www.maledatimes.com ወያኔዎች መቷቸው አጠቋቸው-ግን ለምን ትላንት? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወያኔዎች መቷቸው አጠቋቸው-ግን ለምን ትላንት?

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ወያኔዎች መቷቸው አጠቋቸው-ግን ለምን ትላንት?

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 36 Second

ወያኔዎች መቷቸው አጠቋቸው-ግን ለምን ትላንት?
ከይኸነው አንተሁነኝ

ሙስሊሙ ወገናችን ያነሳቸውን እምነትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ቢቻል ህገመንግስቱን በማክበር እና የእምነት ነጻነታቸውን በመጠበቅ እራሳቸው እንዲፈቱና በአግባቡ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ከመንግስት ይሚጠበቅ ነበር። ይህም ካልሆነ ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሄ ለማፈላለግ የሰፊውን ሙስሊም ማህብረሰብ ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ የሚደረግ የመንግስት ገንቢ እገዛ አሌ የሚባል አልነበረም። ከ 99% በላይ የህዝብ ድምጽ አግኝቼ ተመረጥኩ እያለ የሚያጭበረብረው የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ግን ከሀገሪቱ ህዝብ ከ30% በላይ የሚሆነውን የሚወክለው የሙስሊሙ ህብረተስብ ያነሳቸውን እምነቱን የተመለከቱ ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ላለፉት ሰባት ወራት ሲያቅማማ ከቆየ በሗላ እንሆ በትላንትናው እለት በጥይት፣ በቆመጥና በጭስ ህዝባችንን በማሰቃየት ወያኔያዊ መልስ ሲመልስ ማምሸቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ግን ለምን ትላንት?
በትላንትናው እለት ዓለም በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ቁርጠኛ የሀገር ልጆችና እውነትን በመናገርና በመጻፍ ወያኔንና ጠባቡን መለስ ዜናዊን እራቁቱን ሲየስቀሩት የነበሩት የነፃነት ታጋዮች የነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ እና ሌሎችም በሃገር ውስጥ፤ እንዲሁም በውጭው ዓለም የዘረኛው መለስ ዜናዊንና ወያኔዎችን በመከታተልና በማጋለጥ የእግር እሳት የሆኑባቸው ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮችና አባላት የመጨረሻ የፍርድ ሂደት በአዲስ አበባ ከተማ በካንጋሮው ፍርድ ቤት በይስሙላ ዳኞቹ የሚሰማበት እለት ነበር። ታዲያ ይሄን ምን አገናኘው ትሉ ይሆን? ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያን እየመራሁ ነው የሚለውን የትግራዩን ጉጅሌ ቡድን በማስተዋል ለተመለከተ ግንኙነቱ አጭር ነው።
በአዲስ አበባና በሌሎችም የክልል ከተሞችና በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ሳይቀር ጠንካራ ሰራተኞች፣ ለእውነት ተከራካሪዎች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ገበሬዎች ሳይቀሩ ከአካባቢያቸውና ከይዞታ መሬታቸው፣ ቤታቸውና የንግድ ሃብታቸው በልማት ሽፋን በእድገት ሽፋን ሲፈናቀሉ እንደኖሩ ለሁሉም ግልጽ ነው ብየ አምናለሁ። ወያኔ በግልፅና ፊትለፊት የፈፀማቸው ሰቆቃዎች በቁጥር ጥቂት ይመስሉኛል በስውር ግን የሀገራችነንን ህዝብ አማሯል፣ አስሯል፣ ገርፏል፣ ገድሏል አሰድዷል። ሁሉም ግን ሌላ የሽፋን ታሪክ ነበራቸው።
ከዚህ በፊት ተዛማች የዶሮ በሽታ (የወፍ ጉንፋን) ግብቷል በሚል ሽፋን ያንድን ጠንካራ ተቃዋሚ ግለሰብ የግል ንብረት የነበረ የደሮ እርባታ ሙሉ በሙሉ እንዲቃጠል በማድረግ ግለሰቡ ላይ የኢኮኖሚ ኪሳራ ካደረሰ በሗላ ወዲያው እራሱ በሚቆጣጠረው ሚዲያ የተባለው በሽታ የለም ማለቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። በአዲስ አበባና በሌሎችም የክልል ከተሞች ተቃዋሚዎችን፣ ጠናካራ ተናጋሪዎችንና የህዝብ ወገንተኝነታቸው የተረጋገጠባቸውን ግለሰቦች መሰረት ያደረገ መንገድ፣ የልማት ቦታ እና የኢንቨስትመንት ፕላን በማውጣትና ግለሰቦቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከይዞታቸው እንዲፈናቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል። በመንግስት መስሪያ ቤቶች የነበሩትን ጠንካራ ኢትዮጵያዊያንንም ለመምታት እንደ ቢ-ፒ-አር እና ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም አሁን በቅርቡ ደግሞ ሁሉንም ነፃ ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትን፣ መሪዎችንና ደጋፊዎችን እንዲሁም ተሰሚ የማህበረሰቡ አባላትን በአሸባሪነት ሽፋን በመክሰስና በማስቀጣት ላይ ይገኛል።
የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝም ሆነ ወያኔዎች የእርዳት ገንዘብ በገፍ የሚያፈስላቸውን እንጅ እየመራነው ነው የሚሉትን ምስኪኑን የኢትዮጵያን ህዝብ አይፈሩም። ስለሆነም ለሚፈሯቸው ምእራባዊያን የሚሆን የሽፋን ስእል ይስላሉ ወይም የሽፋን ታሪክ ይተርካሉ፤ ይህም ካልሆነ ደግሞ ትላንት በሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እንዳደረጉት ግዳያቸውን ከሌላ “ዓለም በትልቁ ከሚጠብቀው” ታሪክ ጀርባ ይጥላሉ። ስለሆነም ይመለከተናል የሚሉ ተቋማትም ሆኑ መንግስታት የሚጠይቁትም ሆነ የሚጮሁት በትልቁ ስለሚጠብቁት ኩነት እንጅ ከሱ ጀርባ ስለተከናወነ ክስተት አይሆንም ስለሆነም ዘረኛው መለስ ዜናዊ የበቀል ጥሙን በዚህ መልኩ ህዝቤ በሚለው ላይ ይወጣል።
በዚህም ምክንያት ነበር ሰባት ወር ሙሉ ሲሳብ፣ ሲወጠርና ሲላላ የከረመው የሙስሊም ወገኖቻችን ህገመንግስታዊ ጥያቄ በትላንትናው እለት በህገ አራዊት ፍርድ አይሆኑ ሁኖ ብልሽትሽቱ ሲወጣ፣ ወንድ ከሴቱ ወጣት ከሽማልሌ በጥይት፣ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭሰ ስሰቃይና አይሆኑ ሲሆን፤ ዓለም የጮኸው ግን በተመሳሳይ ቀን ከስምንት ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት በተፈረደባቸው ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጉዳይ ላይ ነበር። ለሙስሊም ወገኖቻችን ዓለም ምንም አላለም ማናልባት ወደፊት…አላውቅም። ሙስሊም ወገኖቻችንም በአሁኑ ሰአት እያለቀሱ ይወድቃሉ ስለነፃነት እየጮሁ ይሞታሉ። ስለሆነም እንደዚህ ላሉ በሽፋን ለሚከወኑ ግድያና ሰቆቃዎች ዓለም እስኪያውቅና አብሮ እስኪጮህ ብሎም የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪ የሆነው ጎጠኛው መለስ ዜናዊና ወያኔዎች እስኪወገዱ አቅማችን እንደፈቀደ ለሚመለከተው ሁሉ ማሰማት፣ ማሳወቅና ማስተጋባት ወገን ነኝ ከሚል ዜጋ ይጠበቃል እላለሁ። አበቃሁ።

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar