www.maledatimes.com ግዙፉ የአሜሪካ ጀነራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ፤ በሕዳሴው ግድብ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ጨረታ ላይ እየተሳተፈ ነው በፋኑኤል ክንፉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ግዙፉ የአሜሪካ ጀነራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ፤ በሕዳሴው ግድብ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ጨረታ ላይ እየተሳተፈ ነው በፋኑኤል ክንፉ

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on ግዙፉ የአሜሪካ ጀነራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ፤ በሕዳሴው ግድብ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ጨረታ ላይ እየተሳተፈ ነው በፋኑኤል ክንፉ

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 56 Second
 
የዓለም ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂን በግንባር ቀደምትነት የሚመራውና ከተመሰረተ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የሆነው ከአሜሪካ ኮርፖሬት ኩባንያ መካከል አንዱ የሆነው ጀነራል ኤሌክትሪክ (GE) በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ጨረታ ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ በአዲስ አበባ የጀነራል ኤሌክትሪክ ተወካይ ለሰንደቅ ገለጽ።
በኢትዮጵያ የጀነራል ኤሌክትሪክ ተወካይ አቶ መሐመድ ኢስማኤል በተለይ ለሰንደቅ እንደገለፁት፤ “የኢትዮጵያ መንግስት በዘረጋው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ዓይነተኛ ድርሻ በሚኖረው በሕዳሴ ግድብ ላይ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ለመሳተፍ እና የተጀመረውን የሕዳሴ ጉዞ ለማገዝ የአሜሪካው ኩባንያ ጀነራል ኤሌክትሪክ በሕዳሴው ግድብ ኤሌክትሮ ሜካኒካል የተለያዩ ክፍሎች ላይ ጨረታ እየተሳተፈ ይገኛል” ብለዋል።
“ጀነራል ኤሌክትሪክ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በሃይድሮ ፓዎር ስራዎች ረጅም ልምድ ያለው ከመሆኑ አንፃር በሕዳሴው ግድብ ላይ በሚዘረጋዋ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ላይ መሳተፉ ኢትዮጵያን ከፍተኛ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል። በተለይ ኩባንያው “smartsignal” ቴክኖሎጂ በመጠቀም በቀላሉ የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፉሎችን ለመፈተሸ የሚያስችል እና ችግሮች ሲገጥሙም በቀላሉ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀም በሕዳሴው ግድብ ላይ ሊነሳ የሚችል ማንኛውንም የደህንንነት ጥያቄ ሊያስቀር የሚያስችል አቅም ያለው ዓለም አቀፍ ተቋም ነው” ሲሉ አቶ መሐመድ ኢስማኤል ገልፀዋል።
በአሁን ሰዓት መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ባወጣው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል አንዱ በሆነው “Balance of plant switchyard autotransformer transformer” ጨረታ ላይ ጀነራል ኤሌክትሪክ እየተወዳደደረ ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ “የአሜሪካ ኩባንያ ጀነራል ኤልክትሪክ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ያሳየው እርምጃ በምን መልኩ ይታያል” ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ አንድ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ባለሙያ እንደገለጽት፤ “ጣሊያን፣ ቻይና እና ፈረንሳይ በተለያዩ ዘርፍ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ መሳተፋቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ጀነራል ኤሌክትሪክ የመሳሰሉ የአሜሪካ ኮርፖሬት ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ጨረታ ሂደት ውስጥ መግባታቸው የሚኖረው ትርጉም ብዙ ነው” ብለዋል።
ዲፕሎማቱ አያይዘውም፤ የኩባንያው መሳተፍ “በተለይ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ የሚናፈሱ አሉታዊ ተፅዕኖዎች መስመር ሊይዙ የሚችሉበት እድልን ያሰፋል። ይህም ሲባል የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምዕራቡን ዓለም ይሁንታ የለውም በሚል፣ ግብፅ እና ሱዳን በዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት ላይ የሚያደርጉት አፍራሽ እንቅስቃሴዎች እና ዓለም ዓቀፍ የሃይድሮ ፓወር ተቋማት እንዳይሳተፉ የሚያደርጉት የተሳሳተ ቅስቀሳ እርምት እንንዲያገኝ ጥሩ ማሳያም ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ምክንያቱም የአሜሪካ ኮርፖሬት ኩባንያዎች የአሜሪካ መንግስትን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን እየተከተሉ የሚሰሩ በመሆናቸው የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ከአሜሪካ መንግስት ብሔራዊ ጥቅም ጋር የፈጠረው ልዩነት አለመኖሩን ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤ ከዚህም በላይ የአሜሪካ ኮርፖሬት ኩባንያዎች በሚሳተፉባቸው ሥራዎች ላይ ማንም ምንም አይነት ጥቃት ሊፈጽም እንደማይችል ስለሚታወቅ ተፅዕኖው በቀላሉ የሚታይ አይደለም” ሲሉ ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል።
ጀነራል ኤሌክትሪክ፣ እ.ኤ.አ. አፕሪል 24 ቀን 1889 የተመሰረተ ኮርፖሬት ኩባንያ ነው። በመቶ ሀገሮች ላይ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርቶ ይገኛል። ከሚጠቀሱት ውስጥ መሠረተ ልማት፣ የአውሮፕላን ሞተሮች፣ ሃይል ማመንጫዎች፣ የሃይል አቅርቦት ስርጋታዎች፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ በሕክምና ዘርፍ እና የሚዲያ ተቋማ ስራዎችነም ያከናውናል። ተቋሙ 300ሺ ሠራተኞች በዓለም ዙሪያ ያስተዳድራል። በዚህ ተቋም ውስጥም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ከሰላሳ የሚበልጡ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስቶች ይገኛሉ።
ሌላው እ.ኤ.አ. 2010 ዓለም በኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ በወደቀችበት ጊዜ ጀነራል ኤሌትሪክ አጠቃላይ ትርፉ 150 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነበር። ከዚህ ውስጥ 12.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘት የቻለ ትልቅ ተቋም ሲሆን፤ በዚሁ ዓመት የተቋሙ የስራ ማስኬጃው የገንዘብ መጠን 14.7 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ፎርብስ መጽሄት አስደናቂ ተቋማት በማለት ከ500 ተቋማት መካከል ባወጣው ዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከዓለም በአምስተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ጀነራል ኤሌክትሪክ ኩባያን ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት መካከል ከአጠቃላይ ትርፍ በስድስተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ሲሆን፣ በአትራፊነት ደግሞ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በተቋሙ ስም የተመዘገቡ 40 የቴክኖሎጂ የአዕምሮ ጥበቃ መብት ያላቸው ውጤቶች አሉት።
እንደሚታወቀው የሕዳሴው ግድብን አጠቃላይ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍሉን አጠቃላይ የስራ ሂደት ሙሉ ለሙሉ የተሠጠው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን መሆኑ ይታወቃል። ከስራው ስፋትና የተለየ አቅም የሚጠይቅ ከመሆኑ አንፃር ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መከላከያ ኢንጂነሪንግ ተባብሮ እየሰራ ይገኛል። የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን Alstom ከተባለው የፈረንሳይ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች አምራች ኩባንያ ጋር የ250 ሚሊዮን ፓውንድ የግዢ ስምምነት መፈረሙ ይታወቃል። በዚህ ስምምነት መሠረት Alstom ስምንት 375 MW ማመንጨት የሚችሉ ተርባይኖች እና ስምንት ጀነሬተሮች ያቀርባል። እንዲሁም የኢንጅነሪንግ እና የፓዎር ፕላንት ኮሚሽን የማድረግ ስራዎችንም ያከናውናል። ከዚህ በፊት ይህ ተቋም በኢትዮጵያ ውስጥ ለተዘረጉት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፓዎር ሃውሶች ተርባይኖች ማቅረቡ ይታወሳል።
 በተመሳሳይ መልኩም ጀነራል ኤሌክትሪክም በጨረታ ተወዳድሮ በሚያሸንፍባቸው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍሎች መካከል በተፈለገው ጥራትና ጊዜ ለማቅረብ ዝግጅት መጨረሱን የአዲስ አበባ ወኪሉ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 403 ረቡዕ ግንቦት 21/2005)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:38 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar