www.maledatimes.com ከፕረዚዳንት ሚልስ ሞት በሁዋላ ፓርቲዎች መካከል መከፋፈል ተጀመረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከፕረዚዳንት ሚልስ ሞት በሁዋላ ፓርቲዎች መካከል መከፋፈል ተጀመረ

By   /   July 25, 2012  /   Comments Off on ከፕረዚዳንት ሚልስ ሞት በሁዋላ ፓርቲዎች መካከል መከፋፈል ተጀመረ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 13 Second

ባለፈው ጁላይ 21 የልደት በአላቸውን በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ያከበሩት እና በአሁን ከጥቂት ቀናት ቆይታ በሁዋላ ህልፈታቸው የተሰማው የጋናው ፕረዚዳንት ሚልስ ህይወታቸውን ማለፍ ተከትሎ የጋናው ብሄራዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የሆነው እና አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው ይኸው ፓርቲ መከፋፈሉን የብሎምበርግ ገልጾአል። የፓርቲው አባል እና በዲሴምበር ወር ለፕረዚዳንትነት ውድድር ላይ አሸናፊ የነበሩት ጆን ድራማኒ ማሃማ ይመረጣሉ ተበሎ ቢታሰበም ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ተገልጾአል ፣በጣም ፈጣን ፣ቀልጣፋ እና የተረጋጋ ልምድ አላቸው እያሉ የሚያሞግሷቸው እኝሁ ሰው ለሽግግር መንግስት ሊሆኑ የሚገባ ታላቅ ሰው ናቸው ሲል አክራ የሚገኘው ማእከላዊ የዲሞክራሲ ግንባታ centre for Democratic Development የተሰኘው ድርጅት ገልጾአል። ጋናውያን ለተሻለ ሁኔታ መምረጥ ያለባቸውን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል ይህንንም ደግሞ ጠንቅቀው የሚያውቁት ይመስላል  ።ይህ ካልሆነ ግን በጋንያውያኖች ጎዳና የከፋ ነገር ሊከሰት ይችላል ብለዋል ። በሌላም በኩል ሲገልጹ ጋናውያን የአፍሪካ የዲሚክራሲ መስመርን በማስያዝ ግንባር ቀደም ከሚጠሩት ተርታ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘች አገር ከመሆኑም በላይ ችግሮቻችንን አቅልለን መፍታት እንደምንችል አንጠራጠርም ሲሉ አክለው ገልጸዋል።   የሚልስ ሞትን እከትሎ ከስድስት ሰአታት በሁዋላ  ፕረዚዳንትነትን ቦታ በመተካት  ምክትል ፕረዚዳንቱ ጆን ድራማኒ ቃለመሃላ ፈጽመው ሃገሪቱን ለማረጋጋት እና ለመምራት ችለዋል ።በሌላም በኩል  የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት የ68 አመቱ ናና አኮፎ አዶ ከውድድሩ ሊታገዱ በቅተዋል ።በግብርና እና በተፈጥሮ ሃብት የእድገት መሰረቷን ያደረገችው ጋና በአለም አቀፍ በኮከዋ ምርት ሁለተኛ ደረጃ የያዘች አገር ከመሆኗም በላይ በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ፈጣን እርምጃ ያስመዘገበች አገር ተብላ መመዝገቧ እና መወደሷ ይታወቃል ። ማለዳ ታይምስ

በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የጋናው ፕረዚዳንት ሚልስ ከማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 25, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 25, 2012 @ 7:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar