www.maledatimes.com አንድ ጥያቄ አለኝ አቶ ብእረ-ከት ስምኦን እና (ወ/ስላስ ነጋ )አቦይ ስብሃት ፣መለስ እረፍት ላይ ነው ሲሉን አዎ አርፎአል ማለታችሁ ነውን ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድ ጥያቄ አለኝ አቶ ብእረ-ከት ስምኦን እና (ወ/ስላስ ነጋ )አቦይ ስብሃት ፣መለስ እረፍት ላይ ነው ሲሉን አዎ አርፎአል ማለታችሁ ነውን ?

By   /   July 24, 2012  /   Comments Off on አንድ ጥያቄ አለኝ አቶ ብእረ-ከት ስምኦን እና (ወ/ስላስ ነጋ )አቦይ ስብሃት ፣መለስ እረፍት ላይ ነው ሲሉን አዎ አርፎአል ማለታችሁ ነውን ?

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 15 Second

ከይፋቴው                        በተደጋጋሚ በወያኔ መሪዎች ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ሲነገር ሰምቻለሁ ትክክለኛ የሆነ መረጃ ለመስጠትም ሆነ ለመስማትም አልታደልኩም ፣ምክንያቱም የወያኔ መሪዎች ከአቶ መለስ ዜናዊ ጨምሮ የዉሸት ዋንጫዎች በመሆናቸው ሊሆን ይችላል ፤እኔም ብቻም አይደለሁም በመላው አገሪቱ ውስጥ ያሉት ህብረተሰቦች ዬነሱን ፕሮፖጋንዳ ከመስማት ተቆጥበው  እንዲያዉም ዘመን አመጣሾቹን ፌስ ቡክ እና ሌሎችንም የሶሻል ኔትዎርኮች ላይ የሚለጠፉትን ከልካይ የሌላቸውን መረጃዎች ለመስማት ተገዶአል ። ለምን ቢባል የመንግስት ያለህ ሲባሉ መንግስት የት ታውቃላችሁ እያለ በር የሚዘጋው መንግስት ሚዲያዎቹን ሁሉ አፍኖ ስለዘጋ ነው የሚሆነው መልሱ ። በዛሬው እለት ደግሞ እንዲህ ቀና ደፋ ስል እና ወሬ ስለቃቅም በሁፊንግተን ፖስት ላይ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ የጤነነት ሁኔታን አስመልክቶ አየሁ ፣ቀልቤንም ስቦት አነበብኩት የእኔም ጥያቄ የእነርሱ አይነት ጥያቄ ነበር እና አርእስተ ዜናቸው ሃተታውን የሚጀምረው የመለስ ጤንነት ሳይገለጽ መቅረቱን እና መንግስት ምንም መረጃ ሊሰጥ እንደማይችል ገልጦ አሁንም ህክምናቸውን እንደሚከታተሉ ይገለጻል ። በሌላም በኩል በዚሁ የመረጃ መረብ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት እረፍት ላይ ናቸው ሲሉ ጠቁመዋል ይላል እውነቱን እስኪ ይገለጽልን ? በእውነቱ አማራ ለተረት ማን ብሎት  እያሉ ሲገበዙብን ኖረዋል እና የተረት ቃላት ጨዋታ ሳይሆን የቅኔ ትርጉሙ እንደገባኝ ከሆነ “መለስ ዜናዊ እረፍት ላይ ናቸው ” የምትለዋ ሃረግ የምትገልጸው እውነትም ሞተዋል ግን እውነቱን አሁን አንነግራችሁም የስልጣን ሽኩቻችንን በውስጠ-ሚስጥር እንጨርስ ከጨረስን እና ከሆነ በሁዋላ እነነግራችኋለን ከሆነ መልሱ ይገባናል እኛም ጊዜ የምንሰጣችሁ ሰላማችንን እንድትሰጡን እንጂ  የናነተን ትቢያ የለበሰ የስልጣን ወንበር ፍለጋ አይደለም የምንፈልገው  እኛ ለህዝባችን ሰላሙን ለሃገራችን መልካሙን ፣ለፍላጎታችን ነጻነታችንን አትንፈጉን ። በሌላ ወገን ደግሞ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ለምትፈልጉት ወገኖችም ይሁን የስልጣን ጥመኞች እስኪ የአቶመለስ ቦታ ለምን ሊጥማችሁ አስፈለገ ብላችሁ የወያኔ መንግስታቶች ለምን አትጠይቁም? እናም እኮ ወንበራችንን እንፈልገዋለን …ወርቅ አንጥፈንበታል ፣ከስኳር መቃም ወጥተን የሰርዲን ቆርቆሮ መቀረፈፍ አቁመን ኮቾሮ መብላት እረስተን  በሰውነታችን ላይ ይረግፉ የነበሩትን የተለያዩ ተባያት አራግፈን የመጣነው ይህንን ፍለጋ ነበር በሏቸው እስኪ ምናለበት ምንስ ይሳናችኋል እናንተ እኮ ይህችንም ምድር የፈጠርናት እኛ ነን ሳትሉን አትቀሩም።  አባይን የደፈረ መንግስት እያላችሁ ስትሳለቁብን እውነት አቶ መለስ አባይን የደፈሩት በዋና ከጎዣም እስከ ግብጥ እና ቪክቶሪያ ድረስ ተጉዘው ይሆን እንዴ? ፣ምነው የአባይ በረሃን ድልድይ ሰብረው ሲገቡ ስሜት ያልሰጣቸው አባይ ዛሬ ምን ወኔ ሰጣቸው ፣ሞታቸውን ሊያቀልላቸው ነው እንዴ ፣ቢሞቱም እኮ እሳቸው የሰው ሞት እንጂ የአውሬ ሞት አልሞቱም የጀግና ሞት ሞቱ እንጂ የፈሪ አይደለም ፣ሰለ እውነቱ አቶ በረከት ቢሞቱ የሰነፍ ሞት ሞቱ ይባላል  ፣ አቦይ ስብሃትም እንደዚያው  ፣”የጀግና ሞት ሞቱ እንጂ የፈሪ አይደለም” በውስጣችሁ ለተፈጠረው ነገር ምንም እምነት ሳይኖራችሁ” የፓርቲያችንን ባህል ማወቅ ይጠቅማል “የምትሉን የውሸት ቋት እንደምትሰለቅጡ እናውቃለን ፣ግን እኮ እኛም ብልጦች ነን ባንዱ ሰምተን ባንዱ እናፈስላችኋለን ፣የትኛው የቁም ነገር ከረጢታችን የእናንተን አርቲ ቡርቲ አጠራቅሞ ይይዛል! ….”ጎመን በጤና” አለ ጸሃይ ዩሃንስ። ሌላም አማራጭ ልናገር በሰሜን አሜሪካ እና እንደዚሁም በአውሮጳ ያላችሁ የወያኔ ቀንደኛ ጀሌዎች ፡ስለ እውነት አንወሻሽ እና እስኪ እናንተ ምን አይነት ጥቅም ከወያኔ አግኝታችሁ ነው አገራችሁን በጥቅም የቸበቸባችኋት  ወያኔዎችስ ምን አይነት ግኝት አግኝተው ነው አገራቸውን ለህንድ እና ለአረብ ሲሸጡ ሲለውጡ የከረሙት ?እርስ በእራሳችሁ ተጠያይቃችኋል ወይስ እንዴት ነው እንዲያው በደፈናው አገር ለምታለች የሚለው የወያኔ ዲስኩር አስማምቶአችኋል ?እስኪ አገር ከለማች ለእስከዛሬው 21 አመታት ከውጭ መንግስታት እና በብድር የተገኘውን ገንዘብ በስሌት አስቀምጡልን ? የሃገሪቱን ጥሬ ሃብት እንዲያው ይቅር በመንግስት እጅ  ይዞታ ስር የነበሩት ትልልቅ ኩባንያዎች በጨረታ ተሸጠው ለህወሃት ልጆች ጡጦ መግዣ ተከፋፍሎአል ፣በሌላም በኩል የወያኔ ባለስልጣናት ምንም ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ውስጥ የለም ሲባል እና ሲደሰኮር የነበረውን የአፍሪካን ኢንተለጀንሲ ዔጀንሲ የተሰኘው ድርጅት  “ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር “በተባለው ጋዜጣው ላይ በየጊዜው በአፍሪካ ላይ የሚያደርገውን ምርምራዊ ጋዜጠኝነት እና የስለላ ስራ ሲያቀርብ በባለፈው 3 ወር እትሙ ላይ በሼክ መሃመድ አላህሙዲ ስም እና በተለያዩ ህወሃቶች በከፈቱአቸው ኩባንያዎች ስም በሚድል ኢስት  በፈረንሳይ እና ሌሎች አውሮጳ አገሮች ላይ የገንዘብ ክምችት እንዳላቸው የሚጠቁም መረጃ አውጥቶአል በተጨማሪም ዊኪሊክስም እንደዚያው ሰለህወሃት ሃብት አመጣጥ በስፋት ገልጾአል ፣ስለዚህ እናንተ የምን ተቀጥላ ናችሁ ። ተባይ እንኳን ተቀጥላ የሚሆነው የሚመገበውን ምግብ ለማትረፍ ሲል ነው <እውነት የወንድሞቻችሁ ደም ለነጻነት ብለው በየመንገዱ ሲረጭ ደስታን ይፈጥርላችኋልን?>ለማንኛውም ጽሁፌን ለማጠቃለል ያህል ከዚያም ከዚህም እያልኩ ለማጣቀሻነት ያቀረብኳቸውን ሃሳቦች እንደመነሻ ሃሳብ ለማድረግ እንጂ እውነት ሃሳቤን ቋጭቸው አልነበረም ሆንም ግን ሁኔታዎቹን በውል ለማወቅ ያስችለኝ ዘንድ ይህንን ያህል እላለሁ አዎ ዋሽቶ ለመታመን አይችልም ሆዴያለው ቴዲ አፍሮ ጉዳችሁን አይቶ አይደለምን ?አሁንም ቢሆን አቦይ ስብሃት (ወ/ስላስ )እና አቶ በረከት ስምኦን፣እውነት ምንጊዜም እውነት ናት ተደብቃ አትቀርም እና አነጋገራችሁን ለምደነዋል ተምረናል ፣አዎ መለስ እረፍት ላይ ናቸው አይመለሱም አርፈዋል ።በላችሁናል ተቀብለናል።

መሰል አርፎአል አዎ እረፍት ላይ ናቸው አርፈዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 24, 2012 @ 9:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar