www.maledatimes.com የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By   /   May 11, 2013  /   Comments Off on የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 39 Second

የፌዴራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን እንዲሁም፣ምክትል ዳይሬክተሩን አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ።

የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኮሚሽኑ እንዳለው በግለሰቦቹ ላይ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ተሰባስበዋል። ጉዳዩ ለፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድረስም ተጠርጣሪዎቹን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል።

የፌዴራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በህዝብና በመንግስት ንብረት ላይ የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን ተከታትሎ አስፈላጊውን መረጃ ካሰባሰበ በኋላ በህግ ፊት አቅርቦ በማስጠየቅ ሙስናን የመከላከልና የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው አካል ሲሆን ፥ ከዚሁ መሰረታዊ ግንዛቤና ቁርጠኝነት በመነሳትም ኮሚሽኑ ከተለያዩ መንግስታዊ አካላትና ከመላው የሃገራችን ህዝብ ጋር በመደጋገፍ በተጠርጠሪዎች ላይ ህጋዊ ስርዓትን ተከትሎ ምርመራ ያካሂዳል።

በዚህም መሰረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለያዩ ባለ ጉዳዮችና ከንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም፣ከልዩ ልዩ መንግስታዊና ህዝባዊ አካላት ጥቆማዎችን ሲቀበል ቆይቷል።ጥቆማዎቹ በአንዳንድ የገቢዎችና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ፥በግል ንግድ በተሰማሩ ህገ ወጥ አካሄድን በሚያዘወትሩ ግለሰቦች ላይ  ያተኮሩ ነበሩ።

ኮሚሽኑ ከህዝቡ  የተቀበላቸውን እነዚህን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግም ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል።በጥናቱም በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ሰብስቧል።

ኮሚሽኑ እንዳለው ጉዳዩ ለፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድረስ ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር እንዲቆዩ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ከፍርድ ቤት ህጋዊ የብርበራና የእስር ትዕዛዝ በማውጣት፣የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን እንዲሁም፣ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ያህል ተጠርጣሪዎች ናቸው፥በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገው።

ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣን መነሻ በማድረግ ተጨማሪ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ ተጠርጠሪዎቹን ከተሟላ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ጋር ለመደበኛው ፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ወደፊትም በጉደዩ ላይ እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

በዚህ አጋጣሚም መላው የሃገራችን ህዝብ መንግስት ሙስናን ለመዋጋት ለሚያደርገው ጥረት የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል ጠይቋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 11, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 11, 2013 @ 2:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar