www.maledatimes.com ታየኝ ተሰባብሮ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ታየኝ ተሰባብሮ

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ታየኝ ተሰባብሮ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 38 Second

By Yehenew Antehunegn

እርስ በርስ ተቃቅፎ ተቆላልፎ ያለው
ጋኑን አስተካክሎ ቀጥ አርጎ የያዘው
ከቀኝና ግራ ከታች የደገፈው
የዘመን አብሮነት ባህል ያያያዘው
ምን እባል ይሉኝታ ገርቶ ዝም ያረገው
አቅም አጥቶ ሰልችቶት ግራ ገብቶት ያለው
ቢታገስ ቢጠብቅ የጋኑ አለመሙላት ፍጹም መመቻቸት
የመከራ ጭነት ከመጨመር በቀር ለሱ እሚያስብ ማጣት
ሁሌ ከስር ሆኖ መሸከም ማትረፉ
አሳስቦት ክብደቱ አጀግኖት ግፉ
“ለኛ አላተረፍንም አይነው መዘነው
ሸክም በቃ እንግዲህ አቅማችንን በላው”
ብሎ ሸርተት ቢል ፍቺ ፈላጊ ህዝብ የሚያደርገው ያጣ
ሁሉም በያቅጣጫው ከሸክሙ ቢወጣ
ታየኝ አወዳደቅ የጋኑ እጣ ፈንታ
ተሰብሮ ወላልቆ ሲበተን ሽህ ቦታ
ደግሞ ላይገጠም በየቦታው ነኩቶ
ታየኝ ተሰባበሮ ለጋኑም ቀን ሞቶ

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2012 @ 3:53 am
  • Filed Under: POEMS
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar