www.maledatimes.com የኮ/ል ካሳሁን ትርፌ ህይወት እና እጣ ፈንታ በግሩም ተ/ሀይማኖት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኮ/ል ካሳሁን ትርፌ ህይወት እና እጣ ፈንታ በግሩም ተ/ሀይማኖት

By   /   May 1, 2013  /   Comments Off on የኮ/ል ካሳሁን ትርፌ ህይወት እና እጣ ፈንታ በግሩም ተ/ሀይማኖት

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 17 Second
የኮ/ል ካሳሁን ትርፌ ህይወት አሳዘነኝ አስነባኝም
በግሩም ተ/ሀይማኖት
የትላንትናው ወታደራዊ መረጃና ደህንነት ከፍተኛ መኮንን የሆኑት፣ የዛሬው ባለ ታሪክ የጎዳና ተዳዳሪ ኮሎኔል በጃንሆይና በደርግ መንግሥት ከሶማሊያ የጦር ግንባር እስከ ኤርትራ- ኡምሃጁር፣ ከረን፣ ተሰነይና ናቅፋ የጦር ግንባሮች የተሳተፉ ናቸው፡፡ እንዲሁም በመከላከያ ሚኒስቴርና በማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን በመሆንም የሰሩ ናቸው፡፡ እኚህ መኮንን ከባለቤታቸው ሞት በኋላ ለሁለት ዓመታት ያህል በጎዳና ተዳዳሪነት ቆይተዋል፡፡ እኝህ ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ ይባላሉ፡፡ revolutionfordemocracy.com ያወጣው አስደንጋጭ ዜና ነው የሆነብኝ፡፡
ኮ/ል ካሳሁን ትርፌን በነጻ ፕሬስ ውስጥ ያለፈ ሁሉ ያውቃቸዋል ብል ስህተት አይሆንም፡፡ ለእኔ በጣም በቅርብ ከማወቅ በላይም አውቃቸዋለሁ፡፡ ከዳግማዊ፣ የፍቅር ሕይወት፣ ቅይጥ፣ ጣዕመ ፍቅር፣ አስኳልና ምኒልክ ጋዜጦችን አብረን ሰርተናል፡፡ ምስኪን እና ታዛዥ የነበሩት ኮረኔል ያልሰሩበት ጋዜጣ የለም፡፡ የሰሩባቸውን መዘርዘርም ሁሉን የመጥቀስ ያህል ነው፡፡ ኮ/ል ካሳሁንን መጨረሻ ሳይ በእጅጉ በጣም ነው ያነባሁት ሁላችንስ መጨረሻንን መቼ እናውቃለን? ሳቃቸው፣ እጥረታቸው፣ ራሰ በረሃነታቸው… ብዙ ያማውቃቸው እውነታዎች ከፊቴ ተደቀኑ፡፡ ስንቶች ተርጓሚ ተብለው አደባባ የወጡበትን ስንት መጸሐፍት እንደተረጎሙ የምናውቅ እናውቃለን፡፡ ኮ/ል ጌታቸው ዝም ብሏቸው ይሆን?ከእሱ ትርጉም መጽሐፎች ጀርባ፣ ለእሱ ጋዜጣዎች ከጎዳናው ጀምሮ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ይህን የመሳሰሉ በርካታ ትውስታዎችን ወደኋለ መለስ ብዬ እንዳይ ያደረገኝ revolutionfordemocracy.com ያየሁት ዘገባ ነው፡፡ ገረመውን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡በዘገባህም በፊት ኮ/ል ሲያወሩት የማውቀውን እውነታ ነው ያሰፈርከው፡፡ የማውቀውን እውነታ አክዬበት ከታች ያለውንም የወሰድኩት ከዚሁ ሪቮሉሽነሪ ለዲሞክራሲ ከሚለው ኮም ላይ ነው፡፡ ታዲያ ልብ እንዲባልልኝ የምፈልገው በቅንፍ ውስጥ ያስቀመጥኳቸውን
ከ1987 ዓ.ም. በኋላ ኮሎኔል ሙሉ ጡረታቸውን ይዘው ከመከላከያ ተሰናበቱ(የጡረታዋ መጠን ቢገለጽ ግን የሚገርም ነበር፡፡ ከቤት ኪራይ የምታልፍ አልነበረችም)፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ መጻሕፍት ትርጉምና ወደ ግሉ ፕሬስ ነበር ፊታቸውን ያዞሩት፡፡(ይሄም ሄደት ጠብ ሲል ስደፍን የሚለው አይነት ነበር፡፡ምክንያቱም ቋሚ ሰራተኛ ባለመሆናቸው ያልተሰራ ጊዜ ሁሉም ዜሮ..ዜሮ ነበርና ነው፡፡) የተለያዩ ከውጭ አገር የሚመጡ ዜናዎችን በመተርጎም፣ የወቅቱን ዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ የሚወጡ ጽሑፎችን ለታሪክ፣ ለዓባይ፣ ለኢትኦጵ፣ (ለገናናው፣ ማዕበል፣ ዳግም ወንጭፍ፣ አርበኛው፣ አትኩሮች፣ መብረቅ…ለመሳሰሉት ጋዜጣዎች ላይ ይሰሩ ነበር) ማኅበራዊና በፍቅር ነክ መጽሔቶችና ጋዜጦች በነበሩት በቸኮሌት፣ (የፍቅር ጫዎታ፣ እውነተኛ ፍቅር፣ ቅይጥ፣ የፍቅር ሕይወት፣ ማዶና፣…) በጣዕመ ፍቅር፣ ሆሊውድ ላይ በጸሐፊነትና በተረጓሚነት መሥራታቸውን ያስታውሳሉ፡፡ (እኔ የራሴን ጋዜጣ ‹‹ገመና›› የሚል ጋዜጣ ስሰራም አብረን ሰርተናል፡፡)
በተለይ ፖለቲካዊ ጉዳዬችን በስፋት ይጽፉ በነበሩት በምኒልክ፣ በዓባይ ጋዜጣ ላይ በሰፊው መስራታቸውንና ከምርጫ 97 በኋላ እነዚህ ጋዜጣዎች በመዘጋታቸውና አንዳንዶቹም ባለቤቶቻቸው በመታሰራቸው አንዳንዶቹም ከአገር በመሰደዳቸው ምክንያት ከነጻ ፕሬስ ወጥተው በመጻሕፍት መተርጎም ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ነግረውኛል፡፡ ኮሎኔል በዚህ የመጽሐፍ መተርጎም ሥራ ላይ እስካሁን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጠኑ ረጃጅም ከሃያ በላይ የሚሆኑ የልቦለዶ ሥራዎችን ለሌሎች ሰዎች በመተርጎም ለገበያ ማብቃታቸውን ይናገራሉ፡፡ (ልብ በሉ በጎመን ደንደስ…ምን ይወደስ እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ እነዛ ሰዎች ዞር ብለው አይተዋቸው ይሆን?)
ኮሎኔል ባለቤታቸው ከብዙ ህመምና ስቃይ በኋላ ከዚህ ዓለም ከሞት ከተለየዋቸው በኋላ፣ ከባለቤታቸው ዘመዶች ጋር መግባባት በመጥፋቱ እንዲሁም አእምሮዋቸው በመረበሹና ጤናቸው በመቃወሱ በጃን ሜዳ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በአዲሱ ሚካኤል አካባቢ ከአንድ ዓመት በላይ በጎዳና ተዳዳሪነት እንዳሳለፉ አጫወቱኝ፡፡ በደጃች ገነሜ ትምህርት ቤት አጥር ስር ሰዎች በሠሩላቸው እንደነገሩ በሆነ የላስቲክ መጠለያ ውስጥ ነበር ኮሎኔልን ያገኘናቸው፡፡
ኮሎኔል ከአስከፊው የጎዳና ሕይወት በኋላ በቅርቡ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን ማእከል ባደረገላቸው ድጋፍ ወደ ማእከሉ ገብተው እንክብካቤ እያገኙ ነው፡፡ ኮሎኔል ካሳሁን ከነርቭ በሽታና በጎዳና ላይ ሳሉም ከነበራቸው ያልተመቻቸ ሕይወት የተነሣ በእግራቸው መሄድ አይችሉም፣ እናም የሚንቀሳቀሱት በዊልቸር ነው፡፡ በማእከሉ ተገኝቼ ሳያቸው ኮሎኔል የተጎሳቆለ ፊታቸው ተመልሶ፣ የነተበና የቆሸሸ ልብሳቸው ተለውጦ፣ ፊታቸው ላይ ደስታና ፈገግታ እየተነበበ ወንበር ላይ ተቀምጠው መጽሐፋቸውን እያነበቡ ነበር፡፡
ከጎዳና ሕይወት ወደ ተሻለ መጠለያ፣ ምግብ፣ ልብስና ሰብአዊ ፍቅርና እንክብካቤ ወደሚያገኙበት ወደእዚህ ዓይነት ማእከል በመምጣታቸው ኮሎኔል በእጅጉ ደስተኛ ናቸው፡፡ ኮሎኔል እንደነገሩኝ ማእከሉን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚያገለግሉ የአማኑኤል ሆስፒታል የሳይካትሪስት ነርሶች ሙያዊ ምክርና እገዛ ማግኘታቸው ጥሩ የሆነ ስሜትን እንደፈጠረባቸውም አጫውተውኛል፡፡
ኮሎኔል ካሳሁን ማእከሉን በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ወንድሞችና እህቶች፣ እንዲሁም አንዳንድ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ማእከሉን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶች የሚያመጡላቸው መጻሕፍትና ጋዜጣዎች የአልጋቸውን ራስጌና ግርጌ ከበውት ነበር ያየኹት፡፡ ኮሎኔል በአሁን ሰዓት እነዚህ ሰዎች ያመጡላቸውን መጽሐፍት በማንበብ ተጠምደዋል፡፡
እንዴት ነዎት? ስላቸው ‹‹ወንድሜ አሁን ደህና ነኝ፤ አእምሮዬም በጣም ደህና ነው፡፡ እንደበፊቱ ወደ ንባብና ትርጉም ሥራዬ እየገባሁ ነው›› በማለት እያነበቡት ያለውንና በእጃቸው የያዙትን ‹‹Among the Russians›› የሚል መጽሐፍ አሳዩኝ፡፡ እንዴት ያለ ግሩም መጽሐፍ መሰለህ በሚል የአድናቆት ቃል እያነበቡት ስላለው መጽሐፍም አወጉኝ፡፡
ባለፈው ሳምንት ‹‹አፍሪካን ኔግሮስ›› የሚል አንዲት ከአፍሪካ በባርነት ተሸጠው ከሄዱ ቤተሰብ የተወለደች አፍሪካ አሜሪካዊት ሴት የሕይወት ታሪኳን የተረከችበትን መጽሐፍ በተመስጦ አንብበው እንደጨረሱትም ነገሩኝ፡፡
‹‹ኮሎኔል ካሳሁን በቅርቡ በራሴና በመቄዶንያ ድርጅት ስም የሚታተም መጽሐፍ ለመተረጎም ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡ አንዳንድ ነገሮችን እንድታግዘኝ ስለምፈልግ እንዳትጠፋ›› አሉኝ ፈገግ እያሉ፡፡ አልጠፋም ኮሎኔል ብቅ እላለኹ ብያቸው ተጨባብጠን ተለያየን፡፡ ኮሎኔል ወደፊት የሕይወት ታሪካቸውን ለመጻፍ እንደሚፈልጉና ለዚህም የሌሎች ኢትዮጵያን ወገኖቻቸውን ድጋፍና እገዛ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል፡፡ ወደፊት ኮሎኔል ካሳሁን የሕይወት ታሪካቸውን የሚተርክ መጽሐፍ ጽፈው እንደሚያስነብቡን አንዳንች እርግጠኝነት በልቤ ውስጥ እየተሰማኝ ተሰናበትኳቸው፡፡
አሳዛኝ ቢሆንም የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን ማእከልን ከልብ አመሰግነለሁ፡፡ በተቻለ መጠን መረዳት ብቻ ሳይሆን መስራት ደሚችሉበት ብቃት የመለሳቸውን አምላክ እና ማዕከሉን በጥምረት ሳመሰግን እንዲህ አይነት ማዕከሎችን ከጎናቸው ሆነን ለወገን እንድንደርስ ጥሪም እያስተላለፍኩ ነው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 1, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 1, 2013 @ 12:06 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar