www.maledatimes.com ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠመግለጫ ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!

By   /   May 7, 2013  /   Comments Off on ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 1 Second

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዚያት በሐገራችን የሚፈፀሙ የተለያዩ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችና ህገ ወጥ ድርጊቶች ኢንዲቆሙ ለመንግስት የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቢቆይም ከመንግስት የተሰጡት ምላሾች ግን ጥያቄዎቻችንን ማንቋሸሽና ማጣጣል ወይም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፓርቲያችን ጥያቄዎችን የሚያቀርበው መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ቢሆንም ችግሮቹ እስካሁንም ሳይፈቱ አንዳንዶቹም እየተባባሱ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ ከተነፈጋቸው መካከል፤

1ኛ. ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና
አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም መልስ ያልተገኘ በመሆኑ፤
2ኛ. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቅን ቢሆንም አሁንም ገና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ስም ዝርዝር በየማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ እያየን በመሆኑ፤
3ኛ. መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን
በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን የተገኘ መልስ ባለመኖሩ፤
4ኛ. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን
መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ በተደጋጋሚ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው በመቆየታቸው እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ አሁንም አጥብቀን የምንጠይቅ መሆኑ እና ሌሎችም፤

በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ግንቦት 17 ቀን 2005 á‹“.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 á‹“.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 á‹“.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከላይ ያነሳናቸውና ሌሎችም ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ሰማያዊ ፓርቲ ለመጠየቅ ወስኗል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. ም
አዲስ አበባ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 7, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 7, 2013 @ 7:31 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar