www.maledatimes.com ኢትዬጵያዊመልኩንነብርዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር ከቶ ይቻለዋልን? (ትንቢተ ኤርምያስ13:23) ከምናሴ መስፍን – ኖርዌይ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዬጵያዊመልኩንነብርዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር ከቶ ይቻለዋልን? (ትንቢተ ኤርምያስ13:23) ከምናሴ መስፍን – ኖርዌይ

By   /   May 9, 2013  /   Comments Off on ኢትዬጵያዊመልኩንነብርዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር ከቶ ይቻለዋልን? (ትንቢተ ኤርምያስ13:23) ከምናሴ መስፍን – ኖርዌይ

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 29 Second

በዚች ባለንበት ፕላኔት ላይ የሰውልጅን አስተሳሰብ ወይም ህገ-ልቦና ከሚዳኙት ረቂቅ ክንውኖች መሀከል የስነ መለኮት ወይም የስነ ፅሁፍ ሀብቶችውስጥ
ታላቁመጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ) አቢዩ ነው። ታላቁመጽሀፍ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያኖችምንነት በቅጡይናገራል።
ምንም እንኩዋን በአገራችን የኢትዬጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ዘመቻ – ከውጭም ሆነ ከውስጥ እኩይ ጡት ነካሽ ልጆቾዋም የሚሰነዘሩ – ዘርፈ ብዙ
እርሳዋነትዋን የማጥፉት ዘመቻዎች እንደ ሕገ ቃል ሆኖ የሚመነዘሩ ቢበዙም እነርሱ እራሳቸው እንቅልፍ ያጣሉ እንጅ አምላክ ኪዳኑን ይጠብቃት ዘንድ
ኢትዮጵያ አንዳች አትሆንም።
አንዳንድ የታሪክ ጸሀፊዎችም ወይንም እግዚአብሄርን የማያውቁ ሃቁን በማዛባት እግዚአብሄር ከላይ የሠራትን ኪዳናዊት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ብዙ
ይዳክሩ እንጂ እሷ እንደሆን ህልውናዋ ከላይ ከሰማይ የታወጀ በዚህማንነቷ ታውቃ የኖረችና ወደፊትምየምትኖርሀገር ነች።
በርካታ የክርስትና ኃይማኖት አባቶች ስለኢትዮጵያ ማንነት በሚጽፏቸው ማጻህፍት ውስጥ ኢትዮጵያንና እርሷ ስትጋደልላቸው የኖረችውን መለኮታውያን
ይዞታዎቿን አፈራርሰው ለመደምሰስ፣ በግልጽና ወይም በስውር ታጥቀው የተነሱባትን ባላጋራዎቿን ደግሞ ስለሚጠብቃቸው እጅግ አስፈሪ ፍዳ
በማስጠንቀቅ በኃያሉ እግዚአብሄር ፊት ንስሃ ገብተውከእኩይ ዓላማቸውይመለሱ ዘንድመማጸኑ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በየዘመናቱ እጅግ መጠነ ሠፊ ጥቃቶች ተሰንዝረውባት በርካታ መከራዎችን አስተናግዳለች። ጥቃቱ የሕዝቡን ሕይወት ጭምር አጥፍቷል።
በሁሉም የመከራ ዘመናት ግን የእግዚአብሄር መለኮታዊ ጥበቃ ህያው ነው። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ዲያብሎስ የተጠቀማቸውን
የእስከዛሬውንሶስት እኩይ የታሪክ ክንውኖች እስኪ እንቃኝ።
የመጀመርያው ዮዲት ወይም ጉዲት በምትባል ኢትዮጵያዊት ንግሥት የተፈጸመ ነው። ይህችው ንግሥት በ 960 ዓም አክሱም ድረስ በመሄድ ደብረዳሞን
ጨምሮ በርካታ አብያተ ክርስትያናትን አውድማ፣ ቅርሶችን አቃጥላ ነዋሪውን በእሳት አቃጥላ ፈጅታለች። ዮዲት ኢትዮጵያዊውን የአክሱም ሥርወ
መንግስቱን ደምሣ በምትኩ የራስዋን አስተዳደር መሥርታለች ይባላል። አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች ጉዲት ከደቡቡ የኢትዮጵያ ክልል የመጣች ነች
ሲሉ አንዳንዶች ከአገው ሕዝብ የተገኘች ቤተ እስራኤላውያን ነች ይላሉ። ዮዲት ጉዲት ክርስትናንና ክርስትያኖችን እንዲሁም የአክሱም ስርዎ መንግስትን
ለማፍረስ ብትንቀሳቀስም ከርሷ በሁላ የተመሰረተው የዛግዌ ስረዎ መንግስት ግን በንጉሥበላሊበላ አማካኝነት ክርስትናን አንደገና በመቀበል በዓለም
አስደናቂ የሆነዉንየላሊበላውቅር አብያተ በተክርስትያንን በማነፅና በመገንባት ዳግምየኢትዮጵያንመፅሐፍ ቅዱሳዊ ዘላለማዊነት አረጋግጦልናል..
ሁለተኛው ትልቁ የእትዮጵያ መከራ የተንሰራፋው የነቢዩ መሃመድን ኢትዮጵያን እንዳትነኩ ትዕዛዝን ባለማክበር አህመድ ግራኝ የተባለ ጦረኛ ከምስራቅ
ኢትዮጵያ በመነሳት ክርስትና ኃይማኖትን ለማጥፋት ጦር ሰብቆ በተነሳበት ዎቅት ነበር። በ 1528 ዓም አህመድ ግራኝ በሸዋ፣ ጎንደር፤ ወሎና ትግራይ ይገኙ
የነበሩ አብያተ ክርስትያናትን በማቃጠል ክርስትያኑን ፈጅቶ መንግስቱን አቃወሰ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አጼ ልብነድንግል ከፍተኛ ተጋድሎ
እያደረጉ ሲዋጉ ብዙ ሕዝብ አለቀባቸው። አጼ ልብነድንግል የፖርቱጋሎቹን ርዳታ ቢጠይቁም እንኳን በአፋጣኝ ስላልደረሰላቸው ትግራይ ውስጥ
በሚገኘው ደብረዳሞ ገዳም ውስጥ ተሸሸገው እንዳሉ እዚያው ሕይወታቸው አለፈች። በ 1543 ዓም የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ አጼ ገላውዲዎስ ዙፋኑን
ከወረሰ በኋላ ውጊያውን በማፋፋም ግራኝን ጣና ሃይቅ አካባቢ ድባቅ በመምታት የሀገሪቱን ኅልውና ዳግም በማደስና ክርስትያኑን በማነጽ የወደሙትን
ቤተክርስትያናትን መገንባት ጀመሩ። በ 1559 አጼ ገላውዲዮስ ሃረር ላይ ዘምተው በጦርነቱ ላይ ሞቱ። በዚሁ የመከራ ዘመን በርካታ ነዋሪዎች የትውልድ
አካባቢያቸውን በመልቀቅና በመሰደድመቶ ዓመታት ያህል ለሰነበተውየኃይማኖትና የመስፋፋቱጦርነት ሰላባ ሆነዋል።
የጉልታዊው ጭቆና ሥርዓት ምሬት የወለደው የ1966 ዓም የሕዝብ አብዮት እግዚአብሄር አልባ በሆኑ ወታደራዊ ኮሙኒስቶች ሥር ወድቆ ሀገሪቱን ፍዳ
ሲያበላ ቆይቶ አስራ ሰባተኛ ዓመቱ ላይ ራሱን አጠፋ። ክርስትያኖቹና እስላሞቹ ባሳዩት የማይበገር ጽናት ይህ የክህደት ዘመን ተገርስሶ ነገር ግን ወታደራዊ
መኮንኖቹን የተኩት ወያኔዎች ይበልጡኑ እግዚአብሄር አልባ ሆነው ከዮዲት ጉዲትና ግራኝ መሀመድ ባልተናነሰ ሀገሪቱን ለማጥፋት በዘር ክልል ሸንሽነው
ለለሶስተኛ ጊዜ ታሪክ የመዘገበውየሕዝብ መከራ እንደገና እውን ሆነ። ወያኔ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ፈጽሞ የሌለና የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት አረንጓዴ፣
ቢጫና ቀይ በድል ጊዜዓት የተውለበለበችዋ ባንዲራዋን ሚስጥር ሳይቀር በማጉደፍ ጠላትዎቿን ጭምር አስደስቷል። በእርግጥ በመጀመርያ በዮዲት
ጉዲት ኋላ በግራኝ መሀመድ ያልጠፋች ሀገር በወያኔዎቹ ግፍና ሰቆቃ ልትጠፋ ባትችልም እንኳን ለጊዜውም ቢሆን የሕዝቡ አንድነትና ፍቅር እጅግ ፈተና
ውስጥ ወድቋል። ኢትዮጵያ ወደቧ ተወስዷል። መሬቷ ላባዕዳን ቱጃሮች እየተቸረቸረ ሕዝቡ ቀዬውን እንዲለቅ ተፈርዶበታል። በዚሁ የሶስተኛው የጥፋት
ዘመን ሃገሪቱን በደማቸው ዋጅተው ድንበሯን አስከብረው ነጻነቷን ያደመቁት አማሮች ልጆቻቸውና የልጅ ልጅ ልጆቻቸው በጠላት ተፈርጀው ሕጻናት፣
ወጣት፣ ሽማግሌ፣ አሮጊት ሳይቀር በበደኖና አርባጉጉ ጥልቅ ገደሎች ተወርውረዋል። ግፉ ቀጥሎ ከደቡብ ኢትዮጵያ ጉራ ፈርዳ ዞን እጅግ በርካታ አማራ
አርሶ አደሮች እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። ይህ የአማራውን ዘር ነጥሎ የማጥፋቱ የወያኔው
እኩይ ዓላማነገ ወደ ተቀሩት አካባቢዎች ላለመደገሙአንዳች ዋስትና የለም።
ኢትዮጵያውያ ማናቸውንም ስቃይና ግፍ በትእግስት ተቋቁማ እግዚአብሄርን በሕይወታቸው በሚያንጸባርቁት ልጆቿ በመታገዝ ዳግም ከፍ ትላለች።
በእርግጥ በዚህ ግለኝነት በተንሰራፋበት፣ ስደት እንደ ኑሮ አማራጭ በተቆጠረበት፣ የወገኑ ስቃይ ያልተሰማው ቤተ ሠሪው በዝቶ ሠርግና ምላሹ ቅጡን
ሲያጣ ብዙዎች ከትግል ቢዘናጉም ረቂቁ የእግዚአብሄር ሃይልና የጥቂቶቹ የእግዚአብሄር ሰዎች ልባዊ ጸሎት ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ጠብቆ እንደ ብረት
ያጸናታል።
የዮዲት ጉዲት ፍጅት፣ የግራኝ መሀመድ ወረራና የወያኔው የዘር ማጥፋቱ ግፍ ሶስቱም ሰቆቃዎች የተፈጸሙት በናት ጡት ነካሽ ልጆችዋ ነው። ነብር
ዥንጉርጉርነቱን መለወጥ የሚችል ኃይል እንደሌለ ሁሉ ኢትዮጵያዊውን መልኩን የሚለውጥ፣ እምነቱን የሚያዛንፍ፣ ቅን አመለካከቱን የሚያሻክር፣
ትዕግስቱን የሚያሸንፍ ስነመንግስታዊ ፈሊጦቻቸውን ማጽናት ግን አልቻሉም። በእርግጥ ከባዕዳኑ ወረራ ይልቅ ኢትዮጵያን እጅግ የሚያቆስሏት የቀን
ጅቦቹ፣ ከሃዲዎቹና ሆዳሞቹ ለጊዜውፈተናዋንያበዙታል።
ወያኔና አሳዳጊው ሻእቢያ ይህን ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በድፍረት የፈጸሙት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ቢሆንም እኛ ማጎብደዱን ትተን ግፉን
መቀበል ስናቆምእግዚአብሄር ዓላማቸውከስር ጀምሮ ይንዳል።
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ይሁን
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች – (መዝሙር 68:31)
ጸሃፊውን በዚህ አድራሻማግኘት ትችላላችሁ almazmina@yahoo.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 9, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 9, 2013 @ 7:40 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar