www.maledatimes.com በህማማት እለተ ሃሙስ ስንቶቻችን ታመምን? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በህማማት እለተ ሃሙስ ስንቶቻችን ታመምን?

By   /   May 2, 2013  /   Comments Off on በህማማት እለተ ሃሙስ ስንቶቻችን ታመምን?

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 11 Second

*ዛሬ ስንቶቻችን ታመምን??? *
“እሳት ወይ አበባ” ን በዛሬው እለት ያልገለጠ፣ “ሰቆቃወ ጴጥሮስ”ን ያላነበበ፣ ባያነብም እንኳን በአዕምሮው ያላቃጨለበት፣ የሎሬቱን ብሶት ያልተጋራ ማን ይኖር ይሆን,,,,,??? ቢሆንም ግን መነበቡ መፍትሄ አላበጀም፣ መታወሱ ማስተዋልን አልፈጠረም። መነሳቱ አግባብ አይደለም ቅርስ ነው; አይ አግባብ ነው ለልማት ነው; በሚሉ ሁለት ሀሳቦች መከፈላችን የሁለት የተለያዩ ሀገራት ህዝቦች እንድንመስል አድርጎናል። ሁሉም የራሱን ሀሳብ መከተል የሚችልበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም; ሀሳቡን መተግበር ግን አልቻለም; አሃ! መነሳቱን ምንቃወም ሁሉ እንደ ደጋፊ ሐውልቱን አጅበን ሸኘን እኮ! ስለዚህ አንድ ሀሳብ ብንሆንም ምንም ማናመጣ ትውልድ አይደለንም እንዴ ጎበዝ???? 

በፀሎተ ሐሙስ በመጨረሻው እራት የመጀመሪያው ድፍረት; የታሪክ ንደት ሲካሔድ፣ ሎሬቱ በህይወት ቢኖሩ “ሰቆቃወ ጴጥሮስ 2″ን ቀልመው ዳግም ባስነበቡን; ባስለቀሱን ነበር። የዛሬውንስ እንኩዋንም አላዩት በምን አንጀታቸው ሊችሉት? በምን አይነት ቃላት ስሜታቸውን ሊገልፁት? አረ እንኳንም አላዩት እንኳንም ጉዳቸውን አልሰሙት። መቃብራቸው እየታዘበን እኛው እንየው እንጂ፣ ከንፈር እየመጠጥን ቆመን እንሸኘው እንጂ፣ እሳቸው በምን ጭካኔአቸው በዚህ ትውልድ መሀል ይቁሙ፣ አረ እንኳንም አልኖሩ።

እውነት ግን የሐውልቱ መነሳት ግድ ነበር??? የባቡሩ መስመር ማለፍ የሚችለውስ በዛ በኩል ብቻ ነበር??? እውነት ሰንት ዘመናዊ ህንፃዎች እንዳይነኩ ተብሎ; በየሰፈሩ ስንት መንገዶች ህንፃዎችን በማይነካ መልኩ አልተቀየሱምን??? ስለእነሱ ሲባልስ የብዙሀኑ ወገኖቻችን ማረፉያ ያለፕላን አልፈራረሰምን??? ለህንፃዎች የመንገድ ፕላን መቀየር ከተቻለ ታዲያ ምነው ለሐውልቱ ግዜ አማራጭ ቅያስ ጠፋ??? እውነት በጣም ያማል። እንዲሆን የማንፈልገውን ነገር ሳናምንበት አሜን ብለን የምንቀበል ምንም ማድረግ የማንችል ትውልዶች መሆናችን በእውነት በጣም ያማል። ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ስህተት፣ በስንት አፅም የሚያስወቅስ የታሪክ ንደት ነው ዛሬ የተካኼደው።

በአካል የተገኛችሁ እንዴት ቻላችሁት ይሆን? እኔ በሬዲዮ ነበር ስረዓቱን ስሰማ የነበረው በምን ቃል ይገለፃል??? ሽለላ ፉከራው፣ መዝሙሩ፣ ግርግሩ፣ የደስታ ይሁን የሀዘን፣ የክብር ይሁን የቁጭት; ግራ ግብት ነው የሚለው። አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ ላይ ያረፉ ያህል ነው ነገሩ የሚያሳምመው። የአስከሬን ሽኝት ያህል አይንን በእንባ የሚሞላ ክስተት!,,,, እውነት ነው ዛሬ ነው ያረፉት ያለፍላጎታቸው የተንቀሳቀሱት፣ የዛኔማ ወደው ፈቅደው ነው ስለሀገራቸው እና ሰለሀይማኖታቸው ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት። ያን ቀንማ አልሞቱም; ተሰየፉ እንጂ; የሞቱት ዛሬ ነው። ህይወታቸውን የሰጡለት ትውልድ ተቃውሞውን እነኳን ማሰማት ባልቻለበት ዕለት; ደማቸውን ያፈሰሱላት መሬት ሐውልታቸውን አቅፋ ይዛ አላስነካም ብላ ባላስከበረቻቸው እለት; ዛሬ ነው የሞቱት። አቤት ያቺ አደባባይ እንዴት ጭር ብላ ይሆን? ሲያይዋት እንዴት ሆድ ታላውስ ይሆን???,,,,,,,,,,,,

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የቀላል ባቡር መንገድ ስራው ተጠናቆ ወደ ቦታው እስኪመለስ ሁለት ዓመታት ያህል ይፈጃል ይሉናል ሚዲያዎች። እስኪ እድሜ ይስጠን; ለነገሩ ሲነሳ ዝም ያልንበት ድንድን ልባችን ለምን አልተመለሰም ብሎ ዘራፍ ይል ይሆን??? እስኪ ለሁሉም አምላክ ያውቃል። ማድረግ የምንችለውንም የማንችለውንም ነገር ሁሉ ላንተ ትተነዋል ስንል; አንድ ቀን ብቻ ትግስትህ አልቆ ባለው ላይ የባሰ እንዳታመጣብን አደራህን የኢትዮጵያ አምላክ??? እውነት ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮች በዝተውብናል የኢትዮጵያዊነታችንን ደም የሚያንተገትጉ ክስተቶች ተበራክተውብናል,,,,,,,, እውነት ነው ያ! ሆኖ እነጂ,,,ግድ ሆኖብን እንጂ,,,, በእውነት የእያንዳዳችን ስጋ ቢቆረጥ; ደማችን በሶስት ቀለማት ያሸበረቀ ነው። ቀስተ ደመናችን የደም ስራችን ነው። እናም አምላክ ሆይ! የተሻለ ነገን አምጣልን እንጂ አትዘንብን።
ቸር ይግጠመን!!!

/ኤልሳ ተስፋዬ/,,,,,,,,, (ፀሎተ ሐሙስ) ሚያዝያ 24/2005

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 2, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 2, 2013 @ 2:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar