www.maledatimes.com ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ በጋዜጣው ሪፖርተር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ በጋዜጣው ሪፖርተር

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ በጋዜጣው ሪፖርተር

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠርጣሪ ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ ከያዘ በኋላ ለኮሚሽኑ የሚደርሰው የሙስና ጥቆማ ቁጥር መጨመሩ ታወቀ።
ኮሚሽኑ በድረገፁ ይፋ እንዳደረገው በተለይ ከግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በኋላ ባሉት አስር ቀናት ብቻ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ በልጦ መመዝገቡን ገልጿል።
ኀብረተሰቡ ሙስና አስከፊ ድርጊት መሆኑን ተገንዝቦ ለማጋለጥና ሙስናን ለመዋጋት እያሳየ ላለው ጥረት ኮሚሽኑ ምሥጋና አቅርቧል። ሆኖም ምን ያህል ጥቆማ እንደቀረበለት በቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል።
የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2005 በጀት ዓመት አስር ወራት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጨምሮ 3001 ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መቀበሉን ከነዚህ ውስጥ በኮሚሽኑ የሥልጣን ክልል ሥር የሚወድቁት 1ሺ 335 ወይም 44 በመቶ ያህሉ ሲሆን የተቀሩት 56 በመቶ ከሥልጣኑ ክልል ውጪ መሆናቸውን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ከሳምንት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለፃቸው ይታወሳል።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar