www.maledatimes.com ይታየኛል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ይታየኛል

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ይታየኛል

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 30 Second

ከይኸነው አንተሁነኝ
ይታየኛል …..
አወ ያታየኛል ግሩም ሂዎት…
የነጻነት እጦት ርሃብ ከአእምሮሯችን ሲኮበልል
ምስቅልቅል ሂዎታችን ስቃያችን ጥርግ ሲል
ወጥቶ መግባት ሰርቶ መብላት እውን ሲሆን ጠፍቶ ክልክል
እኛው ለኛ ተነጋግረን እኛው በኛ የሰራነው
አለቃችን ህግ ሲሆን እኛው ለኛ ያጸደቅነው።
ይታየኛል ከእኩይ መለስ ከወያኔ ህልፈት ማግስት
በእኩልነት ጥላ ድባብ በኢትዮጵያ ምኩራብ ደጃፍ
የንጋት ጎህ ፍንትው ብሎ ተስፋ ሞልቶን ስንከትት
በብሄር በሃይማኖት መለያየት ተረት ሆኖ
ባንዲራችን አስተቃቅፎን አያይዞን አስተማምኖ
ያገራችን ኢትዮጵያ የሷ ብቻ ሰሟ ገኖ
ይታየኛል በሀገሬ ፍቅርና ሰላም ሰፍኖ።
የጠባቡ መለሰ ህልም ሀገር ሊያፈርስ የወጠነው
ኢትዮጵያን ለመበተን ከዳር እዳር የዘረጋው
የወያኔ መርዛማ ቦምብ በኛ መሃል የነበረው
በፍቅር ቅብአቅዱስ ሲበታተን ፈውስ አግኝቶ
በኛ አንድነት በኛ ትግል ሲንኮታኮት አቅሙ ሟሙቶ፤
ይታየኛል ከመለስ ሞት ቀብር በሗላ
ወያኔ ሲንገጫገጭ የኛ አንድነት ግን ሲጎላ፤
ይታየኛል ብሩህ ሰማይ መልካም ሀገር
መልካም ሂዎት መልካም አየር
ሰላሟ የሚያስቀና ጥንካሬዋ የሚያስገብር
ኢትዮጵያዬ ነፃ ሆና እኛ ልጆቿ ስንከብር……አወ ይታየኛል…

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2012 @ 3:55 am
  • Filed Under: POEMS
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar