www.maledatimes.com ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል በመስከረም አያሌው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል በመስከረም አያሌው

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል በመስከረም አያሌው

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 58 Second
የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው እና ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት፤ ፓርቲው ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያራዝም መንግስት በጠየቀው መሰረት የፊታችን እሁድ ያካሂዳል። መንግስት በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር መጠየቅ ይችላል የሚል ህግ በመኖሩ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ መወሰኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን በአፍሪካ ህብረት በዓል ወቅት ማካሄድ የተፈለገው ኢትዮጵያ በአሉን ስለምታዘጋጅ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብና ሚዲያው እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለሚሰሙት ጥያቄው ከፍ ብሎ ይሰማል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን መራዘም ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ገልፀዋል። “የችግሩ ባለቤትም ሆነ መፍትሔ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የሚጨቁነንም መንግስት እዚህ ነው ያለው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ሰልፉ በታሰበለት ቀን ቢካሄድ ጥሩ እንደነበር ገልፀው ቀኑ መቀየሩም ያን ያህል ለውጥ እንደሌለው ተናግረዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ በመራዘሙ በፊት ይሳተፋል ተብሎ ከታሰበው በላይ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉን በህጉ መሰረት ማስፈቀዱ እና ህዝቡም ጊዜ ወስዶ እንዲወያይበት በመደረጉ ከ100ሺ በላይ ሰዎች በሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሰልፉ የሚነሱት አራት ጥያቄዎች በመሆናቸው ህዝቡ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና የተነሱ ጥያቄዎችን የተመለከተ ብቻ እንዲሆንም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ፣ የእስልምናን እምነት ነፃነት በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ በሰላም ተመልሰው ካሳ እና ድጎማ ተደርጎላቸው ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እና በስራ አጥነት እና በሙስና ላይ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የሚሉ ጥያቄዎችን አንግበው ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።
ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ እና ቸርቸል ጎዳና አልፎ እስከ ድላችን አደባባይ ወይም ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሚደረግ ሲሆን፤ በእለቱም አጠቃላይ የሀገሪቱን ሁኔታ የሚገልፁ ንግግሮች እና መፈክሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል::ሰንደቅ ሪፖርት
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 11:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar