www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ሕዝብና እና 666 የሰው ቁጥር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ሕዝብና እና 666 የሰው ቁጥር

By   /   May 21, 2013  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ሕዝብና እና 666 የሰው ቁጥር

    Print       Email
0 0
Read Time:125 Minute, 22 Second

ይህን መልዕክት ለመጻፍ ያስፈለገበት ምክንያት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ለመስጠት ሳይሆን የችግራችን ምንጭና
አሳሳቢነቱን በሃይማኖተኞች ዘንድ የተሰወረውን፣ ፖለቲከኝችም ያልተረዱትን፣ የምጣኔ ሃብት ጠበብተኞችም ሊደርሱበት ያልቻሉትን፣
እግዚአብሔርን ለሚፈሩና እንደ ሐሳቡም ለሚኖሩ ሰዎች የገለጠውን የሰይጣን ምድራዊ 666 አሠራር ሚስጢር ዜጋው ሕዝብ አውቆት ሊመጣ
ካለው አስከፊ እልቂት ራሱን፣ ቤተሰቡን ብሎም ወገኑን ያድን ዘንድ ለማሳሰብም ሆነ ለመምከርም ነው፡፡ የአንባቢ ድርሻም ይህን ወረቀት
ባመቸህ መንገድ ለወገን ማስተላለፍ የሚጠበቅበት ሲሆን አያገባኝም ማለትም እንደ ሚያስጠይቅ “ባትነግረው የወንድምህን ደም ከእጅህ
እፈልገዋለሁ” ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ ደግሞም ወድ ኢትዮጵያዊ አንባቢ፣ ይህ መልእክት ሃይማኖታዊ ነው አይመለከተኝም ብለህ ከማንበብ ወደ
ኋላ አትበል፣ ሊመጣ ካለው የባሰ መከራ ያስመልጥሃልና፡፡
በኢህአዴግና በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መካከል መግብት የመጥፋቱ ምክንያት “አሕባሽ” ሃይማኖት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመንፈሳ እይታ ሲፈተሸ
ግን በከፊል አንዳንድ ሙስሊሞችና በአብዛኛው ክርስቲያኑ ማህበረ ሰብ የተረዱት አይመስል፡፡ መሆኑም ከፊል ኢትዮጵያዊ ዝምታን መርጦ
ፍጻሜውን በጉጉት የሚጠባበቅ ቢመስልም የኋላ ኋላ ግን የከፈ ሰለባ ተቋዳሽ የሚሆነው ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት እያለ መፈክር
የሚያሰማው ሕዝብ እንደሚሆን ነው፡፡ በጸሐፊው መረዳት አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሃይማኖትን ተገን አድርጎ ወደ ሌሎች
የእምነት ተቋማት እንዳይዘምት ሙስሊም ወገኖች ገትረው በመያዛቸው ነው፡፡ ይህም በምድሪቱ አስከፊው እልቂት ያለ ጊዜው እንዳይከሰት
መከላከያ ይሆን ዘንድ ነው እንጂ ቋሚነት የለውም፡፡ አሁን ግን ተወደደም ተጠላ ከዘመናት በፊት ለጥፋት የተቀጠረው ዓመት ውስጥ
መገኘታችን ነው፡፡ ጥፋቱም በሙስሊሙ ማህበረ ሰብና በወያኔ ሠራዊት መካከል ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በሁለቱ ኃያላን ማለትም
በኢየሱስ ክርስቶስ እና መለያ ቁጥሩ 666 ባደረገው ሳጥናኤል (ሰይጣን) መካከል እንደሚሆን ነው መጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርኣን የሚነግሩን፡
፡ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያለው ኢትዮጵያዊ በሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ የ666 መንፈስ በኢኮኖሚው፣ በሃይማኖት እና በአስተዳደረር ዘርፎች
ጀርባ ሆኖ ሚስጢራዊ አሠራሩን ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ጥቂት ወራት ብቻ እንደቀረው ለማስገንዘብና ከወዲሁ የጉዳዩ አሳሳቢነት ነው፡፡
እንደሚታወቀው በዓለም ዙሪያ በኢኮኖሚው ሳቢያ መረጋጋት እየጠፋ ከመጣ ዓመታት ቢያስቆጥርም፤ በዚሁ በያዝነው ዓመት ግን ብሶበታል፡፡
በአፍሪቃ አህጉርም አይበገሩም የተባሉ መሪዎችን ለሞት፣ ለስደትና ለእስራት ያበቃበት ምክንያት ሲፈተሽ በመጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርኣን
በትንቢታዊ ቃል አስቀድሞ ተጽፎ እናገኛለን፣ ይህም በመጨረሻ ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚሆን ነው፡፡ ትንቢታዊው ቃል እውነት ሆኖ
በአገራችን በኢትዮጵየ ከአርባ ዓመት ወዲህ ችግሮች ተባባሰው እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በተግባር የምናያቸው ችግሮች
መንፈሳዊነትም እንዳላቸው ማረጋገጫው ወደ የአሕዛብ አገዛዝ ዘመን (Democracy, Socialism, Communism and …) ፍጻሜ
በመድረሳችን የዚህ ዓለም ገዥ የሆነውም እጄን አልሰጥም ባይነቱ ከፊት ይልቅ የእርሱ የሆኑትን ምሁሮች ፣ የጦር ኃይሎች በካድሬነት በተለያዩ
የሙያ ዘርፎችን ውስጥ እልቅና ሰጥቶ ሕዝቡን በማፈናቀል፣ ያለ ትክክለኛ ፍርድ እያሰረ እየገደለ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሃላፊዎችም ዘመኑን
በመዘንጋታቸው ለግል ጊዜያዊ ጥቅም ብለው ለኢህአዴግ መንግሥት ማደራቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሕይወታቸው የራቀ መሆኑን
የሚያሳይ ነው፡፡ ሰይጣን በሰው ውስጥ አድሮ ሰውን ተመስሎ ነው ምንጊዜም ጥፋት የሚፈጽማና አሁን በተቀደሰው ሥፍራ ቆሞ ቢታይስ
የሚከለክለው ወይም ማነው? ከምር ቢገለጥስ የህውሃት/ኢህዴግ ባለሥልጣነትና ተባባሪዎቹ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከሚፈጽሙት አሰቃቂ
በደል የተለየ ምን ያደርጋል? የአጋንንቶች ( ጂኒዎች) ሥራ በኢትዮጵያ እንደሚታየውና እንደሚሰማው በየትኛውም አገር አይደረግም፡፡ ዛሬ
ጭቆናውና መከራው በተወሰኑ ወገኖች ላይ ብቻ ቢመስልም ነገ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቸች ላይ እንደሚሆን ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል የወረደላቸው ነቢዩ ሙሐመድም (ሶ.ዐ.ወ) ባስጻፉት ቅዱስ ቁርኣንም ውስጥ የሰው ልጅ የሆነው አልረሕማንም ለፍርድ
እንደሚመጣ፣ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ዲያቢሎስም ሰዎችን ከማሳት ለአንድ ሰኮንድ እንኳ እረፍት እንደማያደርግ ይህ ትውልድ አንብቦ
እንዲረዳውም አድርገዋል፡፡ ታዲያ በሰዎች ሃሳብና አእምሮ ያልተጻፉ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ መጨረሻው ዘመን እናውቅ ዘንድ፣ አውቀንም
እንድንጠነቀቅ መንፈሳዊ አባቶች አቆይተውልን በእጃችን ሆነው ሳለ “ሰላምን ለማስፈን” በሚል በመቻቻል ሽፋን፣ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ
መካከል ቀድሞ የማይታወቀውን “አሕባሽ” ሃይማኖት ተቀበሉ ብሎ በማስገደድ ሰላም ይመጣልን? ለምንጊዜም ቢሆን ሰው ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ
እንደማይቻለው እየታወቀ፤ በሰላም ሽፋን ጀርባ ሆኖ እየሰራ ያለው የጂኒዎች አለቃና ኢብሊሶች መሆናቸው መታወቅ አለበት፡፡ ኢየሱስን
ወድቀህ ብትሰግድልኝ የዓለምን ሥልጣናና ክብር እሰጥሃለሁ ብሎ እንደጋበዘው፣ ዛሬም እውነተኛ አማኞችን እያስጨነቁ ያሉት
የህውሃት/ኢህአዴግ ግብረ አበሮች የሰይጣን መንፈስ በልባቸው ነግሶ በተለያዩ በጎ አድራጎት ስም ተጠራርተው ተከታዮቻቸውን አደራጅተው
ወንጌልን እና ቁርኣንን አስጨብጠው የዲያቢሎስን ስራ በኢትዮጵያ ምድር እያሠሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከዓለም ሕዝቦች 1 % ሀብታሞች ሆነው
99 % ድሆች የመሆናችን ሚስጢርም ይህው ነው፡፡ የኢትዮጵያም ሕዝብ በምድሩ ያሉትን ማዕድናት ማውጣት ተስኖት፣ በተሰጡት ወንዞች
መጠቀም አቅቶች፣ ለምለም ምድሩን በመርዝ አድርቆት በለማኝነቱ ዓለምን ያሰለቸ የሆነው፡፡
ህወሓት-ኢህአዴግ መሪ ለሥልጣን ያበቁት በበጎ አድራጎት የተሰየሙት ድርጅቶች እንደሆኑ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን አዲስ ወሬ አይደለም፡፡ አዲስ
የሚሆነው እነማን መሆናቸውን ስናውቅ ብቻ ነው፡፡ እስራኤል በአገርነት በግንቦት ወር 1948 ዓ.ም (በፈረንጆች) ስትመሠረት፣ ሰይጣንም ቀድሞ
በድብቅ ይጠቀምባቸው የነበሩ ሰዎችን (እንክርዳዶች) በተለያዩ ድርጅቶች ስም ተጠርተው ዓለምን ለመቆጣጠር በቁ፡፡ የእግዚአብሔርም ቃልም
በሉቃስ ወንጌል 22 የአሕዛብ ነገሥታት ሕዝባቸውን በኃይል ይገዛሉ፣ በእነርሱም ላይ ሥልጣን ያላቸውም በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ
ተብሎ እንደተጻፈልን ዛሬም የኢትዮጵያን ሕዝብ እያስጨነቀ ያለው በበጎ አድራጊዎች በኩል ለሥልጣን የበቃው ህውሃት ነው፡፡ ህውሃትን
ለሥልጣን ያበቁት በ1948 ዓ. ም ከተቋቋሙት ተቋማት መሃል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (World
Churches Counsel- WCC)፣ የዓለም ባንከ (World Bank)፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፣ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)፣
የአውሮፓ ሕብረት (EU)፣ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO)፣ የዓለም የምግብ ድርጅት( FAO)፣ የዓለም ጤና ድርጅት
(WHO)፣ በአዲስ ስም የተዋቀረው የተባበሩት መንግስታት (UN) እና መሰል ግዙፍ ድርጅቶች ሲሆኑ፣ በዙሪያቸውም ሌሎች ድርጅቶችን
መስርተው በዓለም ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ወኪሎችም አሏቸው፡፡ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (WCC) ተወለዶ በተባበሩት መንግሥታት
ሙሉ ድጋፍ የተቸረው የተባበሩት የሃይማኖቶች ሕብረት (United Religions Initiative -URI) ሲሆን በስሩ በየአገራቱ ቢሮዎችን ከፍቶ እስከ
ወረዳ ደረጃ ዘልቆ እየሰራ ያለው ለሰላምና ለእድገት በሃይማኖቶች መካከል ራሱን Interfaith Peace-building Initiative እያለ የሚጠራው
ድርጅት ነው፡፡ መርሆውም ወርቃማው የሰላም ምንጭ በመባል የሚጠራው “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ
አድርጉላቸው” የሚለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከቅዱስ ቁርኣን ተውሶ፤ “መቻቻል” የሚባለውን መፈክር አንግቦ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡
የሃይማኖት ሰዎች በአንድ ሃይማኖት ካልተዋቀሩ ሰላምና እድገት አይመጣም ቢልም፤ ከ1300 ዓመታት በላይ በጉርብትና፣ በንግድ ሽርክና፣
በጋብቻ ተሳስረው ያሉትን ኢትዮጵያዊያንን አሁን ምን ተገኝቶ ነው በሰላም ስም የሙስሊሙን ሕብረተሰብ አባቶቻቸው የማያውቁትን፣
ከእንክርዳዶቹ ጋር 1948 ዓ.ም ወደ ዓለም የመጣውን “አሕባሽ” የተባለው ሃይማኖት ተቀበሉ መባሉ ነው፡፡ የሚገርመው ከጥፋት ውሃ በኋላም
ሆነ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እግዚአብሔርን እየተፈታተ ያለው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ነው፡፡ለሰላምና ለእድገት በሃይማኖቶች መሃል (Interfaith Peace-building Initiative) ከአስር ዓመት ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በግብረ ሰናይ
ድርጅት NGO ተመዝግቦ በፍርድ ሚኒስቴር እውቅና የተሰጠው ተቋም፣ በሃያላን ድርጅቶች ሙሉ የገንዘብ፣ የሞራልና የኀይል ድጋፍ ያለውና
መቀመጫው አዲስ አበባ አድርጎ በኢትዮጵያና በአፍሪቃ በበላይነት እየሰራ ያለ ነው፡፡ የስራው ጅማሬ ያደረገው የሃይማኖት ተቋማትን፣
በመጀመሪያ ክርስቲያኑን የሥላሴ አማኞች የአንድነት ሕብረት እንዲመሠርቱ፤ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሕብረት በሚል እንደ የ7ኛው
አድቬንቲስት እና የባሁላ እምነት ተከታዮችን በአባልነት እንዲታቀፉ፣ ከዚያም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሃይማኖቶችን የኢስላምን ሃይማኖት
አጠቃሎ፣ “በኢትዮጵያ የሃማኖቶች ሕብረት ምክር ቤት” በሚል መጠሪያ መንቀሳቀሱን በተመለከተ የዓለም የሰላም ዓመት ቀን ማክበሩን
መስከረም 11 ቀን 2003 በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የባሃኢ
ሃይማኖቶች መሪዎችና ተወካዮች የሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማትና ኢንተርፌይዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢኒሼቲቭ
በጋራ ባዘጋጁት በዓል ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የአፍሪካ ኅብረት
ተወካዮችና የኅብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል” በማለት ውስጣዊ አጀንዳውን ሳይሆን ተልእኮው እንደተሳካለት ገልጾአል፡፡
አሁን በወገኖቻችን ሙስሊሙ ሕብረተሰብ የደረሰው ወከባ፣ እኛ ክርስቲያን ነን፣ አይመለከትም፣ የእኛ ጉዳይ አይደለም በሚሉት ሁሉ ላይ
እንዳይከሰት የሚከለክለው ህውሃት ነው ወይስ ኢህአዴግ ወይስ ማን ነው? መላዕክትን ፈርቶ ነው እንዳይባል ከዚህ ቀደም ጦርነት ገጥሞአቸው
እንደነበር ተጽፎልናል፡፡ አጋንንቶች ለመሲሁ ኢየሱስ “ያለ ጊዜው ልታጠፋን መጣህን?” ማለታቸው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ሰዎች በፈቃዳቸው
ገዥአቸው ሆኖ የክፋት ሥራዎቹን እያሠራቸው መጨረሻም አብረው ለዘላለም በሲዖል እንደሚኖሩ አምነውበት እንደሚሠሩ ነው፡፡ “ሰው
ለሁለት ጌቶች መገዛት አይችል፣ አንዱን ይመርጣል ሌላውን ይጠላል” ተብሎም ስለተጻፈልን አሁን በአገራችን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው
ሁኔታ ከእግዚአብሔር ይሁን ወይም ከሰይጣን መሆኑን አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ቁርኣን አንባቢ ብቻም ሳይሆን ሰው በደመ ነፍሱ መለየት
አያቅተውም ክፉና ደጉን ለይቶ ላወቀ ሰው፡፡ ሰዎቹ አገልጋዮቹም በሥራቸው ይታወቃሉና፡፡
በመቻቻል መፈክር ውስጥ “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።” የሚለው የሚደገፍ ቢሆንም ውስጡ ግን
ሞት ነው ያለበት፡፡ ለአገር የሰላም መርህ ሆኖ በስድስቱም የሃይማኖት ተቋማት በፌድራል ደረጃ ተመሥርቶ እስከ ወረዳ ድረስ ዘልቆ በመካሄድ
በ690 ምክር ቤቶች ተዋቅሮ፤ አንድ ለአምስት (1፡5, 1+5=6) በተደራጀ ግብረ ኀይል ተደራጅቶአል፡፡ እነዚህ ምክር ቤቶች የተባበሩት
የሃይማኖቶች ሕብረት (United Religions Initiative -URI) ተነሳሽነት፣ ለሰላምና ለእድገት በሃይማኖቶች መሃል Interfaith Peace building
Initiative ፍርድ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት በበላይነት፣ በአስፈጻሚነት፣ ትዕዛዝ ሰጪነትና በፖሊስ ኀይል ትብብር የሚመለከታቸው የሃይማኖት
ሰዎችን በማሰልጠን ተግባራዊ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን የአዲስ አበባ አስተዳደር ኮሙኒክሽን ቢሮ በኩል የሚተላለፈው ቴሌቪዥን
ጣቢያ በአዲስ ዝክረ ሐሳብ ፕሮገራም የካቲት 2004 ይፋ አድርጎታል፡፡ በዚያው ሰሞኑንም በአስቸኳይ ለሁለት ቀናት ለ32000 የወረዳ
ባለስልጣናት ስልጠናም እንደተሰጠም ነው ሪፖረቱ ያስደመጠው፡፡
በራዕይ መጽሐፍ 13፡18 “666”ን የአውሬው ቁጥር፣ የሰው ቁጥር ይለዋል፡፡ ሰዎችም የሰይጣን መለያ ቁጥር እንደሆነ ተቀብለውታል፡፡ 666
ሲብራራ በውስጡ 6 + 6 + 6 = 6 እንደሆነም ነው ጸሐፊው በመንፈስ የተረዳው፡፡ 6 + 6 + 6 = 6 ቁጥሮች የሚወክሉትም ሰይጣን በሦስት
ዋና ክፍሎች ማለትም በሃይማኖት፣ በምጣኔ ሀብት እና በጦር ኃይል ጀርባ ሆኖ በምድር ላይ የመጨረሻውን ፍልሚያ ለማድረግም ሦስት ሰዎችን
በመሾም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ የሰው ቁጥርም የተባለው ሰው ጻድቅ ከሆነው ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን (አልመሲሕ
ኢሳን) ከመከተል ይልቅ ቅድስና የጎደለውን ሳጥናኤልን በተከተሉ ሰዎች ውስጥ የአመጽ መንፈሱን አኑሮ ነው ወንጀልን የሚፈጽመው፣
የሚያስፈጽመው፡፡ ሃይማኖትን የሚወክለው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (WCC- URI- Interfaith Peace-building Initiative)፣
ኢኮኖሚውን የሚወክለው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)፣ ሰላም እስከባሪውን የሚወክልው የጦር ኀይሉ የሰሜን አሜሪካ ቃል ኪዳን ድርጅት
(NATO) ናቸው፡፡ ለሶስቱም በገንዘብ አቅርቦት ድርሻቸውን የሚወጡት ደግሞ የዓለም ባንክ እና አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሲሆኑ ሌሎች
ደግሞ በድጋፍ ሰጪነት ያሉ ሆነው የስምሪቱን ክፍል የያዘው የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ሆኖ ለነዚህ ሁሉ በአላፊነት ተቆጣጣሪነት
የሚሠራው በ1948 ዓ.ም ማርሻል ፕላኑን (Marshal Plan) የዘረጋውና “በዓለም ዙሪያ የአገራችንን ጥቅም ማስጠበቅ አለብን” የሚለው የሰሜን
አሜሪካ መንግስት (USA) ሲሆን ተባባሪና ረዳቱም የእንግሊዝ መንግስት (Great Britain) በመሆኑ ለስልታቸው ማስፈጸሚያና የመተግበሪያ
ሥርዓትም ማኒፌስቶ ዴሞክራሲ ነው፡፡ መፈክሩም “ማንም አገር በዴሞክራሲ ስርዓት መተዳደር አለበት” ነው፡፡ ዴሞክራሲ ስሙ
እንደሚያመለክተው ሰይጣናዊ የአስተዳደር ሥርዓት (demon bureaucracy) እንደሆነም ነው፡፡ ይህም ለአዲሱ ዓለም መንግሥታዊ ስርዓት
New World Order lሰይጣን መንግስት መሠረት የሚጥል መሆኑ ነው፡፡ ዲሞክራሲ በማር የተሸፈነ ወደ ሞት የሚነዳ ኃይል ነው፡፡
ሶሻሊዝም፤ ኮሚኒዝም እና ሌሎች የአስተዳደር ሥርዓቶች ለሰይጣን ተገዥ አይደሉም ማለት አይደለም፡፡ ዘካሪያስ ትንቢታዊ መጽሐፍ ምዕራፍ 6
“ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት የወጡ አራቱ የሰማይ መናፈስት መጋላ፣ ዱሪ፣ አምባላይ፣ ዥንጉርጉር (ከሦስቱም ጀርባ ያለ) ፈረሶች” በዮሐንስ ራዕይ 6
ደግሞ ስራቸውን ሲገልጽ ቀስት የያዘው ጦረኛ፣ የሰሜን አሜሪካ ቃል ኪዳን ድርጅትን( NATO) የሚወክል፣ ሰላምን ከምድር ላይ የሚወስደው
በሃይማኖት ሽፋን በመቻቻል መፈክር፣ ሸክላና ብረትን፣ ጨለማን ከብርሃን ሊያዋህድ ደፋ ቀና የሚለውና ሰዎችን እርስ በእርሳቸው
እንዲተራረዱ እያደረገ ያለው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (WCC) ሲሆን፣ ሦስተኛው ወዮ! ደግሞ ኢኮኖሚውን የያዘው የዓለም የንግድ
ድርጅት (WTO) ሆኖ በሶስቱም ጀርባ የሚሰራው ሞት ሆኖ ሲዖል የሚከተለው ነው፡፡ WCC news Addis Ababa, 24 September ( WCC)
– general secretary, the Rev. Dr Olav Fykse Tveit the WCC brings together 349 Protestant, Orthodox, Anglican and other
churches representing more than 560 million Christians in over 110 countries, and works cooperatively with the Roman
Catholic Church በማለት አስነብቦአል፡፡ “አመንዝራይቱ የምትቀመጥባቸው ሰባቱ ተራሮች ናቸው፣ የምድር ነገስታትም ከእርሷ ጋር አመነዘሩ፣
የምድር ነዋሪዎችም በዝሙቷ ሰከሩ…የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ በአንድ ሃሳብ እንዲስማሙና ስልጣናቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ
ይህን ሃሳብ ለቃሉ ባለመታዘዙ ሰዎች ልብ ያኖረ እግዚአብሔር ነው”
Interfaith Peace-building Initiative የኢትዮጵያ ወኪልና ተጠሪ፣ ማንም ሰው ስለ ድርጀቱ መናገርም ሆነ መጻፍ በሕግ ያስጠይቃል ቢልም፣
ተጨባጭ እውነትን ለወገን ማሳወቅና ከዘላለም ሞት ማስመለጥ የጸሐፊው ግዴታው ቢሆንም አንባቢውም ማምለጥም ሆነ ያለማምለጥ ምርጫ
ነው፡፡ በአገራችን እየተካሄደ ያለው ሁኔታ ፖለቲካውን ምክንያት አድርጎ በእምነት ተቋማት ላይ እየተወሰደ ያለው ወከባ ከዚህ ድብቅ ሴራ የተለየ
አይደለም፡፡ Skull and Bones elite club was founded by the illuminist, ሰይጣናዊ ድርጅት መሆኑና ተግባሩም አዲሱ የዓለም ሰይጣናዊ
ስርዓት- New World Order´s missioning for the United Religion Initiative (URI) to develop a deep understanding of how
politics, economics and faith can come together in the 21st century for the good of humanity የሚለውን ለመተግበር
የሚንቀሳቀስ ደርጅት ሆኖ በይበልጥ በወጣቶች ላይ ሚስጢራዊ ሴራውን እያስፋፋ ነው፡፡
ሰይጣን በሦስት ዋና ክፍሎች ጀርባ ሆኖ በምድር ላይ የመጨረሻውን ፍልሚያ ለማድረግ ሦስት ሰዎችን በዋናነት በአገራችን መርጦአል፡፡
ከእነዚህም ሦስት ሰዎች መሃል ሁለቱ በሕወት ባይኖሩም ሥራቸውን የተረከቡ ሰዎች ለቦታው ትክክለኛ ሰው በመሆናቸው ከጠላት በኩል
ምንም ተቃውሞ አልተሰማም፡፡ 1ኛው 6 ቁጥር የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ሊቀ መንበር፤ በኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ሊቀ መንበርና የዓለም አብያተ
ክርስቲያናት ፕረዚዳንት የሆኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክነት የተሰየሙ፣ በስራቸው በሚተዳደረው
እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ የሳጥናኤልን መንግስት የሚወክለውን የህወሃት ባንዲራ እንዲውለበል መደረጉ፣ በኢትዮጵያ
የሰይጣን መጽሐፍ (Satanic bible) በገበያ ላይ ሲውል ክርስቲያናዊ ሥልጣናቸውን በመጠቀም መቃወም ሲገባ ዝም መባሉ ቤተ
ክርስቲያኒቱ ውድቀት ላይ እንዳለች አመላካች ነው፡፡ ሰውየው በሕይወት ባይሆሩም እርሳቸውን የተኩት ፓትሪያርክም በዚያው መንገድ
በመሄዳቸው በ1ኛው 6 ቁጥር መንፈስ የሚመሩ በመሆናቸው በቀሳውስት ዘንድ በቂ ድጋፍ የላቸውም፡፡ የቀድሞውን እና ያሁኑን የሾመው
ህውሃት ነውና፡፡
 2.ተኛው 6 ቁጥር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመዳፉ አስገብቶ በብቸኝነት እንዲቆጣጠር በህወሓት-ኢህአዴግ ባለስልጣናት የተቸረው ሼኽ
አላሙዲንን ነው፡፡ የሳውዲ ቱጃር በኢትዮጵያዊነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ሕብረት በአንድ ሃይማኖት
እንዲጠቃለሉ ከፌድራል እስከ ወረዳ ለተዋቀረው ምክር ቤት አንቀሳቃሽ ኀይል የገንዘብ ምንጭ ነው፡፡ በሳውድ አረቢያ ዜግነቱና
ተደማጭነቱ ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ እስር ቤቶች ለሚደርስባቸው ስቃይንና መጉላላትን ለማስቆም ድምጹን አሰምቶ አያውቅም፡፡ አሁንም
ከአጋሮቹ ከህውሃት መሪዎች ጋር በመሆኑ በማን አለብኝነት በሰይጣናዊ መንፈስ ሕዝቡን መዝለፍ አባብሶታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ
በእርሱ ገንዘብ ይተዳደር ይመስል፡፡
 3ተኛው 6 ቁጥር አገሪቱን በአምባ ገነንነት ለ21 ዓመት እየመሩ ያለው በህወሓት-ኢህአዴግ ሊቀ መንበርነት የሰይጣን ስርዓት ለማስፈጸም
ደፋ ቀና በሚሉ ተቋማት WTO NATO World Bank and IMF እውቅና የተቸረው ጠ/ሚር መለሰ ዜናዊ ነበር፡፡ ባህርያቱን ብንመለከት፣
መሲሁ ኢየሱስ ስለ ነፍሰ ገዳዩ ዲያቢሎስ ባህርይ ሲናገር ነፍሰ ገዳይ፣ ሃሰተኛ፣ እውነት ከእርሱ ዘንድ የሌለ መሆኑን በአንደበቱ ይደመጥ
የነበረው ስድብ እና ክህደት ብቻም ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቲቪ እና ሬዲዮ ጣቢያዎች “ጣታችሁን እና እግራችሁን እንቆርጣለን”
ማለቱ ነው፡፡ በዕለት ውሎው አምላኩን በመፍራት የሚኖረውን ሕዝብ በሃይማኖትን እና በኢኮኖሚው ዙሪያ አስጨንቆ፣ በጆሮ ጠቢዎችም
ፍዳውን እያሳየ ነበር፡፡ የማነኛውም አገር መሪ የሚያስተዳድረውን ሕዝብ በመገናኛ ብዙሃን ሲሳደብ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ በኢትዮጵያ
ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያም እና የመጨረሻም ጨካኝና ተሳዳቢ እንደ ነበረ የፓርቲው አባላት በሙሉ የማይክዱት ሃቅ ነው፡፡ ታሪካችሁ
የ100 ዓመት ታሪክ ነው፣ ኢትዮጵያዊያን አባቶችና እናቶች የሞቱለትን ባንዲራ፣ ጨርቅ ነው እንዲል ድፍረት የሰጠው ሳጥናኤል መንፈስ
ካልሆነ ማን ሊሆን ነው፡፡ አሁንም በእግሩ የተተካው ወንጌል እያሳየ ጥፋትን ያደርግ ዘንድ የተመረጠው በሟች መለሰ ዜናዊ ሲሆን ይህም
በሁለቱ ሰዎች መካከል የመንፈስ አንድነት እንዳለ ነው፡፡
ሦስቱን ሰዎች ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለው 666ቱ በክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስን የሚወክለው በኢኮኖሚው፣ በማሕበረ ሰብ ጉዳይ፣ በጦር ኃይሉን
የተቆጣጠር ጠ/ሚር ጀርባ ሆኖ በበላይነት የሚንቀሳቀስ አፍሪካን በመወከል በዓለም መድረክ ያቆመው፣ በG8 እና G20 ስብሰባዎች
በተመልካችነት እንዲገኝ ያደረገው፣ በምስራቅ አፍሪቃ የኢጋድ ሊቀመንበር፣ የኔፓድ ሊቀመንበር፣ የፓን አፍሪቃ ሸንጎ በበላይነት የሚመራው፣
የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የጦር አዛዥነት፣ አፍሪቃን በመወከል ተከራካሪ፣ ከአፍሪቃ ተደማጭ መሪ ፤ የአረንጓዴ ልማታዊ መንግስት መስራች፤
አብዮታዊ ዴሞክራሲ ገንቢ፣ ሌላም ሌላም ማዕረግ የሰጠው ሰይጣን በዓለም መጨረሻ በእርሱ ውስጥ እንዲገለጥ ፈልጎ እንደነበረ ነው፡፡
ሰይጣንም ሁሉን አያውቅምና ቢያውቅማ ኖር በእግዚአብሔር ላይ ባላመጸመን ነበር፡፡ ታዲያ ሰይጣን የራሱን እንጂ የእግዚአብሐርን ሐሳብ
ስለማያውቅ ሁሉን ሥልጣን ለአቶ መለስ ቢየሸክመውም ለቦታው ትክክለኛ ሰው ይመጣ ዘንድ በሞት ተወሰደ፡፡
በሰው አስተሳሰብ በወቅቱ ሕክምና አድሮ አድሜውን ማስረዘም ሲችል በመካከለኛ እድሜ መቀጨቱ ምክንያት በእግዚአብሔር መንፈስ ሲፈተሸ
በዘመኑ ማብቂያ ላይ ስለሆንን የፀረ ክርስቶስም ባህርይ ተላብሶ ወደ ፍፃሜው እንዳይመጣ እንቅፋት የሆነበት የወንጌል አማኝ ነኝ ብሎ ራሱን
ባለማስተዋወቁ ነው፡፡ ስለሆነም አቶ መለስን የተካው ጠ/ሚር የወንጌል አማኝ ነኝ ቢልም በኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ተሞልቶ
መንቀሳቀሱን በተመለከተ ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ ዓለምን እየተቆጣጠሩ ያሉት ኢሉሚናቶች ሲሆን ም/ ጠ/ሚሩምን ያለ ሕዝቡ
ፈቃድ የአገሪቱ መሪ አድርጎ መሾሙ የመንፈስ አንድነት እንዳላቸው ማሳያውም እርዳታ፣ ብድርና መሰል ጥቅሞች አንሰጣችሁም መባሉ ነው፡፡
ጠ/ሚሩ ሥልጣን በያዙ ማግሥት መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው መጽሔቶች ጠ/ሚርን በተመለከተ “ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዳግም የተወለደ መሪ
አገኘች” ከማለት ባለፈ “የቅዱሳን እምባ ውጤት ነው እግአብሔር እርሳቸውን የሾማቸው” ተብሎ እልልታው ሳያቆም በማግሥቱ ከሟች መለስ
አገዛዝ ዘመን በበለጠ ኢትዮጵያዊ በግፍ እየተገደለ፣ ከመኖሪያ እየተፈናቀለ፣ የእታሰረ፣ በዓረብ አገራትም ስቃይና መከራው እየጸና የመጣው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛምርቱንና ተከታዮቹን ሲያስተምር “ሰዎች የእኔ መሆናቸውን በፍሬዎቻቸው ይታወቃሉ” እንዳለው አቶ ኃይለ ማርያም
ደሳለኝ በእውነት የኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት ደረጃ ተከታዩ ቢሆን ኖሮ አሁን በዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ከመብዛቱ
ይልቅ እጅግ ቀንሶ ሕዝቡ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት እግዚአብሔርን ስለ ስጦታው ባመሰገኑ ነበር፡፡
አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሰ አታምጠብን እያለ አምላኩን መማጸኑ አላቆመም፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዘመኑን በሚገባ
ስላልተረዱ ራሳቸውን እና ሕዝቡን ይዘው ሰው በገዛ ኃይሉ ሊወጣው ወደ ማይቻለው የከፋ መከራ እየከተቱት ነው፡፡ ከታሪክ የተማርነው ለ6
ሚሊዮን አይሁዶች ሕይወት መጥፋት የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አስተዋጽዖ እንደነበረበትና በኢጣሊያን ወረራ ጊዜ ባንዳ ሆነው ሕዝቡን
ይገድሉ፣ ቤቱን ያቃጥሉ የነበሩት ክርስቲያኖች ያውም የኦርቶዶክስ አማኞች ባንዳ እንደነበሩ ታሪክ የሚነግረን፡፡ ዛሬም በምድረ ኢትዮጵያ
እያንዣበበ ላለው ሰይጣናዊ መንፈስ ፕሮቴስታንቶች፣ ካቶሊኮች፣ ኦርቶዶክሶች ሌሎችመ ድጋፋቸውን ከመስጠት አልተቆጠቡም፡፡ በየቤተ
ክርስቲያኑ አጋንንቶችን በጸበል፣ በኢየሱስ ስም ከማስጮኽ፣ ባለ 6 ፎቅ አምልኮ ቤት ለመስራት ኮሚቴ ከማዋቀር፣ የገቢ ምንጭ ለማሰባሰብ
ምእመኑን ከመማጸን ባለፈ ስለ መጨረሻው ዘመን በተመለከተ ሲያስተምሩና ሲያስጠነቅቁ አይደመጥም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው
ሁሉን ይመረምራል ቢባልም ዘመኑን ስላለወቁ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጀሌውን ሰይጣን እያስጮኹ ተላልቆቹ አጋንንቶች በህውሃት/ኢህአዴግ
ባለሥልጣናትና ካድሬዎችን ጨምሮ አገርን ሲያፈርሱ፣ በኢኮኖሚውና በማሕበራዊው ጉዳዮቻችን ላይ ትኩረት ባለመስጠታቸው የክህነት
አገልግሎታቸው ዘንግተዋል፡፡
ኢህአዴግም ለውጭ ምንዛሪ ሲባል አለም አቀፍ ስብሰባዎች በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ፈቃጅና አቀነባባሪሪዎች ኢሉሚናቶች የአዲሱን ዓለም
ሥርዓት አራማጆች NEW WORLD ORDER ናቸው፡፡ ያለ ኢሉሚናቶች እውቅና ማንም የአገር መሪ መሆን አይችልም፡፡ እነርሱም በልዩ ልዩ
ስሞች ይጠራሉም “Council on Foreign Relations,” in the United States and its hierarchy. In England “British Institute of
International Affairs.” There are similar secret Illuminati organizations in France, Germany, and other nations operating
under different names and all these organizations, including the CFR, continuously set up numerous subsidiary or front
organizations that are infiltrated into every phase of the various nations’ affairs. The leaders of all major industrial
countries like the The United States of America, England, Germany, Italy, Australia, New Zealand, etc(Members of the
G7/G8 ) are active and fully cooperative participants in this conspiracy. የሥራ ተባባሪዎቻቸውም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጥቶአቸው ወጣቶቸን በመመልመል ዲሞክራሲን ሕዝቡ በግዴታ እንዲቀበል እያደረጉት ነው፡፡ ለዚህና ሌሎችን ድብቅ
ሥራዎቻቸውን በጥልቀት ለማወቅ ለሚፈልግ www.thirdworldtraveler.com/democracy by force ሌሎችን ማንበብ ነው፡፡እግዚአብሔር ዙፋኑ የጣላቸው ሉሰፈርንንና አጋንቶችን ለማስቀናት የመጀመሪያውን ሰው አዳምን በአምሳያው የሠራበት ሥፍራ ኤደን ገነት
ተብላም የምትጠራ፤ መዝሙረኛው ዳዊትም “ጽዮን የሕዝቦች እናት” ያላት ይህችው አገራችን ኢትዮጵያ በመሆንዋ ነው የሰይጣን ግብረ አበሮች
ዐይናቸውን ለጥፋት የጣሉባት፡፡ የአዳምን ዘር ሁሉ ከጨለማው ከሰይጣን ግዛት ነፃ ለማውጣት የምስራቹን ቃል ለዓለም ሕዝቦች ለማብሰር
የተመረጠውም ይህው ሕዝብ ነው፡፡ ሰይጣንም በፊናው አገራትን ሁሉ ለስርዓቱ አስገዝቶ ምድርን ለራሱ ለማድረግ የቀረው ይህችው ኢትዮጵያ
ናት፡፡ ለእቅዱ ዋና ሠራተኞች አድርጎ የሾማቸው የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግሥታትም በሰይጣናዊ መንፈስ ዓለምን እየመሩ ያሉ ቢሆኑም፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ተንኮላቸውን ያወቀው በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ለወረራ ከመጡበት ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ አጼ ቴዎድሮስም ዐይኔ
እያየ ኢትዮጵያን ለጠላቶችዋ አሳልፌ አልሰጥም ብለው በገዛ ሽጉጣቸው ሕይወታቸውን እንደሰው ታሪክ ምስክር ነው፡፡ አፄ ኃይለ ሥላሴም
በወንጌል እምነታቸው የኢሉሚናቲን ሽንገላ እምቢ በማለታቸው በ1953 ዓ.ም ከስልጣን ለማውረድ የሴራውም ጠንሳሽ የነበሩ አገራት በሁለቱም
ቡድን አማካሪ በመሆን የአገር ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎችን አስፈጅተዋል፡፡ በ1966 ዓ.ም ሚኒስቴሮችና የፓርላማ አባልትን አስረሽነዋል፡፡ በ1982
ለአገር ተቆርቋሪ የነበሩትን የጦር መኮንኖችንም አስጨርሰው በመጨረሻም ተልዕኮአቸውን የሚያስፈጽምላቸውን ሰው ማስቀመጥ ስላለባቸው
በአቶ መለስ የሚመራውን ህውሃት ለሥልጣን አብቅተው ተልዕኮውን ከሞላ ጎደል እዚህ አድርሰዋል፡፡ ዛሬም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን ወንጌል
አስጨብጠው ለመጨረሻውን ፍልሚያ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለማድረግ ያለ ሕዝቡ ፈቀድ ሾመውብናል፡፡
በነቢያት አንደበት ሁከት በግብፅ፣ በሊቢያ፣ በኢትዮጵያ እንደሚነሳ ተንብየው ነበር፤ ትንቢቱ ዘመናትን ተሻግሮ በዚሁ በመጨረሻው ዘመን
በጦር ሃይላቸው፣ በስለላ መረባቸውና በገንዘባቸው ተማምነው የነበሩ የግብፅ እና የሊቢያ መሪዎች በእስራትና በሞት ሲለዩ አይተናል፡፡ ይህም
ለመጨረሻው ዘመን ጅማሬ መሆኑን የትንቢቱን ፍጻሜ የሚጠባበቁ መንፈሳዊ ምሁራን በሰፈው እየተነጋገሩበትና እየጻፉ ናቸው፡፡ ደግሞም
ትንቢቱ ወደ ፍጻሜ ይቸኩል ዘንድ ግድ ስለሆነ በኢትዮጵያ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡ ያኔ እንደ ሊቢያና ግብፅ በአጭሩ የባለ ስልጣናት ሽግግር
ብቻም ሆኖ የሚቆም ሳይሆን ስር ነቀል ለወጥ የሚያመጣ ሆኖ የዓለምን ሕዝብ የሚያስደነግጥና የባለስልጣናትን ቅስም የሚሰብር በመሆኑ
እግዚአብሔርም “በመንፈሴ እንጂ በሃይልና በብርታት አይደለም” እንዳለው በቃሉ የታመኑ ቅዱሳን በጉጉት የሚጠብቁት ነው፡፡ ከአመጸኛው
ሰው ቁጣ ለመዳን ወደ ተራሮች በመሮጥ ሳይሆን አሁኑኑ መቻቻል የሚለውን በመቃወምና ከአውሬው ቁጥር ስድስት መቶ ስላሳ ስድስት (666)
አባልነት፤ ከማነኛው ከኢህአዴግ ጋር ንክኪ ካላቸው ጉዳዮች ማምለጥ ነው፡፡ የጻድቁን ልብስ የረከሰ ነገር ቢነካ ጻድቁ እንደሚረክስ ሁሉ አንተም
ጻድቅ ነኝ የምትል እንዳትሰናከልና እንዳታሰናክል ተጠንቅ፡፡ “ጊዜውን ዋጁት” የተባለውም ለዚህ ጊዜ መሆኑን አንባቢ ቢያስተውለው ጥቅሙ
ለራሱ ነው፡፡ በሃይማኖት ስም እውነት ከእኔ ጋር ነው፣ አማኝ ነኝ፣ ዳግም ተወልጃለሁ እየተባለ የሰይጣንም ማህበርተኛ መሆን አይቻልም፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ዘንድ ተዘውትሮ የሚደመጠው “ለባለ ሥልጣን ተገዙ” የሚለውን ነው፡፡ በርግጥም ወንጌሉ
ቢልም፣ መሪው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲያስተዳድር ነው እንጂ ነፍስ ገዳዩን በመዝሙር 144 ፡5-9 እንደተጻፈው ማሰርም እንደምንችል ነው፡፡
ደግሞም የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ወንጌል ነፃነትን የሚያውጅ ነው እንጂ ከሠይጣን ሥራዎች እንድንተባበር አያዝም፡፡ ይለቅስ ሕዝቡን በአገሩ
ሰላም እየነሳ ያለውን መንግሥት በመደገፍ የታበያችሁ ሊመጣ ካለው የእግዚአብሔር ቁጣ እንዴት ታመልጡ ይሆን?
እኛ ክርስቲያን ተብለን የምንጠራ ሁሉ፣ ዛሬ በምድራችን በ1948 ብቅ ያለውን በኢትዮጰያዊ ሼኽ ዐብደላ ሐረሪ አስተምሮ የሚጠራው አሕባሽ
ሃይማኖትን ካልተቀበላችሁ ተብለው ለእስራትና ለወከባ የተዳረጉ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ጉዳይ የእኛም ጉዳይ እንደሚሆን ለአንድ አፍታ
መጠራጠር የለብንም፡፡ ለምን እና እንዴት ቢባል፣ የአሕባሽ ሃይማኖት ለሙስሊም ሕብረተሰብ ብቻ የመጣ ሳይሆን ለሁሉም ነው፡፡ የአሕባሽ
ሃይማኖት መላውን የዓለም ሕዝብን በአንድ ሃይማኖት (Universal Church) ሥር አድረጎ በአንድ ሰው (ሰይጣን) መሪነት ለማስተዳደር ነው፡፡
One World Government የሚባለው ከዚህ የተለየ ነገር የለውም፡፡ ዋናው ተልዕኮ በምድሪቱ ግብረ ሰዶማዊያንና ሌዝቢያንን ለማስፋፋትና
እውቅና ለማስገኘት እንደሆነ ቢታወቅም፣ በሶዶሚያዊያን ላይ ከረር ያለ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ለዚህ ለሰይጣናዊ ሥራ ተባባሪ የሆነውን
መንግሥት በጸሎትም ሆነ በስብከት መደገፍ ሰዎች በወንጌል አምነው እንዳይድኑ እንቅፋት መሆኑ መታወቅ ያለበት ሃቅ ነው፡፡ ይህም ቅጣቱ
ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር ከመጣል የከፋ በእሳት ባሕር ለዘለዓለም መቃጠልን የሚያስከትል ነው፡፡ ሰይጣን እና
ህውሃት/ኢህአዴግ ውለታን አያውቁምና፣ የኢህአዴግ ደጋፊም ሆንህ ወይም ተቃዋሚ ዛሬ አገርን ለመታደግ ከተቃዋሚ ጋር ኃይልህን
ካላስተባበርህ የንፁህ ሰዎች ደም ተጠያቂ ከመሆን የሚያስጥል ኃይል የለም፡፡ “ሰው ኀጢያት ሲሰራ አይተህ ባታስጠነቅቀው፣ ደሙን ከአንተ
እሻለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፡፡ በምሳሌ 25፡26 “ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣ እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጉድጓድ ውሃ ነው፡፡”
የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም፡፡ መዝሙር 125፡3
የኢትዮጵያ ሕዝብ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በዕለት ውሎው የአምላኩን ስም ሳይጠራ የማይውልና የማያድር ሆኖ ሳለ በተለያዩ ምክንያቶች ለም
መሬት እያለው፣ ትላልቅ ወንዞች ባለቤት፣ ታታሪ ገበሬ፣ በአንድነቱ የሚተማመን፣ በእምነቱ የጸና፣ ዳር ድንበር አስከባሪ ሆኖ ሳለ በረሃማ መሬት
እንዳለው፣ ወራጅ ወንዝ እንዳጣ፣ ወኔ እንደሌለው፣ ሠራዊቱ ሁሉ እንዳለቀበት ዳር ድበር ፈርሶ በረሃብተኝነቱ የዓለም ሕዝብ ያወቀው፣
በስደተኝነቱ መንግሥታትን ያሰለቸ፣ መሪዎቹ የጨከኑበት እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አለን? በዚህ ጉዳይ ሙግት ለመግጠም ሳይሆን
በጸሐፊው መረዳት በሦስቱም ያገዛዝ ዘመን ማለትም በአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ በደርግ እና ህወሃት/ኢህአዴግ አስተዳደር ዘመናት ለችግሮቻችን
ምክንያት እና መንስሔው ምን ይሆን በማለት በዐይነ ሕሊናው ሲያወጣና ሲያወርድ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብም
እውነቱን እንዲያውቅ ነው ያ ሁሉ መጻፉ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኃይለ ሥላሴ ውድቀት በኋላ እምነት የሌላቸው መሪዎች ተነስተው ክደት ቢያስተምሩትም፣ ለአርባ ዓመት ያህል ከነችግሮቹ
አምላኩን ማምለክ አላቆመም፣ እግዚአብሔርን የመፍራት ባህርይ አልተለየውም፡፡ ለሕዝቡና ለምድሪቱ ውድቀት ምክንያት የሆነውን ለማወቅ
የምጣኔ ሀብት ጠበብት፣ የፖለቲካ ተንታኝ፣ የማህበረ ሰብ ምሁር አሰባስቦ አለም አቀፍ ወይም አገር አቀፍ ኮንፈረንስ ማካሄድ ሳያስፈልገው
የችግሩ ምንጭ ተረድቶት ሳለ ከሃዲ አለቆችንና ግብረ አበሮቹን በመፍራት ዝም ቢልም መጪውን የጥፋት ወራት በዝምታ ማለፍ ስለማይቻለው
ሊያደርገው የሚገባውንና የዘነጋውንም “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች”Ύ የሚለውን ለማስታወስም ነው፡፡ በሾዛሊዝም እና
በዲሞክረሲ ሥርዓቶች ከምድራችን ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን ብለው የተነሱ መሪዎች ሕዝቡን በሰው ጉልበት ሊወጣው ወደ ማይችለው
አዘቅት ከተቱት፡፡ አሁን ያሉት ችግሮች አንሶታል ተብሎም በየቀኑ ዓይነታቸውና ብዛታቸው እየበዙ መጡ እንጂ በሶሻሊዝም፣ በኮሚኒዝም ሆነ
በዲሞክራሲ መፍቴ አልተገኘም፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች የተባሉትም ቤተ እምነቶች ሰዎችም በራሳቸው ችግሮች ተተብትበው ወንድሞችንና
እህቶችን በእግዚአብሔር ቃል ሲያጽናኑ አልተሰማም፡፡ የመፍቴ ሰዎች የተባሉት የፓርቲዎች መሪዎችም የመብዛታቸው ያህል በመከፋፈላቸው
እስር ቤትን አጣበቡ እንጂ ሕዝቡን ለመታደግ፣ አገርን ከመቆራረስ ለማዳን ወደ አንድነት መምጣት ተስኖአቸዋል፡፡
የኢትዮጵያን ውድቀት የሚሹ ባዕዳን ነገሥታት ጥቂት አፈ ጮሌ ምሁራንን በመያዝ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ዲሞክረሲ ቀመስ እውቀታቸውን
በኢትዮጵያ ምድር ለመተግበር ባላቸው ምኞት ተማሪዎችን በማስቀደም፣ ጦር ሠራዊቱን ደጀን በማድረግ የተንቀሳቀሰው ድብቅ የደርግ ኃይልከንጉሡና ከወታደሩ ጋር ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የቆሙትን ምሁራንን በጠራራ ፀሐይ ረሸኑ፡፡ በመቀጠልም ኢትዮጵያ ትቅደም ያለ ምንም ደም
ተብሎም የሰው ክቡር ደም መፍሰሱን የሚያስቆም ኃይል ጠፍቶ በእየዕለቱ ስልጣን ላይ ላስቀመጧቸው አጋንንቶች ደም ከማፍሰስ
አልተቆጠቡም ነበር፡፡ ባለሥልጣናትም በእርኩስ መንፈስ ቤተ ክርስቲያናትን በምድሪቱ አንዳናይ ከፊሉን አሽገው፣ ከፊሉን በቁጥጥራቸው
በማድረግ በእየለቱ ከአንደበቱ አምላኩን ማመስገን የሚወደሰውን ሕዝብ ክህደት አስተምረው ባዕድ ጣዖታትን አምላኪ አደረጉ፡፡ ምድሪቱም
እሾኽና አሜከላ አበቀለች፣ ሕዝቡም ለከፋ ችግር ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ቀድሞ ለትምህርትም ሆነ ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጪ አገር ይሄዱ የነበሩ
ኢትዮጵያዊያን የተከበሩና እንደ ዐይን ብሌናቸው ይጠነቀቁላቸው እንዳልነበሩ ዛሬ በየአገሩ ተሰለቸን፣ እነርሱ (ኢትዮጵያዊያን) የሌሉበት የት
እንሂድ እስከማለት ተደረሰ፡፡ ያም አልበቃ ብሎ ከእንሰሳት ባነሰ ሁኔታ ታይተን የመድኃኒት ሙከራ ተደረገብን፡፡ በሕይወት እያለን አንዱ
ኩላሊታችን ተወስዶ ለባዕዶ ተሸጠ ያውም በአገራችን፡፡ እንዲያም ሆኖ ጥቂትም ቢሆኑ እግዚብሐርን የሚፈሩ ሰዎች በምድሪቱ በመኖራቸው፣
ዉድቀታንን ለሚፈልጉ ተላልፋ ባትሰጥም ሕዝቡን ግን በተሰጠን ለም መሬት በምታበቅላቸው ፍሬዎች በምስጋና መመገብ አቅቶን የሰውን
በመመኘታችን ለስደት ተላልፈን ተሰጠን፡፡ ህውሃት በስልጣን ተፈናጦ ቀድሞ የአገር ድንበር አስከባሪ የነበረው ወታደር፣ ዛሬ የኢትዮጵያን
ድንበር አፍራሽ ኃይል ሆነ. ሕዝቡን ብቻ ሳይሆን አጎራባች አገራትን ሰላም ነሳ፡፡ በኢትዮጵያዊነያን ላይ የሌላ አገራት ወታደሮች የማያደርጉትን
ኢሰብአዊ ድርጊት እየፈጸመ ነው፡፡ ይልቁንም እምነቱን “በኢየሱስ ብቻ” ላይ ባደረገው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ልጣኑን ከጨበጠ ወዲህ
ምድሪቱ የአመጸኞች፣ የሌባ ግብረ አበሮች፣ ጉበኛች፣ የነፍስ ገዳዮች መኖሪያ ከመሆንዋም ባለፈ ስደተኞች፣ ተፈናቃዮች፣ እስረኞች፣ በግፍ
የተገደሉ ወገኖች በዙ፡፡ ታዲያ እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል፡፡ ለምንስ በእኛ በኢትዮጵያዊያን ላይ የማታ ማታ የዘመኑ ማብቂያ ዋዜማ ግፉና
መከራው ለምን በዛ? ጠላቶቻችንስ እነማን ናቸው?
በፋሺሽት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ከጠላት ጋር በመቆም የሞራል ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ አገራት እንደ አሜሪካ፣ በእግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በሶቪየት
ህበረት፣ ቻይና መንግሥታት ዛሬም አገርን ለማፍረስ ለተነሳው ለህውሃት/ኢህአዴግ መንግሥት ድጋፋቸውን ከመለገስ አልተቆጠቡም፡፡ ለዚህም
ምስክሩ የኃይለ ሥላሴ የቅርብ አማካሪ የነበሩት በአሜሪካዊው ጆን ሐዛወይ ስፔንሰርን የተጻፈው 1ኛ ጥርስ የገባች አገር መጽሐፍ ትርጉም
መንግሥቱ ኃ/ማርያም አርአያ(ሌ/ኮ) እና በመዝገቡ ምትኬ ቢልልኝ፣ 2ኛ የአክሊሉ ማስታወሻ መጽሐፍ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ እና 3ኛ
ሌሎችን መጽሐፍት በድረ ገጾች መመልከት ነው፡፡ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ ሆን ብለው ላደራጁት ህውሃት በሬገን አስተዳደር ዘመን
በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ተመድቦለት ይንቀሳቀስ እንደነበረና አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም በመንግሥትነት እውቅና ለመስጠት ከላይ
የተጠቀሱ አገራትን የቀደማቸው አገር የለም፡፡ በ1997 ዓ.ም ለሁለት መቶ ኢትዮጵያዊያን መገደል፣ ለሺህዎች ለሚቆጠሩ አካለ ስንኩላን መሆን፣
ለብዙ ሺህ ወገኖች መታሰር፣ መሰደድ የአሜሪካ እና እንግሊዝ መንግሥታት በተመለመሉ ኢትዮጵያዊያን ሴራ የተፈጸሙ ስለመሆናቸው ጥርጥር
የለውም፡፡ ያ የኢትዮጵያዊያን እልቂት እየበዛና እየሰፋ መጥቶ በምድሪቱ ባሉ ቤተሰቦች ሁሉ እየተከሰተ ነው፡፡ አሁን እየታየና እየተሰማ ያለው
መከራና ስቃይ የሚያቆመውም ኃይል የለም፡፡ የህውሃት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ካድሬዎች፣ ኃያላን የምንላቸውም መንግሥታትም ቢሆኑ፡፡
ለዚህም ምክንያቱ ብዙዎች የአርማጌድዮን ጦርነት የሚካሄደው በእስራኤል ነው ቢሉም ጅማሬው በእኛው አገር በኢትዮጵያ መሆኑንና አሁንም
የኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ሁላችን ብናውቀውም ባናውቀውም መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ነን፡፡ የዚህ ዓለም ገዥ ተብሎ የተጠራው ሉሰፈር (ሰይጣን
) ጠላቶቻችንን እያስቀደመ በዓለም የቀረችውን ኢትዮጵያን (ጽዮንን) ለመያዝ እዬደረገ ያለ ጦርነት ቢሆንም አሸናፊዎች ስለመሆናችን አስቀድሞ
መዝሙር 125፡3 “የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም” ተጽፎልናል፡፡ ቀድሞ እግዚአብሔርን በሚመሩ
ሰዎች ያልተደፈረችው፣ ዛሬ በከሃዲዎች እጅ ወድቃ መፈንጫቸው ሆናለች፡፡ ሰይጣን መለያው ያደረገው ቁጥሩ 666 እንደሆነ እና በእውነተኛ
ኢትዮጵያዊያን መካከል መለያ ዓርማም የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መስቀል ነው፡፡ ማነው እውነተኛው ኢትዮጵያዊ ከተባለም ዛሬ ኢትዮጵያን
በማስተዳደር ላይ ያሉትን ሰዎችና ድርጅቶቻቸውን የሚቃወሙ ሁሉ ናቸው፡፡ ሰይጣናዊ ሴራ በዓለም ላይ እያካሄዱ ያሉ እነማን መሆናቸውንም
ለማወቅ በድረገጽ The United States and Great Britain in Prophecy by John Ogwyn እና በኢትዮጵያዊ የተለቀቀውን “ሉላዊ ሴራ –
የታሸጉ ታሪኮች” www.antiglobalconspiracy.com እና በወንጌል ራዕይን በማንበብ ከፀረ ክርስቶስ መንፈስ አገዛዝ / አል,መሲህ አድ
ዲጃልማምለጥ ይቻላል፡፡
በዓለም ዙሪያ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን አርሜጌዶን ጦርነት (የመጨረሻ ጦርነት) በተመለከተ ጅማሬውም መጨረሻውም በእስራኤል
እንደሚሆን ነው፡፡ ለዚህም ምክንያታቸው በዓረብ አገራት መከበብዋና እያደረሱባት ያለውን ጦርነት በመመልከት ነው፡፡ አባባላቸው በወንጌል
ብንመለከት ከእስራኤል ይልቅ ኢትዮጵያ ናት የተከበበችው፡፡ የእስራኤል ባለሥልጣናት ከሕዝባቸው ጋር እስራኤልን በተመለከተ አንድነት
አላቸው፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ ድንበርን እየሰፈራረሰ፣ ምድሪቱን ከሕዝቡ እየነጠቀ ለባዕዳን እየቸበቸበ ነው፡፡ ተግባሩን እየቃወሙ ያሉትን
እየገደለ፣ እያሰረ ነው፡፡ ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ የሚየወጣውን ወንጌል እስራኤል በአገር ደረጃ ስላልተቀበለች የወንጌል ተቃዋሚ መንፈስ
ከእስራኤል ሕዝብና መንግሥት ጋር በመንፈሳዊ ጉዳይ ለጊዜው ጸብ የለውም፡፡ ኢትዮጵያ ግን እነርሱ እምቢ ያሉትን ወንጌል በኢትዮጰያዊው
ጃንደረባ በኩል በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ከተቀበለች ጀምሮ ሰይጣንና አጋንንቶች በወኪሎቻቸው በኩል ነዋሪዎችን ማጣላት ማሰቃየት
መግደል የዘወትር ጉዳያቸው አድርገው ዘልቀው በኋላም የነቢዩ ሙሐመድ አገልጋይ ነበር ተብሎ በሚነገርለት በኢትዮጵያዊ ቢላል አል ሀበሽ
በኩል ወንጌልን ከቀይ ባህር ማዶ ላሉ ጣዖታት አምላኪ ለነበሩና አሁንም ለሚያመልኩ ዓረብ አገራት ሕዝቦች በነቢዩ ሙሐመድ በኩል ቁርኣን
(ወንጌል) መዳን ዒሳ በኩል እንደሆነ ተነግሮአል፡፡ ዛሬ በዓለም ዙሪያ እየተሰበከ ስለአለው ኢስላም ሃይማኖት (ሲኒ፣ ዋሃቢ እና ሺያህ) በነቢዩ
ሙሐመድ የመሠረተ ሳይሆን እሳቸው ከሞቱ በኋላ እርሳቸውን እና የእርሳቸውን መልዕክት ሰምተው ያመኑ ቤተሰቦችን ያሳድዱ ከነበሩት
ቤተሰብ የተወለዱ ሰዎች ያቋቋሙት ነው፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ ነገሥታት ሥር ብትሆንም በነቢዩ መሐመድ በኩል ቁርኣን (ወንጌልን) ሰምተው
የተቀበሉ ወገኖችንና ቤተሰቦችን ጥገኝነት መስጠትዋና እና ማስተናገድ ከጀመረች ጀምሮ በዓረብ አገሮች ዘንድ ሙስሊም ነህ ክርስቲያን ተብሎ
የማይጠየቅበት ጥላቻ፣ እስራትና ግድያ ተፈጽሞብናል፣ እየተፈጸመብን ነው፡፡ ለዚህም ዋና ምክንያቱ ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት የተጣሉት
ሳጥናኤል እና ግበረ አበሮቹ በምድር ላይ ለመኖር ሰው ስለሚያስፈልጋቸው በመጀመሪያ ሔዋንን አታሎ ወደ አዳም እንደሄደ ሁሉ፣ ዛሬም
የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ሙሽራይቱን፣ ቤተ ክርስቲያንን (የወንጌል አማኞችን ያቀፈች) ለማታለልና የራሱ ለማድረግ በአለው ኃይሉ
በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መጥተውብናል፡፡ ሙስሊም ወገኖችም በአልበገሬነት በመነሳታቸው፣ ቤተ ክርስቲያንም አንገዛም እያለች በመሆንዋ ድሉ
የእኛው በደርግ፣ በህውሃት/ኢሕአዴግ ለተጠቁ ቤተሰብ ነው፡፡ ቀጥሎም የመጨረሻውን ውጊያ ለማድረግ ጉዞው ወደ እስራኤል እንደሚሆንም
እና ፍጻሜውም ምን እንደ ሚመስል በብሉይ ኪዳን፣ በአዲስ ኪዳንና በቅዱስ ቁርኣን በግልጽ ተጽፎልናል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊመጣ ካለው የከፋ መከራ ማምለጫው በአንደኛው ክፍለ ዘመን በጃንደረባው ኢትዮጵያዊ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገባውን
ወንጌል ሰምቶ መታዘዝ ነው እንጂ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአጋንንቶች እገዛ በሰዎች ጥበብ የተጻፈውን የማርያም እና የመላዕክት አማላጅነት
መከተል አልተቆጠቡም፡፡ ሰይጣንም መላዕክትን ፈርቶ እንደማያውቅና ጦርነትም እንደገጠማቸው በብዙ ቦታዎች ተጽፎልናል፡፡ ዛሬም
የምንማጸናቸው መላዕክት ከክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ጥቃት ሊያስመልጡ አይችሉም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል “በእናንተ ውስጥ ያለው ከሁሉ
ይበልጣል” ተብሎም የተጻፈልን ከፈሪሳዊያን እና ግብረ አበሮቻቸው ብቻም ሳይሆን አሁን ላለንበት መንፈሳዊ ጦርነትም ስለሆነም ነው፡፡
“ኢየሱስ! ኢየሱስ!”Ύ በማለት ብቻ ከሚመጣው ከእግዚአብሔር ቁጣ እንደማያስመልጥ “በስምህ አጋንንትን አላወጣንም”Ύ ባሉት ጊዜ
“አላውቃችሁም፣ ለሰይጣንና ለተከታዮቹ ወደ ተዘጋጀው ሲዖል ውረዱ” መባሉ ዛሬም በልማት ስም ቤተ ክርስቲያንን እና መስኪድን እያቃጠለ፣ እያፈረሰና እያሸገ ላለ መንግሥት ድጋፍ መስጠት በሰማይም ሆነ በምድር ከመጠየቅ አያስመልጥም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን የወንጌል ባለ አደራ
ሆነን ሳለ በሰንካላ ምክንያትና በድንቁርና ምድራችን በዲሞክራሲ ስም የአጋንንቶች ልጆች መጨፈሪያ መሆንዋን መረዳት ተስኖናል፡፡
በመጨረሻው ዘመን ላይ መሆናችን ምልክቶቹ በሙሉ እየታዩ ናቸው፡፡ የቀረው ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ ምድር ለመጨረሻ ጊዜ ሁከቱ ተቀጣጥሎ
ያለውን ሥርዓት ማስወገድ ብቻ ነው፡፡ ይህም የእኛ የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ስለሆነ መንግሥታትን መማጸን ሳይሆን ኃይል ያነሰው ለመቀበል፣
የፈራም ብርታት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ብቻ ነው፡፡
ቀድሞ የፀረ ክርስቶስ መንፈስ በኢትዮጵያዊው ናምሮድ (ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ) አድሮ የባቢሎንን ግንብ አስገንብቶ እንደነበረና እንደፈረሰበት
ሁሉ ዛሬም ያ መንፈስ በህውሃት መሪ አቶ መለስ አድሮ የነበረው እርኩስ መንፈስ በሰባት እጥፍ በአቶ ኃይለማርያ የወንጌል አማኝ ነኝ፣ ወንጌልን
ጠንቅቄ አውቄአለሁ፣ የሕይወቴ መመሪያ አድርጌ ተቀብያለሁ ደግሞም አምኜበታለሁ የሚል ምሁር ተሸጋግሮ የቀሩትን ጥፋቶች እየሠራ ቢሆንም
ፍጻሜው እጅግ የከፋ እንደሚሆን መገመት አያቅትም፡፡ 1 ዮሐንስ መልእክት 4፡16; «ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ
ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? ደግሞም በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 : 4 -7 “ደግሞ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤
ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት
ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል”Ύተብሎ እንደተጻፈ
ከተስማማን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ደጋፊዎች ወንጌላዊ መሪያቸውን በየትኛው ብድብ ሊቀመጥ ነው?
 “የክርስቶስን ሐዋሪያት ለመምሰል ራሳቸውን የሚለዋውጡ ሐሰተኞች ሐዋሪያትና አታላዮች ሠራተኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ሰይጣን ራሱን የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል፡፡ እንግዲህ የእርሱ አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሰል
ራሳቸውን ቢለውጡ የሚያስገርም አይደለም፣ ፍጻሜአቸው እንደ ሥራቸው ይሆናል” 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡13-15
ካሪዝማ መጽሔት ልዩ እትም 2005 ዓ.ም “ጠቅላይ ሚ/ር መለሰ ዜናዊ በሞቱ ማግስት በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዘመነ መንግሥት አምስት
የፕሮቴስታንት አማኞች ማምለኪያ ጣቢያዎች እንዲፈርሱ መደረጉ”፣ ጋዜጦችም “ምድራችን በዙምቢዎች ተወራለች” ማለታቸውን በዘፍጥረት 5
የተጠቀሱት የቃየል ዝርያ ኔፊሊም (www.Nephillim.org/youtube) አሁንም በምድር ላይ መራባታቸው አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን
በህውሃት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች ዘንድም በተግባር እየታዩ ነው፡፡ ደግሞም በዳንኤል 8፡23 “በስተ መጨረሻው ዐመጾች ፍጹም እየከፉ ይሄዳሉ፣
አሰቃቂ ጥፋት ይፈጽማል፣ ታላቅ አድርጎ ራሱን ይቆጥራል፣ በሰላም ተደላድለን ተቀምጠናል ያሉትን ከመኖሪያ ቀያቸው ያፈናቅላል፣ ቤቶቻቸውን
ያፈርሳል፣ ንብረታቸውን በእሳት ያጋያል፡ ጥፋት ሁሉ ይከናወንለታል” የተባለው ወንጌልን (ክርስቶስን) በተቀበለች አገር በኢትዮጵያ መሆኑ
አንባቢ ቢረዳውና እንደ ነነው ሰዎች ንስሃ በገባ ነበር፡፡ ምን ያደርጋል ዘመኑ ወደ ፍጻሜው እየቸኮለ ሳለ፣ ሰይጣንም የተለያዩ ጥቅሞችን ለቤተ
መቅደስ ጠባቂዎች በመስጠት እያዘናጋ መሆኑን ለመጠቆም ነው ይህ መልዕክት መጻፍ ያስፈለገው፡፡
ታዲያ እንዴት መጽሐፍ ቅዱሱ ቢተረጎም ነው የነፍሰ ገዳዮች ቡድኖች ጥርቅሞች፣ በኢየሱስ ብቻ አማኝ መሪነት መጽሐፍ ቅዱስንና ቅዱስ
ቁርኣንን ያቃጠሉ፣ ቤተ ክርስቲያናትን እያፈረሱ፣ ሙስሊሞች ለፈጣሪያቸው የምስጋና መስዋዕት እንዳያቀርቡ ዓርብ ዓርብ በእጅ አዙር እያወኩ፣
ገበሬው የራሱን መሬት እንዳያርስ እየተነጠቁ፣ በአገርም እንዳይኖሩ እያሳደዱ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶም ቤተ ክርስቲያን ዘንድም አንድነት
መጥፋቱ፣ ዳግም ልደት አግኝተናል ባዮችም ዘንድ በመንፈስ መደማመጥ የመጥፋቱ ምክንያት የነፍስ ገዳይ መንፈስ አገሪቱን በሙሉ በመቆጣጠሩ
ነው፡፡ ማስረጃውም ህውሃት/ኢህአዴግ ዓርማ የሆነው ጨርቅ አዲስ አበባ በሚገኘው ከእስጢፋኖስ ከቤተ ክርስቲያ መስቀል በላይ ሰቅሎ ዛሬ
መታየቱ ነው፡፡ ነገ በቤተ መቅደስ ተገኝቶ እኔው ነኝ ስገዱልኝ ለማለት የሚከለክለው እንደሌለ ነው የሚያስመሰክረው፡፡ እንዲያ መሆኑን
እየታወቀ ኢትዮጵያ ዳግም ልደት አገኘ መሪ እግዚአብሔር ሰጣት ብላችሁ ደስታችሁን የገለጣችሁ፣ ብዕራችሁን ያሾላችሁ፣ የእልልታም ድምጽ
ያሰማችሁ ሁሉ ለአጥፊው ሰው ድጋፍ መስጠታችሁ በምድሪቱ እሰከ ዛሬ ለፈሰሰው፣ ወደፊትም ለሚፈሰው ንጹህ ደም ተጠያቂ መሆናችሁን
አታውቁምን? የወንጌሉ አርበኛ ሐዋሪያው ጳውሎስ የእስጢፋኖስን ነፍሰ ገዳዮችን ልብስ በመጠበቁ ተጸጽቶ ንስሃ እንደገባ ሁሉ ከእናንተም
የሚጠበቀው ከአጥፊ መንግሥት ራሳችሁን አግልላችሁ ንስሃ እንድትገቡ ነው፡፡ ይህም ነገ ሳይሆን አሁን ነው፡፡ ነገ የእናንተ ሊሆን አይችልምና፡፡
 1ዮሐንስ 2፡18 በመጨረሻው ሰዓት የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል፣ አሁንም እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፣ የመጨረሻው
ሰዓት እንደ ሆነ የምናውቀው በዚህ ነው፡፤ ከእኛ መካከል ወጡ፣ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ አይደለም
ብሎ ከሚክድ በቀር ሃሰተኛ ማነው? ይህ አብንና ወልድን የሚክደው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፡፡
ጠ/ሚሩ ኢየሱስን በመጥራቱ ደጋፊዎቹ ቢበዙም፣ ክርስቶስን በመካዱና ከኢትዮጵያዊያን ጠላቶች ጋር በማበሩ ግን ጥቂቱን አንገት አስደፍቶአል፡፡
“ሐዋሪያት፣ ኢየሱስ ብቻ”Ύእምነት መሠረቱ ከወንጌል ስብከት እና ከቅዱስ ቁርኣን አስምሮ በእጅጉ ያፈነገጠና ለእግዚአብሔር ቃል የማይገዙ
ሰዎችን ያቀፈ ሃይማኖት መሆኑን ብቻም ሳይሆን በዋናው በአጋንቶች አለቃ የሳጥናእል የሚመራ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፡፡ ስለሆነም
ለዘመናት በኢትዮጵያዊያን መካከል ሃይማኖትን መሠረት አድርጎ ደም ሲያፋስስ የዘለቀው ሰይጣን በግለሰብ ደረጃ ማብቂያው የሚሆነው
ኢስላሙ በክርስቲያኑ፣ ክርስቲያኑም በኢስላሙ ላይ ጥላቻ እንደማይኖው ማረጋገጫው ለሁለቱም የእምነት መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ
ቁርኣን ውስጥ የተጻፈውን ያለ ተጽዕኖ አንብቦ ሲረዳው ብቻ ነው፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ቃልም ስጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ ተብሎ እንደተጻፈ፣
በቅዱስ ቁርኣንም በመርየም 19፡30፣34 “ዒሳ የአላህ እውነተኛ ቃል ሆኖ በመንፈስ ወደ መርየም ተልኮ በተዓምር ሰው ሆኖ መወለዱን፣
አልመሲሕም (ክርስቶስ) ተብሎ እንደ ተጠራም፡፡ በአል-ዡኽሩፍ 43፡63 በአላህና በመልዕክተኛው አልመሲህ ዓሳ (በኢየሱስ ክርስቶስ) ያላመነ
የገሃነም እሳት እንደሚጠብቀው”Ύደግሞም በአል-ሐዲድ 57፡7 ፣ በአል-ሙልክ 67፡29፣ በአል-ኒሳእ 4፡171 በግልጽ ተጽፎአል፡፡ በወንጌል ውስጥ
ትልቁ ሥፍራ የያዘው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ሁሉ በቅዱስ ቁርኣንም ከነቢዩ መሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ስም የበለጠ በብዙ ምዕራፎች ውስጥ
ተጽፎ ያለው የአልመሲህ ዒሳ ስም ነው፡፡ አሁን ምድሪቱ በአጋንቶች፣ ኢብሊሶች፤ በዙምቢዎች የተሞላች ብትሆንም የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ
መንፈስ፣ አል,መሲህ አድ ዲጃል የተሞላው ሰው ምልክቱም በሃዲስ እንደተጻፈው በተግባርም የእምነትን ተቋማት የሚጻረር መሆኑን እያየን ነው፡
የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናምሮድ በገዛ አገሩ እንዳልተገለጠ ሁሉ ሁለተኛውም ናምሮድ በኢትዮጵያ እንዳይገለጥ የሚከለክለው በመዝሙር
125፡3 “የክፉዎች በትረ መንግሥት፣ ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም” የምትለዋ ቃል ናት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በሚመሩ የቤተ
ክርስቲያን ሰዎች እምቢ ባይነት ነው እንጂ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በተካተተው አስተምሮ “ለመሪዎቻችሁ ጸልዩ፣ ሰይፍ የሚያነሳው አጥፊውን
ለመቅጣት ሥልጣን ተሰጥቶታል” የምትለዋ አይደለችም፡፡ በውዳሴ ማርያምስ ተመርቶ አይደለም እንዴ በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ዘርዓ ያዕቆብ
የወንጌል አማኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ የፈጀው፡፡ ዛሬስ እየተደገመ ያለው ያው አይደለም እንዴ? ሕዝበ ክርስቲያን የዘመኑ መጠናቀቁን ለማወቅ
ይረዳህ ዘንድ ሂሳቡን ማስላት ነው፡፡ እስራኤላዊያን ከባቢሎን መልስ ቅጥሩ ለመስራት ወደ እስራኤል የገቡት 538 ዓመተ ዓለም (BC) ሲሆን
አሁን ያለነው 2013 እ.ዘ.አ (538 +2013 = 2550 = 1260 +1290 = 7 ዓመት = 3½ +3½) የዳንኤል እና የዮሐንስ ራዕይ መመልከት ነው፡፡
በዳንኤልም “በስተመጨረሻ አመጸኞች ፍጹም እየከፋ በሚሄዱበት ጊዜ አለቃው ከብዙዎች ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፣ በእኩሌታው መሥዋዕትና
ቁርባን ማቅረብ ያስቀራል፡፡የታወጀው ፍርድ በእርሱ ላይ እስኪፈጸም ድረስ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደስ ውስጥ ያቆማል፡
፡ መንግሥት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማየታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል እንደ ተባለ “ኢትዮጵያ ከመከራዋብዛት እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ግድ ስለሆነ ስለ ሕዝባችን እና አገራችን በተመለከተ መልካሙንም
ማየት እንፈልጋለን የምንል ሁሉ ንሥሐ (ቃልህን ትተን የሰዎችን ፍልስፍና በመከተል አሳዝነናልና ይቅር በለን) መግባት ይጠበቅብናል፡፡ ያ
ካልሆነ ግን ኢብሊሶች፣ ጂኒዎች ቀድሞ ነቢዩንና ተከታዮቻቸውን የገደሉ የአላህን ብርሃን በአፋቸው ሊያጠፉ የሚሹ የመካ ከሓዲዎች ግብፅን፣
ሱዳንን፣ ኢራቅን፣ ኢራንን እና ሌሎችንም በማስተባበር የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አል,መሲህ አድ ዲጃል የተሞላው ሰው በቅዲስቲቱ
አገር በኢትዮጵያ ማንገሥ ነው፡፡ አሁንም በመካከላችን ስለሆነ የሚከለክለው አንዳች ነገር ሳይኖር እግዚአብሔር በቸርነቱ የዋሆችን እየጠበቀ
ነው፡፡ የጸሐፊው ተልዕኮ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የዘነጉትን ለማስታወስ ነው፡፡
 ዮሐንስ 6፡51 እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፣ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም፡፡
 አል-ማኢዳህ 5፡ 46 በነቢያት ፈለግ ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን አስከተልን፣ ኢንጂልንም
በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆች መሪና ገሳጭ ሲሆን ሰጠነው፡፡
 አል-አንዓም 6፡104 ከጌታችሁ እንደ ብርሃኖች በርግጥ መጣላችሁ፣ የተመለከተም ሰው ጥቅሙ ለነፍሱ ብቻ ነው፣ የታወረም ሰው ጉዳቱ
ለራሱ ብቻ ነው፣ እኔም በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም፡፡
 መርየም 19፡15፣ 33 በUUተወለደበት ቀንና በሚሞትበትም ቀን ሕያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን፣ ሰላምም በእኔ ላይ
ነው በተወለድሁ ቀን በምሞትበትም ቀን በምቀሰሰቀስበትም ቀን
 ራዕይ 1፡ አትፍራ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፣ ሞቼ ነበር እነሆ አሁን ከዘለለም እስከ ዘላለም ሕያው ነኝ፡፡
 አልዡኽሩፍ 57፣ 61 የመርየም ልጅ ምሳሌ በተደረገ ጊዜ ከሃዲዎች በርሱ ይስቃሉ፣ እርሱም ለሰዓቲቱ ማብቂያ ምልክት ነው
 ሰይጣን የሚፈልገው ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፣ አላህን ከማስታወስና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡
የእኛ የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በብሉይ ኪዳን በ1ኛ ሳሙኤል 8፡5-18 የታጸፈውን ይመስላል፡፡ ይህም እስራኤላዊያን መሪያቸው ሳሙኤልን “አንተ
አርጅተሃልና እንደ ሌሎች ሕዝቦች የሚመራንን ንጉሥ አንግሥልን” በማለታቸው ሳዖልም ለአርባ ዓመት ሕዝቡ እያስከፋና እግዚአብሔርን
እያሳዘነ ቆይቶ በውርደት ከሥልጣኑ ተሸሮ በመጥፎ አማሟት ከሞተ በኋላ እግዚአብሔርም ቃል ኪዳኑን ለመጠበቅ ሲል የበግ እረኛ የነበረውን
አንዳነገሰና ሕዝቡም ወዶት እንደተገዛለት ተጽፎልናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም እግዚአብሔር ከሾመው እኛ የመረጥነው ይሻለናል ቢልም አፈ
ጮሌውና ጨካኙ ደርግ በትረ ሥልጣኑን ጨብጦ ያስከተለው የክህደት መንፈስ እልባት ሳያገኝ ከ18 የሰቆቃ ዓመታት በኋላ የአሜሪካ እና
የእንግሊዝ መንግሥተት በመጡለት በአቶ መለስ ዜናዊ እጅም ለ21 ዓመት ቀኑ ምነው ቶሎ በነጋ፣ ምነው በጨለመ እስከሚል ድረስ ቁም ስቃይ
አይቶ በሞቱ ቢገላገልም በቀሪዋ ዓመት ሳያገመግም እነሆ በወንጌል አርበኛ በአቶ ኃይለማርያም በሁኔታው ከእሳቱ ወደ ረመጡ ሆኖበት፡፡
ለዚህም በአቶ መለስ የታሰበው ጥፋት ቀጣይነት ያገኝ ዘንድ እንደሆነም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሳይጠቅሰው ያለፈበት ስብሰባ የለም፡፡ አቶ
መለስ በነበረው ገዘንብ በዘመናዊ የሕክምና መሳሪያ እድሜውን በማስረዘም የወጠነውን የጥፋት ተግባራትን ወደ ፍጻሜ ባመጣ ነበር፡፡ አካሄዱ
ምንም እንኳ በክፉ መንፈስ ተመርቶም ቢሆን ማስፈጸሙ የእርሱ ድርሻ አልነበረም፡፡ አሁንም የህወሓት ባለሥልጣናት ሁኔታው እንዲፋጠን
ከማድረግ ያለፈ የሚፈይዱት ሥራ የለም፡፡ ሁሉም በክህደት መንፈስ ተሞልተው መጽሐፍ ቅዱስንና ቅዱስ ቁርኣንን ያቃጥሉ እንደ ነበረ በድረ
ገጾች አንብበናል፡፡ ስለሆነም አስፈጻሚው ግብረ ኃይል መምጣት ስላለበት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማኝ ተብሎ ወንጌልን ጨብጦ የሟች
መለስ ዜናዊን ሌጋሲ አስፈጽማለሁ ብሎ በሙሉ ልቡ በድፍረት ተናገረ፣ ሕዝቡም እግዚአብሔርን የሚፈራ መሪ አገኘን ባለበት ማግሥት በሟች
መንፈስ ተነሳስቶ ሁኔታው ወደ ከፋ ጥፋት ፈጠነው፡፡ አሁን በአቶ ደሳለኝ የግዛት ዓመት ውስጥ ተወደደም ተጠላ በመከራ ውስጥ ማለፋችን
የማይቀር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምሁራን ዘንድ በናፍቆት የተጠበቀውና ለብዙ ወንድሞችችንና እህቶቻችን ሕይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው ዲመን
ክራሲ demon-bureaucracy ተዘርቶ ሳይበቅል ይዞአቸው መክሰሙ ነው፡፡
አቶ ኃይለማርያም የሚከተለው ሃይማኖት ሐዋሪያት ኢየሱስ ብቻ Only Jesus መሆኑን የሃይማኖት ሰዎችም የወንጌል አማኞች የሚያውቁት
ጉዳይ ቢሆንም ጥቂት ሃማኖቱን በተመለከተ እዚህ ላይ ለአንባቢ ማሳወቅ ግዴታ ነው፡፡ ኢየሱስ ብቻ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን እናውቃለን፣
አምልኮና ስግደት የምንሰጠው ግን ለኢየሱስ ብቻ ነው ባዮች ናቸው፡፡ ይህም “ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ
አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከካደ በቀር ሃሰተኛ ማነው? ይህም አብንና ወልድን የሚክደው የክርስቶስ ተቃዋሚ እርሱ ነው” ይለናል፡፡ ጠ/ሚሩ
በጸረ ክርስቶስ መንፈስ የሚንቀሳቀስ አይደሉም የሚልም ካለ በሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉት ግድያዎች
“በሥራዎቹ ታውቁታላችሁ” እንደተባለው እያወቅነው ነው፡፡ የኢየሱስ ብቻ ተከታዮች መመሪያቸው ውስጥ አንዱና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር
የሚጋጨው “አንድ ሰው በጥምቀት አምኖ ኃጢአት ቢሠራ ኀጢአተኛ አይባልም፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ያለፈውን ያሁኑንና የወደፊቱን ኃጢአት
አስወግዶአል፣ እኛ የዳነው ለአንዴና ለሁሌም ነው” የሚለው ነው፡፡ ምንጩም “በዕውኑ በውሃና በመንፈሱ እንደገና ተወልዳችኋልን?” በፖውል
ሲጆንግ ፣ ትርጉም በአብርሃም ተመስገን፡፡
 በሮሜ 8፡7 ለኃጢአት የተገዛ አእምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ጠበኛ ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፡፡
 2 ተሰሎንቄ 2፡3-12 ማንም ሰው በምንም መንገድ አያታላችሁ፣ አስቀድሞ ዐመፅ ሳይነሳ፣ ለጥፋት የተመደበውም የአመፅ ሰው ሳይገለጥ ያ
ቀን አይመጣምና፡፡
በሥልጣን ላይ ያለው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በእውነት የወንጌል አማኝ ቢሆን ኖሮ ህወሃት/ ኢህአዴግ ያሠራቸውን ወንድሞችና እህቶችን
በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ቀርበው በገለልተኛ ዳኞች ጉዳያቸው ታይቶ በተፈቱም ነበር፡፡ የሟቾች ቤተሰብንም ይቅርታ በጠየቀ ነበር፡፡ እንዲያ
ከማድረግ ይልቅ ግድያውና እስሩ ተባብሶአል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በመለስ ዜናዊ ይሠራ የነበረው መንፈስ በሰባት እጥፍ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ
ምስክሮቹም
 አቶ በረከት ስምዖን “የነባሩ ልምድ ወደ አዲሱ እንዲተላለፍ ለማድረግ እድል የተገኘ ይመስለኛል”
 ወ/ሮ አዜብ መስፍንም የባለቤታቸውን ራዕይ “ሳይበረዙና ሳይከለሱ ማስፈፀም ነው”
 ጠ/ሚሩም በቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ወቅት ባሰማው ንግግር ሳይጨመር እና ሳይቀነስ የመለስን ሌጋሲ እንደሚያስቀጥል መደመጡ ናቸው፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሰ ያለው የሐሳቹ መንፈስ (666) ሃይማኖትን፣ ኢኮኖሚን ፣ ሚሊቴሪውን ይዞ በአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ
እንደሚገለጥ ማሳያው፣ እርሱ በህውሃት/ኢህአዴግ ከተመረጠ በኋላ በየትም አገር ተደርጎና ተሰምቶ የማይታወቀውን ሦስት ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስቴሮች 666 የሚወክሉ መሾሙ ከላይ የተጠቀሱትን የማህበረሰብ አውታሮችን በበላይነት በመምራት ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ነው፡፡
በሃይማኖት በኩል አዲሱ ፓትሪያርክን በተመለከተ 6ኛው መሆኑ ብቻም ሳይሆን በምእመኑ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑና ተጠሪያቸውም
ከሦስቱ ለአንዱ ምክትል ጠ/ሚር ነው፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን የተሰጠው ማስጠንቀቂያ በመጀመሪያ ወንጌልን እንደ ተቀበልነው
ሁሉ ተግባራዊ ባለማድረጋችን ቅጣቱም በእኛ እንደሚጀመር ማሳያው ዘካሪያስ 13 “መንጋውን ለሚተው ለማይረባ እረኛ ወዮለት…”
እንደተባለው ነው፡፡ አሁን በምድሪቱ እየተካሄዱ ያሉት ክፋቶች ብቻም ሳይሆን ሕዝቡን በማስጽናናት አንድነትም እየታየ ነው፡፡ በጨለማ ውስጥ
በጭላንጭልም ቢሆን ብርሃን እየበራም ነው፡፡ የዘመኑ ወደ ፍታሜ ላይ መገኘታችንን ከላይ የተጠቀሰ ቢሆንም ዓለም ፈጽማ ትጠፋለች ማለት እንዳልሆ አንባቢ እንዲያስተውለው በያስተውል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 20፡23 ሐዋሪያቱን ሰብስቦ “የአሕዛብ ገዥዎች
በሕዝባቸውን ላይ ጌቶች እንደሚሆኑ፣ ባለ ሥልጣኖቻቸውም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ፣ በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን
የአለበትም ከእናንተ ታልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፣ የበላይ ለመሆን የሚሻም የእናንተ የበታች ይሁን” ያለውን አይነት አስተዳደር
ኢትዮጵያ ስለሚጀመር፣ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎቻቸው በሞት ካልተለዩ በምድሪቱ እንደማኖሩ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያዊያን
በዜግነታቸው በኢትዮጵ (ጽዮን) እንደማይኖሩ ነው፡፡ አንድ ሰው ለሁለት ኃያላን ጌቶች መገዛት አይቻለውም ተብሎ እንደተጻፈ፣ ዛሬ በገዛ ወገኑ
ላይ ግድያ ዘረፋ ከሚያካሄድ ኢህአዴግ ጋር የተበበረ ራሱ ግለሰቡ እንዳደረገው ስለሚቆጠር የሕይወት ድርሻውን በምርጫ ከጨለማው ገዥ
በማድረጉ የእግዚአብሔር በበራበት መኖር አይችልም፡፡ ይህም በብርሃን ውስጥ ጨለማ እንደማይታይ ነው፡፡ ክፈች ምድር ለመኖር ሰው ራሱን
በመከራ ውስጥም ቢሆን መዘጋጀት አለበት፡፡
በኢሳያስ ምዕራፍ 60 ደግሞ “ብርሃንሽ ወጥቶልሻልና፣ ተነሺ አብሪ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና፡፡ እነሆ ጨለማ ምድረን፣ ድቅድቅ
ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይወጣልሻል፣ ክብሩንም ይገልጥልሻል፡፡ ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ ነገስታትም ወደ ንጋትሽ
ጸዳል ይመጣል”፡፡ በመዝሙር 87 ደግሞ “የሕዝቦች እናት” መሆንዋን ብቻም ሳይሆን አሁን በቅርቡ የሚሆነውንም በምዕራፍ 132፡13-18
“እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወዶአታልና፥ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች
አድራለሁ። አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ። … ጠላቶቹንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ .. ተብሎአልና፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 21, 2013 @ 4:16 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar