www.maledatimes.com ከትንሣኤ በዓል ጀምሮ የሥጋ መሸጫ ዋጋ ተተመነ በታደሰ ገብረማርያም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከትንሣኤ በዓል ጀምሮ የሥጋ መሸጫ ዋጋ ተተመነ በታደሰ ገብረማርያም

By   /   May 3, 2013  /   Comments Off on ከትንሣኤ በዓል ጀምሮ የሥጋ መሸጫ ዋጋ ተተመነ በታደሰ ገብረማርያም

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 3 Second

የቄራዎች ድርጅት ለየት ያለ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸከትንሣኤ በዓል ጀምሮ የሥጋ መሸጫ ዋጋ ተተመነ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በተቋቋሙት የሕዝብ መዝናኛ ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ሥጋ ቤቶች አንዱን ኪሎ ሥጋ ከፍተኛው በ80 ብር፣ ዝቅተኛው ደግሞ በ70 ብር ሒሳብ እንዲሸጡ ተወሰነ፡፡

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበርም ለሚገዛቸው የቁም እንስሳት ደረሰኝ ባለማግኘቱ ምክንያት ከትንሳኤ በዓል ዕለት ጀምሮ የሥጋ ሽያጭ አገልግሎት መሰጠት እንደሚያቆም ያሳለፈውን ማስጠንቀቂያ አነሳ፡፡ መደበኛ ሥራውንም እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንደገለጸው፣ የመሸጫ ዋጋውን የወሰኑት በየወረዳዎቹ የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድ ኪሎ ሥጋ እስከ 150 ብር በሚሸጥበት ሁኔታ በሕዝብ መዝናኛ ተቋማት የሚገኙ ሥጋ ቤቶች ከትንሳኤ በዓል ዕለት ጀምሮ በተወሰነው ዋጋ እንዲሸጡ በመደረጉ፣ ከፍተኛ የሆነ የገበያ መረጋጋት እንደሚፈጠር ቢሮው ገልጿል፡፡

በካዛንቺስና በቦሌ አካባቢ አልፎ አልፎ በተቋቋሙት የሕዝብ መዝናኛ ክበብ ውስጥ የሚገኙት ሥጋ ቤቶች ከገና በዓል ጀምሮ ከፍ ብሎ በተወሰነው መሠረት በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ከቢሮው ሕዝብ ግንኙነቱን ክፍል ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ወልደገብርኤል አባተ እንደገለጹት ከሆነ፣ ማኅበሩ ቀደም ሲል ያስታወቀውን ማስጠንቀቂያ በማንሳት መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንዲጀምር የተነሳሳው ደረሰኝ ማግኘቱን በተመለከተ ጉዳዩ በይበልጥ ከሚመለከታቸውና በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በሰፊው ከተወያየና ከስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ነው፡፡

ማኅበሩ ደረሰኝ የማግኘቱ ጥያቄ መፍትሔ እንዲያገኝ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ አካላት ለሦስት ዓመታት ያህል ሲወተውት ቢቆይም፣ እስካዛሬ ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሔ እንዳላገኘና ይህ ዓይነቱም ሁኔታ ለኪሳራ እንደዳረገው አስረድተዋል፡፡

በውይይቱም ወቅት ጉዳዩ የቆየና ውስብስብ ባህርይ ያለው በመሆኑ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስፈላጊውን መፍትሔ ለመሻት የሦስት ወራት ጊዜ እንዲሰጣቸው የተቋማቱ ተወካዮች አሳስበዋል፡፡ በዚህም የተነሳ መፍትሔ ለመሻት ሲባል ጥያቄያቸውን መቀበል ግድ በመሆኑ ከስምምነት ላይ ሊደርስ እንደተቻለ አቶ ወልደገብርኤል ተናግረዋል፡፡ የዋጋው ሁኔታ ከቀድሞው ምንም የተለየ ነገር እንደሌለው፣ እያንዳንዱም የማኅበሩ አባል ይህንኑ ተገንዝቦ ለኅብረተሰቡ ቀና አገልግሎት እየሰጠ መፍትሔውን በትዕግስት እንዲጠባበቅ ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቄራዎች ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም ደሳለኝ፣ ድርጅቱ ለየት ያለ አገልግሎት ከሚያበረክትባቸው የሥራ መስኮች መካከል አንደኛው ለቅርጫ ተደራጅተው ለሚመጡ ተጠቃሚዎች የሚሰጠው አገልግሎት ይገኝበታል ብለዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ጤንነቱ ባልተጠበቀ አካባቢ እንስሳቱን ከሚያርድ ይልቅ እንስሳቱን በቁመና ለድርጅቱ በማስረከብ ለዚህም የአገልግሎት 185 ብር ከፍሎ ካሳረደ በኋላ፣ ሥጋውን የሚፈለግበት ቦታ ድረስ ድርጅቱ አጓጉዞ ቅርጫው በባለሙያ እንዲከፋፈል ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ በአካባቢ ባቋቋማቸው ስምንት ሱቆችና እንዲሁም በጎፋ ማዞሪያና በቦሌ አያት በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በከፈታቸው ሁለት ሱቆች ውስጥ ጤንነቱ የተረጋገጠ የበግ ሥጋ ኪሎውን በ80 ብር ሒሳብ እንደሚሸጥና የእያንዳንዱ የበግ ሥጋ ክብደትና ዋጋው መለጠፉ አገልግሎቱን ለየት እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

“ማንም ሰው የግድ የአንድ ሙሉ የበግ ሥጋ ግዛ አይባልም፡፡ ለምሳሌ አንድ በግ አሥር ኪሎ ቢሆን ዋጋው ደግሞ 800 ብር ይደርሳል፡፡ ስለሆነም ሁለት ሰዎች እያንዳንዳቸው አምስት፣ አምስት ኪሎ ሥጋ የመግዛት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ ሱቆቹ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፤” ሲሉ አቶ ኤፍሬም አስታውቀዋል፡፡

ቄራዎች ድርጅት ለፋሲካ በዓል ሦስት ሺሕ በግ አርዶ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን፣ የልኳንዳ ነጋዴዎች ደግሞ ሁለት ሺሕ ሠንጋዎችን፣ ደንበኞች ደግሞ አንድ ሺሕ በጎችን ለዕርድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለዕርድ የሚቀርበው ሰንጋ ቁጥር አነስተኛ ሊሆን የቻለው በዓሉን የሚያከብሩ ሰዎች በየቤታቸው በግና ዶሮ ስለሚያርዱና የበሬ ሥጋም በቅርጫ የማግኘት ዕድል ስለሚኖራቸው ነው፡፡ በፆም መያዥያ ወቅት ግን በሁለት ቀናት ውስጥ 7,800 የቁም እንስሳት መታረዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ኤፍሬም እንደሚሉት በየቀኑ እስከ አምስት ሺሕ በግና ፍየል በሕገወጥ መንገድ ይታረዳሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የታረዱ እንስሳት ሥጋ ደግሞ ጤና ላይ ችግር ያስከትላል፡፡ ከሚያስከትላቸው ችግሮች መካከል ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፈው አበሰንጋ የተባለ በሽታ ለከፋ ሞት መዳረጉ፣ በሴቶች ላይ የውርጃና የዕድሜ ልክ መካንነት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በቤት ውስጥ የሚታረዱ ዶሮዎችና በጎች እንዲሁም ቅርጫ ሕገወጥ ዕርድ ተብለው እንደሚፈረጁ ነገር ግን ከልማዳዊው ሁኔታ አንፃር እየታዩ እንደሚታለፉ ነው የተናገሩት፡፡ በሕገወጥ የታረዱ የእንስሳት ሥጋ በድርጅቱ በሚገኘው “ሬንደሪንግ ፕላንት” ተብሎ በሚጠራው ትልቅ የማስወገጃ ክፍል በከፍተኛ ደረጃ እንዲቃጠል ተደርጎ ይወገዳል፡፡source ETR

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 3, 2013 @ 11:01 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar