www.maledatimes.com የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ “አትፓ” ጠየቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ “አትፓ” ጠየቀ

By   /   May 4, 2013  /   Comments Off on የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ “አትፓ” ጠየቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 54 Second

አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) በሃገር አቀፍ ፓርቲነት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ተመዝግቦ ሠርተፍኬት መውሰዱን ገልፆ፣ የሰለጠነ ፖለቲካ እንዲፈጠር በእስር የሚገኙ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው ጌታቸው ከሌሎች አመራሮች ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ፓርቲውን ለመመስረት ከነሐሴ 2003ዓ.ም ጀምሮ ሲጥሩ ቆይተው ጳጉሜ 2004 ዓ.ም መስራች ጉባኤውን በአዲስ አበባ እንዳካሄዱ አስታውሰዋል፡፡

ፓርቲው የካቲት 22 ቀን 2005 የእውቅና ሠርተፍኬት ማግኘቱን ጠቅሰው፤ “የገዥ ፓርቲ የኢህአዴግ አባል የሆነው ህወሓት 37ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ባከበረ ሰሞን የኛ ፓርቲ ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል፡፡ የአንዱ ፓርቲ ሲያረጅና ሲዳከም ሌላ የአዲስ ትውልድ ፓርቲ መፈጠሩ ተፈጥሯዊ የለውጥ ህግ ነው” ብለዋል – ፕሬዚዳንቱ፡፡ ፓርቲው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማዘመን እንደሚሠራና ለሀገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች ሁሉ ጣቱን በኢህአዴግ ላይ ከመቀሠር ይልቅ የጥላቻ ስሜትን አስወግዶ፣ የመከባበር ባህልን በማዳበር፣ አገሪቱ መጠላለፍ ከበዛበት የፖለቲካ አዙሪት እንድትገላገል እጥራለሁ ብሏል፡፡ የሰለጠነ ፖለቲካ እንዲፈጠር፣ በሽብር ተጠርጥረው የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ በቤኒሻንጉል እና በጋምቤላ እንዲሁም በቤንች ማጅ የደረሰው አይነት የዜጐች መፈናቀል እንዲቆም ጠይቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 4, 2013 @ 9:13 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar