www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠበነመራ ዲንሣ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ በነመራ ዲንሣ

By   /   May 3, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ በነመራ ዲንሣ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 37 Second

 

 

ከ፩፯ አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ፪፪ አመታት የስርአቱን ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ  አፓርታይድ ስርአት ተቀይሮዋል።
ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት ፪፩ አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ።
ለመጥቀስ ያክል ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ የህወሐት ባላስልጣናት ትእዛዝ መለስን ጨምሮ በጋምቤላ፣በኦሮሞ፣በአማራ፣በኦጋዴን እና በደቡብ ህዝቦች ላይ አስከፊ የእስራት የግርፋት እና የጅምላ ግድያ ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ዜጎችን በሀገሪቱዋ በየትኛዉም አካባቢ የመኖር የሀገሪቱዋ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ የዘር ማፅዳት ወንጀል በህወሐት አምባገነን መሪዎች እየተፈፀመ ነዉ።
በ፩፱፰፫፣፰፬ ጋምቤላ፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፮ በኦሮምያ ጅማ፣ሰጠማ፣ሲጊሞ እና ጌራ የሚባሉ አካቢዎች፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፰ በአማራ ተወላጆች ላይ በበደኖ፣ወተር፣በአርሲ ባሌ፣በሐረር ጉርሱም አካባቢ፣ከ፩፱፱፱ እስከ ፪፲፻ በደግሐቡር፣በቀብሪደሐር እና በኦጋዴን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በመከላከያ ሠራዊት በጦር ሄሊኮፕተር በመታገዝ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል።ከወራትም በፊት በደቡብ ኦሞ እና በጋምቤላ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል። ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምና አሁንም እየተፈፀመ ባለበት ወቅት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ማንም ተከሶ ለፍርድ የቀረበ የለም ነር ግን ይሄን ሁሉ በደል እና ግፍ የተቃወሙና የፃፋ ንፁሀን ያገሪቱ ዜጎች ለአፈና፣ለስደትና ለእስር ተዳርገዋል።
በስደት ያሉትን ባልዘረዝርም ሀገር ዉስጥ ሆነው በሀገሪቷ ህገመንግስት ተጠቅመው ስርዐቱን ስለተቃወሙና ስለፃፋ ከእድሜ ልክ እስከ ረጅም አመት እስራት ተፈርዶባቸዉ በእስር ላይ ያሉና እስርቤትም ሆነው ይግባኝ በማለትም ሆነ ባለማለት በሀገሪቷ የመጨረሻዉ ጠቅላይ ህወሐት ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን ያበሰሩንን ጀግኖች ጠቅሳለሁ፣
ሌልሴ ወዳጆ፣ርዮት አለሙ፣እስክንድር ነጋ፣በቀለ ገርባ፣አንዱአለም አራጌ፣ዉብእሼት ታዬ፣የድምፃችን ይሰማ ኮሚቴዎች>>>ወዘተ ኮራንባችሁ ያላችሁበት ህይወት የኛ ሆኖ ቢያቃጥለንም።
በአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ላይ የይግባኝሽ ፍርድ ቤት ያፀናዉ ፍርድ ከመለስ ሞት በውሓላም ህወሐት ፍትህን የገደለ የአፓርታይድ ስርዐት መሆኑን አሳውቆናል።
ስለሆነም ከሰሜን ኮርያ በላይ የከፋው የህወህት ስርዐት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እየተደገሰለት ባለዉ የዉሸት ፖለቲካ ክስ እሱንም በይግባኝ ፍርድ ቤት ጭምር ከምናምን እድሜ እስር ጋር ቂሊንጦ ወይም ዝዋይ እስርቤት ማየታችን አይቀርም።
እናም የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቷ ፍትህ መቀበሩን አረጋግጦልናል።
ውድ አንባቢዎቼ ነገር ግን እኔም ተመስገን ደሳለኝ ነኝ እናንተስ?
ሀገራችንን እና ህዝቧን ከአፓርታይድ ስርዐት ዛሬዉኑ እንታደግ!!!
ህዝብ ያሸንፋል።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 3, 2013 @ 11:22 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar