www.maledatimes.com ዶ/ር ያዕቆብ ከመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት እርቅ እንዲወርድ እየጣሩ ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዶ/ር ያዕቆብ ከመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት እርቅ እንዲወርድ እየጣሩ ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on ዶ/ር ያዕቆብ ከመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት እርቅ እንዲወርድ እየጣሩ ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 33 Second
የቀድሞ ቅንጅት ከፍተኛ አመራርና የዓለም አቀፍ ምሁር የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጠቅላላ ጉባኤ ከመጥራቱ በፊት ሦስት ቦታ የተከፈሉትን የፓርቲውን አመራር አባላት ለማስታረቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ።
ቀደም ሲል በተመሳሳይ በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በእርቅ ለመፍታት ቢሞከርም የእርቅ ሂደቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቶ ነበር።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት አዲስ አመራር ከመምረጡ በፊት በጉዳዩ ላይ ጥያቄ አለን የሚሉ ወገኖች በጠረጴዛ ዙርያ ተቀራርበው እንዲመክሩ ዶ/ር ያዕቆብ ሙከራ እያደረጉ ናቸው።
ፓርቲው አሁን ያለበትን አጣብቂኝ ሁኔታ ለመፍታት ተቀራርቦ ከመነጋገር ውጪ አማራጭ እንደሌለ የሚጠቅሱት ምንጮች ይሄንኑ የመቀራረቢያ መድረክ ከጠቅላላ ጉባኤው በፊት በማካሄድ እንደገና ጥረቱ መጀመሩን ምንጮች አመልክተዋል።
በዚህም መሠረት ወደ እርቁ መድረክ የሚመጡ ሦስቱ የፓርቲው ቡድኖች እያንዳንዳቸው ሦስት ተወካዮችን በመምረጥ ለእርቅ መድረኩ እንዲያዘጋጁ ተወስኗል።
ስለጉዳዩ የተጠየቁት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ከዚህ ቀደም የእርቅ ሂደቱ መጀመሩን ነገር ግን በቡድኖቹ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መቋረጡን አስታውቀው፤ የአሁኑ የእርቅ ሂደት በተመለከተ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በአሁኑ ወቅት የፓርቲው ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ካሳሁን አበባው በበኩላቸው ቀደም ሲል ከተጀመረው የእርቅ ሂደት ባለፈ ሰሞኑን ስለተጀመረው የእርቅ ሂደት አስተያየት ለመስጠት አልፈለጉም።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:44 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar