www.maledatimes.com በቡሌ ሆራ የሚትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ ቁጣን ቀሰቀሰ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በቡሌ ሆራ የሚትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ ቁጣን ቀሰቀሰ

By   /   May 8, 2013  /   Comments Off on በቡሌ ሆራ የሚትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ ቁጣን ቀሰቀሰ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 45 Second

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ/ ሀገረ ማርያም/ ከተማ የምትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ በአካባቢው ቁጣ መቀስቀሱን ታወቀ፡፡ የአካባቢው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት “የከተማው ከንቲባ ሀላፊነት በጎደለው እና በማን አለብኝነት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰው ቦታውን ለባለሀብት ለመሸጥ መወሰናቸው ለሀይማኖቱም ለህዝቡም ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ነው፡፡” ሲሉ አውግዘዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን የወሰዱትን አቋም ሲገልጹ የከተማው ከንቲባ በድፍረት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰን እንጨትና ቆርቆቆውን እንድናነሳ አዘዋል ፡፡
“እኛ የእግዚያብሄርን ቤት አናፈርስም ፡፡እሳቸው ከፈለጉበት በሚረፈልጉት ኃይል ሊያስፈርሱ ይችላሉ ፡፡ ለወረዳው አስተዳደር አመልክተን የወረዳው አስተዳዳሪ በስፍራው ተገኝተውተ ተመልክተውታል ፡፡ ቤተክርስቲያኑ እንዳይፈርስ የሚያስችለው ውሳኔ ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረተዋል ፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻ በሰጡት አስተያየት በዚሁ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አለ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን  ካለፈው መንግስት ጀምሮ በከተማው ማስተርፕላን መሰረት ፍቃድና ካርታ አለው ይሁን እንጂ እኚህ የከተማው ከንቲባ ቦታውንና ከቦታው ላይ ያለውን ባህርዛፍ አላስረክብም ብለው ችግር ፈጥረውብን እስካሁን ችግሩ ባልተታበት ሁኔታ እንደገና አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ቅድስት አርሴማ ማዘወራቸው ገርሞናል ብለዋል ከተማውን ከንቲባ አቶ ቡሌ ገመዳ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና በጽ/ቤታቸው ስልክ ለማግኘት ያደረግነው መከራ ለጊዜው አልተሳካም ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 8, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 8, 2013 @ 12:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar