www.maledatimes.com ቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች ወደ ዝዋይ እየተወሰዱ ናቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች ወደ ዝዋይ እየተወሰዱ ናቸው

By   /   May 8, 2013  /   Comments Off on ቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች ወደ ዝዋይ እየተወሰዱ ናቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 3 Second

በሽብርተኝነት ተከሰው የተፈረደባቸው እና በይግባኝ ክርክር ላይ የሚገኙ የነበሩት ፖለቲከኞች ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እየተወሰዱ መሆኑን ቤተሠቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡የእስረኛ ቤተሠቦች እንደሚሉት “የጠየቁት የይግባኝ ክርክር ውሳኔ ሳያገኝ እና እንዲሁም ቤተሠቦቻቸው በሚገኙበት አካባቢ መታሠር ሲገባቸው እስረኞቹን ወደ ዝዋይ መዘዋወራቸው እጅግ አሣዝኗል፡፡ ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበሩት እና  ከፓርላማው በክብር ተሸኝተው በሀገሪቱ ውስጥ ሠርተው መኖር ባለመቻላቸው በስደት ወደ ሱዳን ከሄዱ በኋላ ታስረው የተመለሱት አቶ አንዱአለም አያሌው ከአንድነት ፖርቲን ወክለው ለፓርላማ የተወዳደሩት ሻምበል የሽዋስ ይሁንአለም
እና በሽብርተኝነት ተከሠው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ምትኩ ዳምጤን ጨምሮ  ከ100 በላይ እስረኞች ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ ተጓጉዘዋል፡፡ እስረኞቹ በሌሉበት የይግባኝ  
አቤቱታቸውን የተመለከተ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መሀል ዳኛ አቶ ዳኜ  መላኩ እስረኞቹ ያልቀረቡበትን ምክንያት ጠይቀው ወደ ዝዋይ በመሄዳቸው ምክንያት እንደሆነ ሲነገራቸው ክርክሩ ሳያልቅ እንዳይሄዱ ብለን ነበር ለምን ሄዱ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይሁን እንጅ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ አሣማኝ እና በቂ መልስ መስጠት አልቻሉም ፡፡ በቅርቡ ጋዜጠኛ  ውብሸት ታየ ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ እስር ቤት መዛወሩ ይታወቃል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 8, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 8, 2013 @ 12:13 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar