www.maledatimes.com በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ቤት የንብረትና የሰነድ ማስረጃዎች ተገኙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ቤት የንብረትና የሰነድ ማስረጃዎች ተገኙ

By   /   May 12, 2013  /   Comments Off on በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ቤት የንብረትና የሰነድ ማስረጃዎች ተገኙ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 38 Second

nበሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከትናንት በስትያ በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተገኘ።

ከገንዘብ በተጨማሪ በርካታ የቤት ካርታዎች፣የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና ሌሎችም ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ተገኝተዋል።
የፌዴራል ፖሊስ  የፍርድ ቤት ማዘዣ በማውጣት ታዛቢዎችና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸው በተገኙበት ነው በትናንትናው እለት በግለሰቦቹ ቤትና መስሪያ ቤት ብርበራ ያካሄደው።
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ በሆኑት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት በተደረገው ብርበራ ስምንት ላፕቶፖችን ጨምሮ 200 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ፣26 ሺህ 300 የአሜሪካን ዶላር፣19 ሺህ 435 ዩሮ ፣560 ፓውንድና 210 የታይላንድ ገንዘብ  ተገኝቷል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲና ለገጣፎ የሚገኙ የቦታ ካርታና ፕላን እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፤
የፌዴራል ፖሊስ እንዳለው የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ በነበሩት ሌላኛው ተጠርጣሪ አቶ አስመላሽ ወልደማርያም ቤትም እንዲሁ ወደ 2 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ  በጥሬው ተገኝቷል።
አቶ አስመላሽ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ውስጥ የጉምሩክ ስነ ስርዓት አፈጻጸም የስራ ሂደት፣የኤርፖርት የኤርጉምሩክ የድህረ ክሊራንስ ኦዲት የስራ ሂደትና የኤርፖርት ጉምሩክ ስነ ስርዓት ቡድን መሪ በመሆን ጭምር ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹን ለህግ ለማቅረብ ከፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመሆን የተካሄደው ጥምር ዘመቻ በእቅድ የተመራ፣ህጋዊ ስርዓትን መሰረት ያደረገና የተሳካ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በሂደቱም ከወንጀሉ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ነው በፌዴራል ፖሊስ የፋይናንስ ነክ ወንጀሎች ቡድን መሪ ኢንስፔክተር በለጠ ባለሚ የተናገሩት።
በቀጣይም ፖሊስ በምርመራ ሂደቱ የደረሰበትን መረጃ ለህዝብ እንደሚያሳውቅና ህብረተሰቡም ህግን ለማስከበርና ሙስናን ለመዋጋት መንግስት በሚያደርገው ጥረት ተሳትፎውን እንዲያጠናክር የፌዴራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 12, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 12, 2013 @ 10:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar