www.maledatimes.com የፀረ-ሙስና ሕግ ሊሻሻል ነው · የአክሲዮን ማኅበራት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የልማት ማኅበራት በአዲሱ የሙስና ሕግ ይካተታሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የፀረ-ሙስና ሕግ ሊሻሻል ነው · የአክሲዮን ማኅበራት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የልማት ማኅበራት በአዲሱ የሙስና ሕግ ይካተታሉ

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on የፀረ-ሙስና ሕግ ሊሻሻል ነው · የአክሲዮን ማኅበራት፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የልማት ማኅበራት በአዲሱ የሙስና ሕግ ይካተታሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 28 Second
በዘሪሁን ሙሉጌታ
     የፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕግ በወንጀል ሕጉ የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች እንደገና የሚደነግግ አዋጅ በማዘጋጀት አሁን እያስቀጣበት ያለውን ሕጋዊ ወሰን በማስፋት አዋጁን ሊያሻሽል ነው።
አዲስ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ ሕግ በዋናነት የግል ዘርፍ አካላትን በሙስና ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በመቶ ሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ሀብት እያንቀሳቀሱ ያሉ፣ የሕዝብ ሀብት የሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት ላይ ረቂቅ ሕጉ አተኩሯል። እነዚህ አካላት በማንኛውም አግባብ ከአባላቶቻቸው ወይም ከሕዝብ የተሰበሰበ ወይም ለሕዝባዊ አገልግሎት እንዲውል የተሰበሰበ ገንዘብ፤ ንብረት ወይም ሌላ ሀብትን የሚያስተዳድሩ ወይም የሚያንቀሳቅሱ አክሲዮን ማኅበራት በማኑፋክቸሪንግ፣ በእርሻ፣ በንግድ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትራንስፖርት፣ በፋይናንስ እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መካከል በአክሲዮን የተቋቋሙ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሐዋላ ተቋማት የሙያና የብዙሃን ማኅበራት ፌዴሬሽኖችና ኮንፌዴሬሽኖች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች፣ ኢንዶውመንቶችና የልማት ማኅበራት (ለምሳሌ አልማ፣ ኦልማ፣ ወዘተን) ያካትታል።
ሕጉን እንደገና ለማሻሻል ያስፈለገው ሙስናን የሚፀየፍ ኅብረተሰብ እንዲፈጠር የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም፤ በግል ዘርፍ የሚፈፀም ጉቦኝነትና ምዝበራ በሙስና ወንጀል የሚያስቀጣ በመሆኑ ሲሆን፤ አዲሱ ረቂቅ ሕግም ከሲንጋፖር፣ ከስዊዲንና ከደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ ሕጎች በመቀመር መዘጋጀቱም ታውቋል።
በአዲሱ ሕግ መሠረት ለሕዝብ ተብሎ የተሰበሰበ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ እና የሚያስተዳድሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ ማድረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በሕጉ ያልተካተቱ ሲሆን፤ ሌሎች የሕዝብን ገንዘብና ሀብት የሚያስተዳድሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት፣ እድር እና ተመሳሳይ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ማኅበራት አባላቱ እርስ በርስ የሚተማመኑና ለሙስና የመጋለጥ ዕድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ በሙስናውም ቀጥተኛ ተጠቂ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥቂቶች በመሆናቸውና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብት አነስተኛነት የተነሳ በሙስና ተጠያቂ በማድረግ ከሚድነው ሀብት ይልቅ ተጠያቂ ለማድረግ የሚባክነው ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ ከሕጉ ውጪ ተደርገዋል።
በአዲሱ የሙስና ወንጀል ረቂቅ ሕግ በግለሰብ ባለሀብት ወይም ባለሀብቶች የተቋቋመ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሙስና ወንጀል አይጠየቅም።¾

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar