www.maledatimes.com የግልገል በለስ ከተማ በመብራት ችግር ውስጥ ናት በጋዜጣው ሪፖርተር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የግልገል በለስ ከተማ በመብራት ችግር ውስጥ ናት በጋዜጣው ሪፖርተር

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on የግልገል በለስ ከተማ በመብራት ችግር ውስጥ ናት በጋዜጣው ሪፖርተር

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 44 Second
ሰንደቅ ጋዜጣ
ከህዳሴ ግድብ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የግልገል በለስ ከተማ በመብራት ችግር ምክንያት ሆቴሎች አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ በመባል የሚታወቀው ከተማ ለህዳሴው ግድብ ሙያተኞች፣ ግድቡንም ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች የሚያርፉበት ከተማ ሲሆን ኤሌክትሪክ ኃይል በተደጋጋሚና በተከታታይ መቋረጥ ጋር በተያያዘ ሆቴሎች አገልግሎት መስጠት መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።
አንድ የሆቴል ባለቤት እንደተናገሩት “በአሁኑ ወቅት መብራት ከጠፋ አራተኛ ቀኑን መያዙን፣ አገሩ በረሃ በመሆኑ ፍሪጅ ከሌላ እንደ ሥጋ ያሉ ምግቦችን ብዙ ሰዓታት መቆየት ስለማይችሉ ለደንበኞቻችን ሽሮ ወጥ ብቻ ለመሸጥ ተገደናል” ብለዋል።
ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ የመጠጥ ውሃ እንዲሁም የስልክ አገልግሎት እንደሚቆራረጥ ጠቁመው እንግዶቻችን እዚህ በረሃ ውስጥ መጥተው ፊታቸውን እንኳ የሚለቃለቁበት ውሃ አያገኙም ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። ሆኖም ኮርፖሬሽኑ የኃይል መቆራረጥ ችግሮችን ከቴክኒክ ችግር ጋር በማያያዝ ተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው።¾
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar