www.maledatimes.com አገራችን እንደ ዳቦ አትቆራረስም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አገራችን እንደ ዳቦ አትቆራረስም

By   /   June 2, 2013  /   Comments Off on አገራችን እንደ ዳቦ አትቆራረስም

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 34 Second

ዛሬ ‹ሰማያዊ› ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
* በሰልፉ ላይ የተገኙት ሰዎች ብዛት ከ6000-7000 ይሆናል፡፡ (ሆነ ብሎ ቁጥር በማሳነስ አትጠርጠሩኝ፤ በ2 ዘዴና ከፍተኛውን ግምት ወስጄ የሠራሁት ስሌት ነው እንጂ ትክክለኛው ቁጥር ከዚያ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡)

* ‹‹ሰልፉን የኛ ሰልፍ እናድርገው›› የሚል ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት የአወልያ ንቅናቄ ደጋፊዎች በመፈክር ወቅት የተለየ ድምጽ በማሰማትና በመሳሰሉት ብዛታቸው እንዲስተዋል አድርገዋል (በግርድፍ ግምት ከሰልፈኞቹ 40% ገደማ ያህል ነበሩ፡፡)

* ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም በተጋባዥ እንግዳነት ንግግር ሊያደርግ ሲወጣ ‹‹ጀግና›› ‹‹ጀግና›› የሚል ድምጽ ከአንድ ጥግ ተሰምቷል፡፡ እነማን እነደሆኑ የማውቅበት መንገድ ባይኖርም፣ አንድ ሰልፍ ላይ ‹‹ልደቱ ማንዴላ›› የተባለውን አስታወሰኝ፡፡

– ዶ/ር ያዕቆብ ከተናገራቸው መሀል፡- (ቃል በቃል አይደለም) ‹‹የ1997ቱ ድል በ2007 እንድገም››፣ ‹‹የበደኖውን ግድያ ኢሕአዴግ ነው የፈፀመው››፣ ‹‹ኢሕአዴግ 22 ዓመት የቆየው በኛ ድክመት ነው›› (ከ1983 ጀምሮ ተቃዋሚ ነበር እንዴ? ለሹመት ታጭቶ ነበር መሰለኝ) የሚሉ ይገኙበታል፡፡

ሌላ…ሌላ….በቃ ‹ኢቲቪ›ን እና ‹ዛሚ ኤፍ ኤም›ን የሚሰድቡ ነበሩ፡፡ (የረሳሁት ካለ እመለስበታለሁ)

በነገራችን ላይ የሰልፈኞቹ ብዛት ያነሰው አንዳንድ ቀበሌ አስተዳደሮች ስለቤት ጉዳይ ስብሰባ ስለጠሩ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡
ጓዶቸ፣ አዲስ አበባ ውስጥ እኮ ለዓቅመ-ሰልፍ የደረሰ ቢያንስ 1ሚሊየን ሰው አለ፡፡ በዛ ላይ ይሄ የቤት ጉዳይ የሚመለከተው እኮ ቢያንስ በወር 187 ብር መቆጠብ የሚችለውን ነው፡፡ ለማንኛውም ኢሕአዴግ የተቃዋሚው ፓርቲ ዝግጅት እንዳይደምቅ ቢፈልግ አይደንቀኝም፡፡ ግን ስሞታችን በአመክንዮ(logic) የተመሠረተ ይሁን፡፡መማር ያስከብራል የሚለውን መፈክር ሲያሰሙ የሚታየው ቪድዮ እና ጸሃፊው የዘገበውን ዘገባ ያነጻጽሩ ለዚህም ከስር የሚታየውን ሊንክ ይጫኑ
http://www.ethiotube.net/video/26328/Peaceful-demonstrators-chant-Memar-yaskebiral-hagerin-yakoral–June-2-2013
ለማንኛውም ሰልፉ በሰላም አልቋል፡፡ አንድ መቶም ሆነ ሆነ አንድ ሺህ ሰው ቢገኝ ፋይዳውን አይቀንሰውም፡፡

በቀጣይ የምንሰማው ዜና ግን ሰልፉ በሌሎች ተቃዋሚዎች (በተለያ በአንድነት ፓርቲ) ላይ ስለፈጠረው ተፅዕኖ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ዝም ብለው ከርመው በሰልፉ ዋዜማ ‹‹እኛም ለሰልፉ እየቀሰቀስን ነው›› ማለታቸው ብልጠት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ለወትሮም በቋፍ ያለው አንድነት ፓርቲ አንድም ይከፋፈላል አልያም ከመድረክ ይወጣል፡፡ ከመድረክ ስል፡- ከ‹መድረክ› ፓርቲ እንዲሁም ከፖለቲካው መድረክ፡፡ መቼም ወጣትና ትጉህ አባላቱን ለሰማያዊ ፓርቲ አስረክቦ (ከአሁኑ እንኳን እነ BefeQadu Z Hailu ዝውውር ጀምረዋል ይባላል)፣ እንደመኢአድ ዓይነት ፓርቲ መሆን ከመኖር አይቆጠርም፡፡

ምናልባትም አንድነት ፓርቲ ከሰማያዊና ከመኢአድ ጋር ጥምረት በመፍጠር አመክንዮአዊ አሰላለፍ ይከተል ይሆናል፡፡ እነዶ/ር መረራና ፕ/ር በየነ እንኳን በዚህ አይሞቃቸው አይበርዳቸው፡፡ በ1996 ቅንጅትን እንዳሉት ‹‹የቀኝ ሀይሎች›› ስብስብ ነው ብለው ያልፉታል፡፡

እንዲህ ፖለቲካው ሞቅ ሲል እንዴት ደስ ይላል?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on June 2, 2013
  • By:
  • Last Modified: June 2, 2013 @ 8:33 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar