናቸው!? ጭምጭምታው ከህውሃት መንደር እንደተደበቀ አይቀረም …ማለዳ ታይምስ ነፍሳቸውን በገነት እንመኛለን

የጋናው ፕረዚዳንት ጆን አታ ሚል እኝህ ነበሩ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 24, 2012 @ 8:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar