www.maledatimes.com ርእሰ አድባራቶች ጉዞአቸው ከድጡ ወደ ማጡ ቀጥሎአል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ርእሰ አድባራቶች ጉዞአቸው ከድጡ ወደ ማጡ ቀጥሎአል

By   /   June 3, 2013  /   Comments Off on ርእሰ አድባራቶች ጉዞአቸው ከድጡ ወደ ማጡ ቀጥሎአል

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 31 Second

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከድጡ ወደ ማጡ
በዚህ በትልቁ የአውሮፓ ክፍል የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት
ማርያም ለረጅም ዘመናት አገልግሎት የሰጠች እንደመሆንዋ መጠን
በሙያ የበሰሉ በአገልግሎታቸው የተመሰገኑ አባቶች አገልግሎት የሰጡበት
መሆኑ ታሪክ የሚያስታውሳቸው ነው ከነዚህም አባቶች መካከል በቀድሞው
ስማቸው አባ አረጋዊ በኋላ ብጹእ አቡነ ዮሐንስ እንዲሁም ሊቀ ካህናት ሰሎሞን
ገብረ ስላሴና ሌሎችም ይገኙበታል ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ለተዋህዶ እምነት
ተከታዮች ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክተች ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኣውሮፓ ቀደምት ተብለው ከሚጠሩት
አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በቁጥር አንድ የምትቀመጥ ከመሆንዋም በላይ
ከሀገራችው ተሰደው ከወገን ከዘመድ ተለይተው ለሚገኙ ምእመናን ከፍተኛ
መጽናናት ትንሿ እናት ሀገር ኢትዮጵያ መሆንዋ የማይካድ ነው
ስለሆነም በካህናቱ መልካም አገልግሎት በምእመናኑ ያልተቆጠበ ጥረት ህንጻ
ቤተ ክርስቲያን በመግዛት አርያነቱ ለሌሎች የሚተርፍ ቅርስና ታሪኩ ለትውልድ
የሚተላለፍ አስደናቂ ተግባር ፈጽመው በባእድ ሀገር የህንጻ ቤተ ክርስቲያን
ባለቤት ለመሆን በቅተዋል
ስለሆነም በዚህ ተግባራቸው ዘወትር የሚመሰገኑ ናቸው
ይሁን እንጂ ይህን አንጸባራቂ ታሪክ የያዙት ካህናትና ምእመናን እስከ ቅርብ
ጊዜ ድረስ ሰፊና ብዛት ያላቸው ማህበረ ምእመናን ቁጥራቸው የማይናቅ ማሀበረ
ካህናትን በማቀፍ መልካም አገልግሎት እየሰጠች ባለበችበት ወቅት የቤተ
ክርስቲያን ደንብ ለማውጣት በሚል በተነሳው ውዝግብ ሂደቱ ተካሮ መለያየቱ
ጡዞ ካህናትን ጨምሮ ቁጥራቸው የማይናቅ ምእመናን በአንድ በኩል ለረጅም
ዘመናት በሰበካ ጉባዔ አባልነት እንዲሁም በተለያዩ የቤተ ክርስቲኒቱ
የአገልግሎት ክፍሎች ያበረከቱና በገንዘባቸው በጉልበታችው እንዲሁም
በእውቀታቸው ያገለገሉ በርካታ ምዕመናን በአንድ በኩል ሆነው ልዩነቱ ሰፍቶ
ከሁለቱም ወገን የማይጠበቅ ተግባር ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኑ ተዘግቶ
አገልግሎት ከመቋረጡ ባሻገር ያን የመሰለ የተሟላ አገልግሎት የሚፈጸምበት
ቤተክርስቲያን ያውም በሱባኤ ወቅት ተዘግቶ ለፋሲካው በአል እንኳን ችግሩ
ተፍቶ በፍቅርና በሰላም በኣንድነት ማክበር አለመቻላቸው ሁለቱም ወገን ለቤተ
ክርስቲያን አንድነት ለፍቅርና ለሰላም ገና ያልተዘጋጁ መሆኑን ለማወቅ መረዳት
ይቻላል የምእመናኑ ወገን የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳዳሪ አባ ግርማን ለወያኔ
ሊሸጡን እያለ ከዚህም አልፎ በአዲስ አበባ የሚገው ሲኖዶስ በጅማ አካባቢ
ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል ምእመናን ሲታረዱ የቤተ ክርስቲያን ክብርና ሞገስ
ለሀገር ቅርስና መመኪያ የሆኑት ገዳማት ሲቃጠሉ ቅዱሱ ገዳም ዋልድባ ሲታረስ
መናኝ መነኮሳት እየተደበደቡ ከበአታቸው ሲባረሩ ግድ የማይለው ሲኖዶስ
እያሉ ሲተቹ በሌላው በኩል ደግሞ መንፈሳዊ አመራር እንቀበላለን በማለት
መግለጫ አውጥተዋል ታዲያ ኣባግርማን ኤምባሲ ሄደው ተደራደሩ ከወያኔ ጋር
ተፈራረሙ የሚለው የምእመናን ወገን ከመነኩሴው ጋር ልዩነታችው ከምን ላይ
ነው ግማሽ አጎፍሮ ግማሽ ተላጭቶ አይሆንምን አባ ግርማን በወያኔነት ፈርጆ
በስላ ሂስና ስድብ የሚወርፈው የምእመናን ወገን ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ
መመሪያ የሚቀበልና ተጠሪነቱ ለእሱ ከሆነ ክሱና ዘለፋው መሰረተ ቢስ ከመሆኑ
በቀር ፋይዳ የሌለው ዋጋቢስ ከመሆኑ በቀር የግለሰብ ጥላቻ ብቻ ከመሆን
አያልፍም የአዲስ አበባው ሲኖዶስ አባላት አባ ገብርአልና ቀውስጦስ ለማስታረቅ
ሲመጡም አንቀበልም እያለ የሚደነፋው የምዕመናን ወገን ለመሆኑ አባ
ገብርአልና አባ ቀውስጦስ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ አባላት አይደሉምን በማን
ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ ነው ነገሩ
የለንደን ምእመናን ሆይ እውነትን ተከተሉ አቋማችሁን ደግሞ መምሩ ቤተ
ክርስቲያን እንወዳለን በሕጓ እንመራለን የምትሉ ከሆነ ተወደደም ተጠላም
በፓትርያክ በሚመራ በቅዱስ ሲኖዶስ መመራት ቀኖናዊ ግድ የሚል አግባብ ነው
እንደ ምድራዊ የፖለቲካ ድርጅት ገለልተኛ ነን ማለቱ ኦርቶዶክሳዊ ሳይሆን
ፕሮተስታዊነት ነው ጥቂት ስልጣን ፈላጊ ምእመናንና ጥቅመኞች ካህናት
በጀመሩት ሰው ሰራሽ ስርዓት መከተሉ ለእናንተም አይጠቅምም
ቤተ ከርስቲያንንም አይገነባም በአንድ በኩል በሀገራችን የተሰራፋውን የዘረኛና
የጎጠኛ መንግስት እየተቃወማችሁ ግከወሬ በስተቀር ተግባራዊነቱ አጠያያቂ ነው
አለመታደል ሆኖ በአገራችንም ሆነ በቤተ ክርስቲያናችን የተሳራፋውን መጠነ
ሰፊ ችግር መጨረሻ እንዳይኖረው ትልቁ ምክንያት የሆነው በአንድነት
አለመቆማችን ነው በሰለጠነው ዓለም እየኖርን አንድነት ምን ያህል
እንደሚጠቅም እያወቅን በጥቃቅን ምክንያት ልዩንት እየፈጠርን የችግሩ ዘመን
ተራዝሞ እነሆ ፳፪ ዓመት ሞላን
የተዋህዶ እምነት ተከታዮች የምንል ከሆነ በቀኖናዋ እንመራ ሕጓንም እንከተል
በዓለም ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በማይገኝ ስርዓት ገለልተኛ እያልን
እስከመቼ ሕገ ቤተክርስቲያንን እንጻረራለን ለትውልድ የማይተላለፍ አፍራሽ
ሥርዓት ገለልተኛ ነን ሲኖዶስን ብቻ ያውም ያዲስ አበባውን እንቀበላለን ማለት
ፕሮቴስንታዊ ልምምድ መቅረት ይገባዋል ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የመሰረታትን
ቅዱሳን ሐዋርያት በስብከታቸው ያጸኗትን ሰማዕታት በደማቸው ጻድቃን
በተጋድሎ እና በጸሎታቸው ያቆዩዋትን ቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ዶግማ
በማይደግፈው ገለልተኛ ስርዓት መገታት አለበት
ሰዎች ሊለያዩ ይችላሉ ቤተ ክርስቲያን ግን መለያየት አይገባም ዛሬ ቤተ
ክርስቲያናችን እንደ ሀገራችን በዓለም ፊት ተዋርዳ ማንነትዋ እየተሸረሸረ
ሊቃውንትዋ ሳይሆኑ ሕዝባውያኑ የሚመሩዋት በከተፍኛ ደረጃ የምግባር
ብልሹነት የሚታይበት ዘረኛና ሙስና ብልሹ አስተዳደር የሰፈነባት
እግዚአብሔር የማይፈራበት ሰው የማይታፈርበት የጉቦና የዝርፊያ ቤት ሆናለች
ታዲያ ይህን አስከፊ ችግር ታግሎ ለመጣል መለያየትን ወደ ጎን ትተን
በአንድነት መቆም ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
ዘመነ ካሳ
ከጀርመን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on June 3, 2013
  • By:
  • Last Modified: June 3, 2013 @ 2:41 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar