www.maledatimes.com ውሸት ቢጋነን እውነት አይሆንምና ዛሬ እውነቱ አደባባይ ላይ ሲቀርብ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ውሸት ቢጋነን እውነት አይሆንምና ዛሬ እውነቱ አደባባይ ላይ ሲቀርብ

By   /   May 12, 2013  /   Comments Off on ውሸት ቢጋነን እውነት አይሆንምና ዛሬ እውነቱ አደባባይ ላይ ሲቀርብ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 26 Second

በኢሳ አብድሰመድ Issa Abdusemed

ወያኔ ኢህአዴግ ዴሞክራሲንና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ይዞ ይመጣል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ለአገዛዙ የማይመቹትን ገድሏል ወይም አስገድሏል፤ ብዙዎቹን አገር ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል፡ ይህ የማይካድ ሀቅ ነው….  እንደማንኛውም አምባገነን ገዥ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችንም አካሂዷል፡፡ አሁንም በማካሄድ ላይ ይገኛል በአሁን ወቅት የአገሪቱ መንግሥት የንግድ ሥርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ዕድገትና በድህነት ቅነሳ ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝና በመንገድ ግንባታ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም የባቡር መስመር ትስስር ለማሳደግ ጥረት በማድረግ  ላይ  መሆኑን የሚያስረዳን የወያኔ መንግስት እራሱ በሾማቸው የጉሙሩክ ባለ ስልጣናት የኢትዮዽያን ሀብት እና ንብረት ሲዘርፉ ያስኴቸው በማለት ቱልቱላውን እየነፋልን ነው

ሲጀመር  ወያኔ ከሙስና እና ከዘረፋ መቼ ፀዳና ነው በሃገራችን ነጻነት፣ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የምንሻ ወገኖች ሁሉ ሌሎች የሚሰሩትን ከመተቸታችን በፊት እኔ ምን ሰርቻለሁ ማለት አስፈላጊ ጥያቄ ነው?

የምነቅፋቸው ምን ሰርተው ምን ተሳሳቱ ስህተት ካለ በምን መንገድ በገንቢ ሁኔታ ማረም ይቻላል የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን በማንሳት መመርመር ያስፈልገናል በወያኔ ስርአት ውስጥ ከቀበሌው ሊቅመንበር እስከ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ድረስ  አንዳችም ህዝብን ለማገልገል የሚታገል የወያኔ አባል የለም በመጀመርያ ደረጃ የወያኔ አባል ስትሆን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚለው አባባል ማመን ይኖርብሃል ይህንን አባባል ካልተቀበልክ ኣንተ ፅንፈኛና አሸባሪ ከሚባሉት የተለየህ አይደለህም

ወያኔኢህአዴግ በዚህ አገር ከአሁን በፊት ያልታዬ ወደፊትም ሊታይ የማይችል ግዙፍ የሙስና ሰራዊት ገንብቷል፡፡ የሙስና ሰራዊት አሁን አገሩንና ህዝቡን ረስቷል፡ ራሱን ከምንጊዜውም በበለጠ ከህብረተሰቡ አርቆ፣ ለህብረተሰቡ ምንም አይነት የልማት አስተዋጽኦ ሳያደርግ ህዝቡ ያመረተውን እና በህዝቡ ስም በእርዳታ የተገኘውን ሁሉ በመዝረፍ ላይ ይገኛል፡፡ ይህች አገር ነገ ከአንዳች  ከችግር ሊያወጣት የሚችል የልማት መሰረት የላትም

እኝህ ዛሬ ወያኔ በሙስና ሲጨማለቁ ያስኴቸው የሚላቸውውን አቶ መላኩ ፋንታ በአንድ ወቅት ያገር ውስጥ አልበቃ ብሎአቸው በውጪው አለም ለሚገኙት  ኢትዮዽያውያን  ፓልቶክ በሚባል የወያኔ ማከማቻ በሆድ አደሩ ኣባ መላ ጋባዥነት አገራችንን እናልማ አገራችን በፈጣን ሁኔታ በማደግ ላይ ካሉ ኣገሮች ጋር ተሰልፋ ትገኛለች ልማታችን ፈጣን ነው በማለት ይደሰኩሩ ነበር ውሸትን በሕዝብ ውስጥ ለመከተብ የሚደረገው ጥረት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን ያስገነዝበናል ሊንኩን ተጭነው  ቅጂውን ያዳምጡ

http://goo.gl/ag9P8

417889_298991513567102_1739676750_n[1]

መጨረሻው ይሄ ሆኖ ሳለ አሁንም ድረስ የህዝብን አሸናፊነት ባለመረዳት ህዝብን እናሸንፋለን በማለት ህዝቡን ራሱንና የህዝቡን ሃብት የሚጨርሱ ጨቋኝ አምባገነኖች አሉ፡፡ የማይሸነፈውን እናሸንፍ በማለት የሚችሉትን ያክል የህዝቡን ህይወትና ሃብት ጨርሰው በቅርብ ጊዜ ራሳቸው ያበቃላቸውን አምባገነን ገዥዎችን እናስታውሳለን የቱኒዚያ፣ የግብፅና የሊቢያ አምባገነኖች ከማይሸነፈው ህዝብ ጋር በከንቱ ታግለው ተሸንፈዋል የወያኔም መጨረሻ ከነዚህ የተለየ አይሆንም በተጨማሪ ወያኔ አቶ መላኩ ፋንታን ምንያህል ታማኝ ሰራተኛ አድርጎ ይመለከት እንደነበር ከ http://sodere.com/profiles/blogs/ethiopia-melaku-fanta-director-general-of-the-ethiopian-revenues-  ላይ የተወሰድውን ያንብቡት

ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑርልን

 
Ethiopia: Melaku Fanta, Director General of the Ethiopian Revenues and Customs Authority, Detained on Corruption charges

Daniel Birhane  Ethiopian police detained twelve individuals today, according to the press statement from the Federal Anti-Corruption Commission. Melaku Fanta, Director General of the Ethiopian Revenues and Customs Authority with the rank of a Minister is among the detainee. His deputy, Gebrewahed Woldegiorgis is also put in custody. The identity of the rest ten detainees was not disclosed. Though it appears none are in the top leadership. Melaku Fanta was elected to the out-going Council of Addis Ababa city Administration in 2008 as a candidate of ANDM/EPRDF. Melaku Fenta has BSc in Economics and MBA as well as Diploma in Public Management and Urban Governance. He was studying MA in Customs and Revenue in 2010. Previously, he served in the Ministry of Labour and Social Affairs, then in the Regional Affairs Department of the Prime Minister Office at different levels and also at the then Ministry of Revenue. As of 2008, he is in charge of the Revenues and Customs Authority – which replaced the Ministry of Revenue. He is also one of the 180 EPRDF Council members. Melaku will be the second Cabinet member to be sacked since the passing of former Prime Minister Meles Zenawi last August. It is to be recalled Prime Minister Hailemariam Desalegne recently called the public to provide him tips on corrupted officials.

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 12, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 12, 2013 @ 6:11 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar