www.maledatimes.com “አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል” (ደረጀ ሃብተወልድ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል” (ደረጀ ሃብተወልድ)

By   /   May 10, 2013  /   Comments Off on “አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል” (ደረጀ ሃብተወልድ)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 25 Second

የኢህአዴግ ታማኝ ተሿሚ የሆኑት የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በዘር ላይ ያነጣጠረ አደገኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የሚያሳይ ቪዲዮ ኢሳት እጅ ገብቷል። በአንድ ከፍተኛ የኢህዴግ ተሿሚ ደረጃ እንዲህ ያለ አሳፋሪ፣ ዘግናኝና ዘረኛ የሆነ ቅስቀሳ በአደባባይ ሲታወጅ መሰማቱ፤ ገዥዎቻችን ይህችን አገር መውጫ ወደሌለው አረንቋ እየከተቷት እንደሆነ የሚያስረዳ ነው።
ባለስልጣኑ ተራ ግለሰብ እስካልሆኑ ድረስ እና ንግግሩንም ያደረጉት መንግስታዊ ሥራቸውን እያከናወኑ ባለበት ወቅት እንደመሆኑ መጠን፦”ይሄ የባለስልጣኑ ግላዊ እንጅ- መንግስታዊ አቋም አይደለም” ሊባል አይችልም። ” …ባለስልጣኑ ከመስመር ወጥተው ያደረጉት ነው” ከተባለ ደግሞ መንግስት በክልሉ ፕሬዚዳንትና፤ የተናገሩትን ነገር “ነግረውኛል” ባሏቸው ሌሎች ሹማምንት ላይ ማጣራት አድርጎ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል።ይህ ካልሆነ….
ሌላው ሌላውን ትተን በአጭሩ ለማሳየት ያህል”.. የኦጋዴን ህዝብ ከትግሬ ጎን እንዲቆም፣ አማራና ትግሬን፣ አማራና ኦሮሞን አንድ አድርጎ መጥራቱን እንዲያቆም….”ነው ያሉት- ፕሬዚዳንቱ። ይህ በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ሁሉ ላይ(በትግራይ ተወላጆች ላይ ጭምር ) የተቃጣ ወንጀል ነው። ይህን ያልኩት ፕሬዚዳንቱ አማራው ወይም ኦሮሞው ወይም ጉራጌው ወዘተ ላይ ያነጣጠረ ቅስቀሳ ስላደረጉ አይደለም- “… የኦጋዴ ህዝብ ከአማራው ወይም ከኦሮሞው… ጎን እንዲቆም…”ቢሉ ኖሮም፤ ይሰማኝ የነበረውም ስሜት ይኸው ነው። ዘረኝነት የትም ቦታና በማንኛውም አካል ሲፈጸም ፤ያው ዘረኝነት ነው። በከፍተኛ ሹማምንት ደረጃ ሲናፈስ ደግሞ አገራዊ ጥፋቱ የከፋ ይሆናል።በመሆኑም ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት፣አብሮ የመኖር እሴታችንን እና የዘመናት ፍቅራችንን ለመናድ ሌት ተቀን እየባዘኑ ያሉትን ሁሉ በጽናት እንቃወማቸዋለን! እንታገላቸዋለን!!!
ዘረኝነት፣ጎሰኝነትና ክልላዊነት ከሰውነት ያነሱ ናቸው። ሌላው ቀርቶ ብሔራዊነት( ኢት ዮጵያዊነት) እንኳ ሰውነትን አያህልም።ሰውነት ዐለማቀፋዊ (Univesal)ነው።ዘር አይቆ ጥርም፤ቀለም አይለይም።ሰው እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 10, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 10, 2013 @ 7:57 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar