www.maledatimes.com መንግስት በህገ ወጥ እስር ቤቶችን ዜጎችን እያሰቃየ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መንግስት በህገ ወጥ እስር ቤቶችን ዜጎችን እያሰቃየ ነው

By   /   May 8, 2013  /   Comments Off on መንግስት በህገ ወጥ እስር ቤቶችን ዜጎችን እያሰቃየ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 7 Second

ህውሃት/ኢህአዴግ/ አገሪቱን በመሳሪያ ሀይል ተቆጣጥሮ ማስተዳደር ከጀመረ 22 ዓመት ያስቆጠረ ቢሆንም ዛሬም በህገ ወጥ እስር ቤቶች እየተገለገለ ስለሆነ እስር ቤቱን እንዲዘጋ አንዳንድ የአገሪቱ ዜጎች ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ ጥሪው የቀረበው ሰሞኑን የህውሀት መስራች እና በአሁን ጊዜ የአረና ፖርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ ልጅ በህገ ወጥ እስር ቤት እንደታሠረ ከተሠማ በኋላ ነው፡፡የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚሉት “ህውሃት” በጫካ በነበረበት ወቅት ባዶ 6 በሚል መጠሪያ በየቦታው እስር ቤቶችን አቋቁሞ ዓለም አቀፍ የእስረኛ አያያዝን በሚያሟላ መንገድ እስረኞችን ያስር ነበር፡፡ 

በየ እስር ቤቶች ቶርችና ግድያ ይፈፀም ነበር፡፡ መንግስት ከሆነም በኋላ ማሰቃየት የሚፈልጋቸውን ሰዎችና በቶርች  መረጃዎችን ለማግኘት ሲባል እነዚህን እስር ቤቶች ይጠቀማል ብለዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በማያያዝም “በቅርቡ የአቶ አስገዳ ልጅ የአባትህን ጹሑፍ በኢንተርኔት ታስረጫለህ በሚል ከተያዘ በኋላ ከህጋዊ እስር ቤት አውጥተው ባዶ 6 ወደሚባል ህገወጥ እስር ቤት መዛወሩን አባቱ ይፋ አድርገዋል፡፡ 

“መንግስት እንደመንግስት ኃላፊነት ሊሰማው ይገባዋል፡፡ ከህገወጥ ተግባር መታቀብ አለበት፡፡ ስለዚህ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ህገወጥ እስር ቤቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መዝጋት አለበት፡፡” ካሉ በኋላ የኢህአዴግ መንግስት ከዚህ ድርጅቱ እንዲቆጠብ ጥሪያችን አስተላልፉልን ሲሉ
ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 8, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 8, 2013 @ 12:16 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar