www.maledatimes.com የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባሉን ለማስፈታት “አካልን ነፃ የማውጣት ክስ” ሊመሰርት ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባሉን ለማስፈታት “አካልን ነፃ የማውጣት ክስ” ሊመሰርት ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

By   /   May 28, 2013  /   Comments Off on የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባሉን ለማስፈታት “አካልን ነፃ የማውጣት ክስ” ሊመሰርት ነው በዘሪሁን ሙሉጌታ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 17 Second
ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም በፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ በፖሊስ አማካኝነት በቁጥጥር ስር የዋለው የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመራር አባልና የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድን ከእስር ለማስፈታት “አካልን ነፃ የማውጣት ክስ” እንደሚመሰርቱ ጠበቃው አስታወቁ።
የወጣቱ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ደንበኛቸውን “የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎች እኛ አልያዝነውም” የሚል ምላሽ በመስጠታቸው፣ ደንበኛቸው ማን እንደያዘው ለጊዜው ባለማወቃቸውና በተጠርጣሪውም ላይ ምርመራ እየተካሄደበት ባለመሆኑ፤ ፍርድቤትም መቅረቡን ማረጋገጥ ባለመቻላቸው፤ በሕገ-ወጥ መንገድ በመያዙ ጭምር በፍትሐብሔር ሥነስርዓት ሕግ ቁጥር 177 መሰረት ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት አቤቱታቸውን እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል።
“ማህበሩ በበኩሉ ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም በአምባገነኖች የሐሰት ውንጀላ እስር እና እንግልት አንበረከክም” በሚል ባወጣው መግለጫ የወጣቱን መያዝ አውግዟል። ማህበሩ በመግለጫው በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገው ወጣት ብርሃኑ በሕግ አማካሪ እንዳይጎበኝ መከልከሉና በቀጣይም የማህበሩ አመራሮች ላይ ሊወሰድ የታሰበው እርምጃ የስርዓቱን አፋኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲል እስሩን አውግዟል። ከማህበሩ አባላት በተጨማሪ ዜጎችን በእስርና በድብደባ ማንበርከክ እንደማይቻል ለማረጋገጥ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማስተባበር ወደ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ እንገባለን ሲል በመግለጫው የጠቆመ ሲሆን በቅርቡም ዝርዝር የተቃውሞ ፕሮግራም ይፋ እናደርጋለን ሲል ጨምሮ ገልጿል።
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር በአብዛኛው ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበራት ፌዴሬሽን በተውጣጡ አባላት ለወጣቱ ሁለንተናዊ መብት መከበርና በሀገር አንድነት ዙሪያ የተቋቋመ ሲሆን በማህበራትና በጎአድራጎት ኤጀንሲ በቅርቡ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ የሲቪክ ማህበር መሆኑ ይታወቃል።¾
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on May 28, 2013
  • By:
  • Last Modified: May 28, 2013 @ 9:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar