www.maledatimes.com አስመጪዎች የሦስተኛ ወገን ሰርተፍኬት ሊጠየቁ ነው በፀጋው መላኩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አስመጪዎች የሦስተኛ ወገን ሰርተፍኬት ሊጠየቁ ነው በፀጋው መላኩ

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on አስመጪዎች የሦስተኛ ወገን ሰርተፍኬት ሊጠየቁ ነው በፀጋው መላኩ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 31 Second
ንግድ ሚኒስቴር አስገዳጅ ደረጃ ያወጣላቸውን ከውጪ የሚገቡ ምርቶች በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር ያመቸው ዘንድ ከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ አስመጪዎችን የሦስተኛ ወገን ሰርተፍኬት የሚጠይቅ መሆኑን አስታወቀ።
በንግድ ሚኒስቴር የገቢና ወጪ እቃዎች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ገኖ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር አንድ አስመጪ የምርቱን የጥራት ደረጃ የሚያስመረምረው ሀገር ውስጥ ገብቶ በጉምሩክ ላብራቶሪዎች አማካኝነት መሆኑን አስታውሰው፤ ቀድሞ የነበረውን አሰራር በመቀየር ከቀጣዩ ሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ ግን አስመጪዎች ሸቀጦቻቸውን ከሚያስመጡባቸው ሀገራት የምርቶቻቸውን ደረጃና ጥራት የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከታወቀ ድርጅት ካመጡ እቃዎቻቸው በቀላሉ በጉምሩክ የሚያልፉ መሆኑን ገልፀዋል። ‘‘አስመጪዎች የሦስተኛ ወገን ሰርተፍኬት ካመጡ በሀገር ውስጥ ጉምሩክ የፍተሻ ሂደት የሚወስድባቸውን ጊዜ ስለሚያሳጥሩ መጋዘን ኪራይና ለኢንሹራንስ ከሚያወጡት ወጪ ይድናሉ’’ ያሉት ዳይሬክተሩ ሆኖም የሚቀርበው የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አለም አቀፍ እውቅና ካለው ላብራቶሪ የተሰጠ መሆን የሚገባው መሆኑን አስታውቀዋል። አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ላብራቶሪዎች ዝርዝር (List) በየጊዜው በኢንተርኔት የሚለቀቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ታምሩ፤ አስመጪዎች የሚያቀርቧቸው ሰርተፍኬቶችም ከእነዚሁ አካላት በትክክል የተሰጠ መሆኑ ፍተሻ የሚደረግበት መሆኑን አመልክተዋል።
እስከዛሬ በነበረው የጥራት ፍተሻ አሰራር አንድ በአስገዳጅ ደረጃዎች ሥር ያለ ምርት ሀገር ውስጥ ደርሶ የጉምሩክ የፍተሻ ላብራቶሪን ካላለፈ ወደመጣበት እንዲመለስ ይደረግ የነበረ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን፤ ከቀጣይ ሐምሌ ወር ጀምሮ የሚተገበረው አዲስ አሰራር ግን የምርቱን የጥራት ደረጃ ገና ከመነሻው ስለሚወስን ነጋዴውን ከክስረት ያድናል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ካለው የናሙና መፈተሻ ላብራቶሪ እጥረት ጋር በተያያዘ ሸቀጦች ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ፍተሻ እስከሚካሄድባቸው ድረሰ በመጋዘን ስለሚቆዩና የኢንሹራንስ ክፍያም ስለሚጠይቅባቸው አስመጪዎች ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጉ የነበረ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን በአዲሱ አሰራር መሠረት ግን እቃዎቹን በሰነድ ልውውጥ ብቻ ከጥራት ጋር በተያያዘ የጉምሩክን ኬላ እንዲያልፉ ስለሚደረግ ሸቀጦቹ በመጨረሻ ተጠቃሚው ላይ የሚኖራቸውም የዋጋ ጫና በተወሰነ ደረጃ የሚቀንስበት ሁኔታ ይኖራል ተብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በሀገሪቱ ያሉ አስመጪ ነጋዴዎች ከሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አዲሱ አሰራር እንዲጠቀሙ በአሁኑ ሰዓት በደብዳቤ በማሳወቅ ላይ ይገኛል።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar