www.maledatimes.com ህገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሞቱ አይፈቀድላቸውም!? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ህገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሞቱ አይፈቀድላቸውም!?

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ህገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሞቱ አይፈቀድላቸውም!?

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 30 Second

ትላንት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያምከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር የጠቅላይ ሚኒስተሩን መያዝ እና ምትካቸውን አስመልክቶ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። ዛሬ ደግሞ ተወዳጇ ዞን 9 ብሎግ “ባልቻን ፍለጋ”በሚል አንድ ወግ አስነብባናለች።

ሁለቱም እንደጠቆሙት በህገ መንግስቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱ ወይም ደግሞ በሆነ ምክንያት “ከጥቅም ውጪ” ቢሆኑ ማን ይተካቸዋል? እንዴት ይተካሉ? ለሚለው ጥያቄ ህገ መንግስቱ መልስ የለውም።

ህገ መንግስታችን አንቀፅ 34 ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ድርሻ በአንድ ገፅ ተኩል ያህል ይዘረዝራል። (በቅንፍ እናደንቃለን፤ ጠቅላያችን ይሄንን ሁሉ ኖሯል ሃያ አንድ አመት ሙሉ ሲሰሩ የኖሩት…?  መድከም ይነሳቸው እንዴ…!? አንዱ ስብሰባ ላይ ክልትው ብለው አለመቀረታቸውም በእውነቱ ብርታታቸውን ያመለክታል!)

በአንቀፅ 35 ላይ ደግሞ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የስራ ድርሻ ይናገራል። ቆይ እዝች ጋ ፍሬን ያዝ እናድርግ እና ህገ መንግስቱን እናንብብ፤

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤
1     በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል።
2     ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩ ጊዜ ተክቶ ይሰራል።

ከዛም በነጥብ ሁለት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል። ብሎ ያበቃል። እንግዲህ በተራ ቁጥር 2 ላይ ባለው መሰረት “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩ ጊዜ ምክትሉ ተክቶ ይሰራል።” የሚል ከመገለፁ ውጪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይበልባቸውና አንድ ነገር ቢሆኑ የሚተካቸው ሰው ማንነት አልተገለፀም።

አሁን በቅርቡ ግንባር መሆኑን ያሳወቀው መድረክ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ መሆን አለባቸው ስልጣኑን ሊረከቡ ይገባል ብሎ መጠየቁ ሲሰማ የኢህአዴግ ቀሪ ባለስልጣናት ህገመንግስቱን ጠቅሰው  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚተኩት ለአጭር ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩ ወቅት እንጂ ከናካቴው ሳይኖሩ ሲቀር አይደለም። ብለው መከራከራቸውን ሰምተናል። (ወሬ መቼም አይደበቅ!)

እሺ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱ ወይም አጓጉል ሆነው ቢቀሩ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሆናል። የህገ መንግስቱን  142 ገፆች ቢያገላብጡ ምንም ምላሽ የለውም። ስለዚህ በህገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት አይችሉም ማለት ነው?

ጉድ እኮ ነው!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2012 @ 5:13 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar