www.maledatimes.com ፍትህ ጋዜጣን የሚያትም ማተሚያ ቤት መጥፋቱን ምንጮቼ ነገሩኝ ( አቤ ቶኪቻው) www.abetokichaw.com - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፍትህ ጋዜጣን የሚያትም ማተሚያ ቤት መጥፋቱን ምንጮቼ ነገሩኝ ( አቤ ቶኪቻው) www.abetokichaw.com

By   /   July 27, 2012  /   Comments Off on ፍትህ ጋዜጣን የሚያትም ማተሚያ ቤት መጥፋቱን ምንጮቼ ነገሩኝ ( አቤ ቶኪቻው) www.abetokichaw.com

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 25 Second

ፍትህ ጋዜጣ በትላንትናው እለት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፤ “ፍትህ ሚኒስቴር እንዳታትም ብሎኛል” በሚል ክልከላ እንዳደረገባት አውርተን ነበር። የጋዜጣው አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ቢያመሩም ፍትህ ሚኒስቴር ደግሞ “እኔ አልከለከልኩም ማሳተም ትችላላችሁ!” ብሏቸው ነበር። ነገር ግን ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሲሄድ ከስራ በመወጥጣታቸው የተነሳ ትላንት ሳትታተም ቀርታለች።

በዛሬው እለት ሌላ ሙከራ ያደረጉት የፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በአቋሙ ቢፀናባቸው በድጋሚ ፍትህ ሚኒስቴር ሄደው አቤት ቢሉም “ማተሚያ ቤቱ ራሱን የቻለ ተቋም ነው እንጂ በኛ የሚታዘዝ አይደለም” በሚል አሰናብተዋቸዋል። አሁንም ፍትሆች በታጋሽነት ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሄደው ደጅ ቢጠኑም የማተሚያ ቤቱ ሃላፊዎች “ቢላ በአንገቴ” ብለዋቸዋል። (ቢላ በዚህ ጊዜ ከየት ይመጣል…!?)

የጋዜጣው ባልደረቦች አሁንም ተስፋ አልቆረጡም ወደ ቦሌ ማተሚያ ቤት ሄደው “እስቲ እናንተ አትሙልን!?” ብለው ጠየቁ። ነገር ግን ቦሌዎች “የደንበኞቻችንን ብቻ ነው የምናትመው” ብለው እምቢኝ አሉ። ፍትሆችም በሆዳቸው “እኛስ ደበኛችሁ ነን እንዴ?” ብለው በአንደበታቸው ግን፤ “አረ እባካችሁ ወደፊት ደንበኛ እንሆናለን!?” ብለው ቢያግባቡም እሺ ብሎ የሚያትምላቸው አላገኙም።

በነገራችን ላይ ፍትህ የሚያሳትመውን ከሰላሳ ሺህ በላይ ኮፒ ጋዜጣ ማተም ብቃት ያለው ሌላ ማተሚያ ቤት በኢትዮጵያ የለም።

ስለዚህ አሁንም ፍትህ በኢትዮጵያ ምድር የለችም! የሰዎቻችን ፀብ ከስሟ ከሆነ ምናልባት ስሟን ቀይሮ መሞከር ይሻል ይሆን!? እንጃ….!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 27, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 27, 2012 @ 7:49 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar