www.maledatimes.com የጊቢ ሞት በተባለ ኦፕሬሽን በየመን ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከአፋኞች ነጻ ወጡ ግሩም ተ/ሀይማኖት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጊቢ ሞት በተባለ ኦፕሬሽን በየመን ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከአፋኞች ነጻ ወጡ ግሩም ተ/ሀይማኖት

By   /   May 1, 2013  /   Comments Off on የጊቢ ሞት በተባለ ኦፕሬሽን በየመን ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከአፋኞች ነጻ ወጡ ግሩም ተ/ሀይማኖት

    Print       Email
0 0
Read Time:40 Minute, 30 Second
     ለሰሞኑ የየመንን መገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበው የኢትዮጵያያኑ ላይ እየጠፈጸመ  ያለው አሰቃቂ ስራ ሲሆን ከችግሩ ጀርባ ያለውን እውነታንም በይፋ እየተናገሩ ነው፡፡ እስከዛሬ የነበረ ድምጻችን፣ መፍትሄ ይፈለግ ጥያቄያችን ሰሚ አግኝቶ የየመን መንግስት በየቦታው ያሉ ታጋቾችን ሲያስለቅቅ ከችግሩ መፈጠር ጀምሮ እስከ መንግስት አካላት ድረስ መነካካት እንዳለበት አጋልጠዋል፡፡ አሁንም ከአጋቾቹ ነጻ ከወጡ በኋላ ስደተኞቹ ላይ አግባብ ያልሆነ ነገር እየተፈጸመ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ስለሁኔታውና የዘገቡትን እውነት እያመሳከርኩ እንይ፡-
      ባለፈው ረቡዕ ምሽት ማታ ተንቀሳቃሽ ስልኬ ደጋግሞ ‹‹ወሬ ሊያቀብልህ የመጣ ሰው አለ ክፈት..ክፈት..›› እያለ አንቃጨለ፡፡ ቁጥሩን የማወቀው ወዳጄ እና የሞያ አጋሬ ጋዜጠኛ መሀመድ ደርማን ነው፡፡ መሀመድ ደርማን ኢትዮጵያዊያኑ በህገ-ወጥ አጓጓዦች እየታገቱ የሚደርስባቸው ስቃይ የውስጥ እግር እሳት ሆኖ ያቃጥለዋል፡፡ እውነታውን ከመረጃ ጋር ካሳየሁት በኋላ በቁጭት እሳት ተርመጥምጦ ከሞት ጋር ለመታገል ቆርጦ ተነሳ፡፡ ይሄ ሰብዓዊነት የተላበሰ ሀሳቡ ነው ያገናኘን፡፡ ያግበባን፡፡ ከዚህ በፊት በሁለት ዙር የየመን መንግስት ወታደሮች ከአጋቾቹ ጋር ተዋግተው ኢትዮጵያዊያኖቹን ነጻ ሲያወጡ ቦታው ላይ በመገኘት ዘግቧል፡፡ ባለፈው ሳምንት ግን የመንግስት አካላት እጅ እንዳለበት ከዘገበ በኋላ ችግር ተፈጠረ፡፡ ደጋግሞ የሚያንጫርረው ስልኬን ከፈትኩት…
   ‹‹አሎ! ኬፍ አለክ ያ-አኪ ጉሮም አነ መሀመድ ደርማን…›› እንደምነህ ወንድሜ ግሩም እኔ መሀመድ ደርማን ነኝ የሚለውን ቃሉን አቀበለኝ፡፡ ‹‹አረፍት ኬፈክ ያ-ሪጃል ሰሀፊ!››  አውቄሀለሁ አንተ ወንድ(ጎበዝ) ጋዜጠኛ አልኩት
    ‹‹አልዬም  ሾዬ መርቡሽ አሸን ከወፉኒ ሙጅሪሚን…›› ዛሬ ትንሽ ተረብሻለሁ፡፡ አሸባሪዎቹ ረበሹኝ አለኝ እና ነገ እንገናኝ የሚለውን አስከተለ፡፡ በማግስቱ በተቀጣጠርንበት ሰዓት ቤቴ መጣ፡፡ የተረበሸው ቢሯቸው ፎቅ ስር 400 ግራም የሚመዝን ቲንቲ /TNT/ ፈንጂ አጥምደውባቸው ሳይፈነዳ ለደህንነቶች ጠቁመው መክሸፉን ነገረኝ፡፡
      ቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ እንዲሰራ አደረጉት እንጂ ፈርቶ ወደኋላ እንደማይል ነገረኝ፡፡ ያበርታህ የሚለውን በሆዴ አልጎመጎምኩ፡፡ ይህን ያነሳሁት አፋኞቹ ምን ያህል የጠነከሩ ሲነኳቸው ለማጥፍት እንደሚሄዱ ላሳየት ነው፡፡ አጠቃላይ ዘገባውን ስቃኝ ደግሞ…በዚህ ወር ብቻ ባህሩን ተሻግረው የመን ከገቡ ኢትዮጵያዊያኖች መካከል በአጋቾች ከተያዙት ውስጥ ወደ 1000 የሚሆኑት ነጻ ወጡ፡፡ በሀረጥ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች ድንበሩን ጠባቂዎች እና የመንግስት ወታደሮች(የመከላከያን ሰራዊት) በማስተባበር አካባቢውን በመፈተሸ ከአንድ ጊቢ ብቻ 210 አስፈቱ፡፡ በ22/04/13 እሁድ ዕለት ከተያዙት ውስጥ 89 ሴቶች ሲሆኑ 10 ህጻናት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በግርፋት፣ በድብደባ፣ በእሳት ማቃጠል፣ በመደፈር..የተጎዱ አካላቸው የደቀቀ እና የተጎሳቆሉ ናቸው፡፡
      ከአፈና የተፈቱት የሰጡትን ቃል ስንመለከት……ካህሳይ ሚኬሌ እና ወንድሙ የደረሰባቸው ግፍ በጣም ሰቅጣጭ ነው፡፡ ‹‹..በጣም በጣም ነው የደበደቡን፡፡ በብረት ሁሉ ደብድበውናል፡፡ ላስቲኩን በእሳት እያቃጠሉ ሰውነታችን ላይ ያንጠባጥቡታል፡፡ ስልክ ሰተውህ ለዘመዶችህ ደውል ይሉሀል፡፡ ደውለህ የሚልክልህ ከሌለ ዘመዶችህ እንዲሰሙ ነው እላይህ ላይ የቀለጠውን ላስቲክ ጠብ እያደረጉ ስትቃጠል እና ስትጮህ ቤተሰቦችህ እንዲወሰሙ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ስቃይ መካከል ወንድሜ ህይወቱ አለፈ፡፡ገንዘብ ለማግኘት ወጥተን ወንድሜን በሞት አጥቼ ሌሎቻችንም አካላችንን ከፈልን..›› በማለት ተናግሯል፡፡ ለስምንት ወርም በእንግልት ቆይቷል፡፡
    ንጉሴ በግሩፕ ሲጓዙ ከነበሩት አንዱ ነው፡፡ ‹‹.ከባህር እንደወረድኩ ተያዝኩ፡፡ ተደበደብኩም፡፡ ከሚደበድቡት መካከል ኢትዮጵያዊያንም አሉበት፡፡ ከድብደባ ብዛት ግራ እግሬ ተሰበረ፡፡ ስቃዩ ሲብስብኝ ወደ ኢትዮጵያ ደወልኩ፡፡ ግዳቸውን የሳዑዲ 1000 ሪያል ላኩልኝ፡፡ ተደብድቤ አካሌ ከጎደለ በኋላም ቢሆን ተላከልኝ አውጥተው በረሃ ላይ ጣሉኝ፡፡ ሲጥሉኝ ራሴን አላውቅም ነበር፡፡ ስነቃ ራሴን ጭው ያለ በረሀ ስጥ አገኘሁት፡፡ደግ የመናዊያን አግኝቼ 10 ኪሎ ሜትር ወስደው ተከምኩኝ፡፡ ይህን ድርጊት የሚፈጽሙት ሀይል ያላቸው እና ከመንግስት ሰው ያላቸው ናቸው፡፡….›› ንጉሴ ከኢትዮጵያ ላኩልኝ ብሏል፡፡ በደንብ ስላላብራራው እኔ ልግለጸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ወኪላቸው በፖሊስ ተይዞ ፍርድ ካገኘ በኋላ ዘዴ ቀይረዋል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የሚያውቁት ሰው ይፈልጉ እና እሱ በሳዑዲ ሪያል 1000 ለእነሱ ይልካል፡፡ የታጋቹ ቤተሰቦች የሳዑዲ 1000 ሪያል የሚሆነውን በኢትዮጵያ ብር ከሳዑዲ ለላከላቸው ቤተሰቦች ይሰጣሉ፡፡
   አካባቢው ላይ ያለ ባለስልጣን ሲናገር ደግሞ ‹‹..ሆስፒታል ውስጥ 27 ሬሳ ፍሪጅ ውስጥ በስብሷል፡፡ የእነዚህ ሰዎች አሟሟ ት በስቃይ ለመሆኑ በሰውነታቸው ላይ ያለው ምልክት ያስረዳል፡፡ እስካሁንም ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ነው፡፡ መቅበር አልቻልንም፡፡ ፍርድ ቤቱ እንዲቀበሩ ቢፈርድም እስካሁን ከሶስት ወር በላይ ሆኗለወ አልተቀበረም፡፡ይህ የሆነው ግን መውበሪያ ስላጣን ነው፡፡አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት IOM እና UNHCR አንድ ላይ መሬት ሊገዙ ተስማሙ፡፡ እኛ ሁኔታውን ለማወቅ ከሆስፒታሉ ጋር መረጃ እንለዋወጥ ነበር፡፡ የሚገዛ መሬቱ ተገኘ አልተገኘ እንጠይቃለን፡ በኋላ መሬቱ ተገኘ ተስማሙ እና ተገዛ፡ በሳምንቱ ለመቅበር በቦታው ተገኘን፡፡ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አምጥተው ሊቀብሩ ሲሉ የአካባቢው ሰው አይቻልም እዚህ አይቀበሩም አሉ፡፡ዳግም ሆስፒታል ተወስደው እ ነው አሁንም ሬሳው….›› ብሏል ባለስልጣኑ፡፡ ጋዜጠኛው ራሱ ሲመሰክር ‹‹..ማዳ የተባለ ቦታ ብዙ የስደተኞች ሬሳ አገኘን፡፡ የብዙዎችን ሬሳ በየበረሃው አገኘን፡፡ አሰቃይተው በእሳት ካቃጠሉዋቸው በኋላ ይጥሏቸዋል፡፡
  ይህን በተመለከተ አል-ተውራ ተብሎ የሚጠራው የመንግስት ጋዜጣ ደግሞ አካባቢው ላይ ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው በለስልጣናት በዝምታ መለጎማቸው እና መንግስት የሰጠው ክፍተት ለዚህ አንዳደረሰ ዘግቧል፡፡ በዘገባውም ሀረጥ አል-ዘሀራ የተባለ ቦታ 48 የታፈኑ ሰዎች አሉ፡፡ በተደጋጋሚ የመንግስት ወታደሮች ሊያስለቅቋቸው ሞክረው እነዚህን አጋቾች ሊረቱ ስላልቻሉ 48 ሰዎች እስካሁን እንደያዙዋቸው ነው፡፡ የመንግስት ወታደሮች ሲናገሩ አጋቾቹ ሊያስጠጉን አልቻሉም ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳልብን አለወቅንም ብለዋል፡፡
    ይህ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ጋዜጣ የሚባለው ቶውራ የመንግስት ቁጥጥር መላላት እንደሆነ ለችግሩ መንስኤ ገልጾዋል፡፡ ይህ ወንጀል በሚሰራበት አካባቢው ያሉት የወታደር እና ደህንነት ዝም ማለት የፈለጉት አፋኞቹ (ህገ-ወጥ አጓጓዦቹ) ከጀርባቸው ትላልቅ የመንግስት ባለስልጣናት ስላሉ መሆኑን ዘግቧል፡፡
       እኔ እስካውቀው ደግሞ ይ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አይደለምም፡፡ አካባቢው ላይ ላሉ ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን ድንበር ጥበቃ ላይ ያሉት ሰዎች በባህር በገባው ስደተኛ ልክ ማለት በአንድ ሰው ሂሳብ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲያውም ከዚህ በፊት ባናገርኳቸው ሰዎች መረጃ መሰረት ጀልባው ቀድሞ ሲመጣ እንኳን ደውለው እንደሚጠሯቸው ነው፡፡ የመን ግልጽ ሙስና የሚከናወንባቸው ከሚባሉት ሀገሮች ተርታ በመሆኗ ሲታሰሩ እንኳን በገንዘብ ሀይል እንደሚወጡ የታየ እውነታ ነው፡፡ ማጣራት እስክችል ድረስ ስሙን ለመጥቀስ ባልፈልግም አንድ በዚህ ስራ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ አግቶ ከያዛቸው 60 ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር የየመን መንግስት በቁጥጥር ስር አዋለው፡፡ ከ80000 የሳዑዲያ ሪያል ከፍሎ ከእስር ተፈታ፡፡ ይሄ ያለውን ሙስና ለማሳየት ያሰፈርኩት ይሁን እንጂ ኤምባሲውም ሊፋረደው ሲገባ በአቅራቢያው ያሉ እዛው ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሰዎች ሲያስፈቱት ዝም ማለቱ ምን እንደሚያሳይ መገመት አያቅትም፡፡
      በኤምባሲ ዙሪያ ካነሳሁ በነካ አፌ ልጨርሰው እና ልለፍ፡፡ ሰሞኑን ቅጥ ያጣውን እና በየእስር ቤት ውስጥ ተሰግስጎ ያለውን ኢትትዮጵያዊያ ስደተኞች ወደ ሀገር ለማስገባት አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን ከቢሮው አካባቢ የገኘሁት መረጃ ያስረዳል፡፡ በየእስር ቤቱ ያሉትን ወደ 3000 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ለማሰገባት የሚደረገውን ጥረት ተቀብለው አሁን በቅርቡም 469 ስደተኞችን ወደ ሀገር ለመመለስ መመለሻ ወረቀት (ሊሴ ፓሴ) እያጋጁ መሆኑም ታውቋል፡፡ ኤምባሲው አሁን ከምን ጊዜውም በላይ ትብብር ማሳየቱ ደስ የሚል ጅምር ነው፡፡
     ወደ ጋዜጣው ገባ ስገባ በየቦታው የኢትዮጵያዊያኑ ሬሳ ወድቆ እንደሚገኝ፣ እንደሚታይ እና ጸሀሪው ራሱ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ማየቱን ተናግሯል፡፡ የቀሩትን ታጋቾች ለምን እንደማያስለቅቁ ሲጠይቃቸው አለመቻላቸው እና ከመንግስት ወታደር የተሻለ ሀይል እንዳለው እንደሚናገሩ ገልጾዋል፡፡ እንዲያውም በቦታው ላይ ያሉትን ሀላፊዎች ሲያናግራቸው ከፍርሃት የተነሳ አንድም ቃል አልሰጡንም፡፡ ለነፍሳቸው ፈሩ..ብሏል፡፡ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ጊቢ ውስጥ ሲገቡ ያዩት በጣም ሰቅጣጭ እንደነበረ የገለጸው ጋዜጠኛ ብረት አግለው ሰውነታቸውን ከጠበሷቸው አንስቶ አሰፈሪ እና ሰቅጣጭ ሁኔታ የተፈጸመባቸው ለማየት በቅተዋል፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች ግን በአስጸያፊ ስድብ በፖሊስ ከጊቢ እንዳስወጧቸው ዘግቧል፡፡ እንዲያውም እንዳንገባ እና ጉዱን እንዳናይ ዱላ ቀረሽ በሆነ ሁኔታ መለሱን፡፡
   ይህ ሁኔታ ሲታይ እነዚህ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዱን እየደበቁ ተደፋፍኖ እንዲቀር የሚፈልጉበት ሁኔተሰ እንዳለ የዘገበ ሌላ ጋዜጠኛም አለ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡
የጊቢ ሞት በተባለ ኦፕሬሽን በየመን ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከአፋኞች ነጻ ወጡ
                                                       ግሩም ተ/ሀይማኖት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 1, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 1, 2013 @ 10:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar