www.maledatimes.com ህልም አለኝ (ለምለም አንዳርጌ(ከኦስሎ) ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ህልም አለኝ (ለምለም አንዳርጌ(ከኦስሎ) )

By   /   July 8, 2013  /   Comments Off on ህልም አለኝ (ለምለም አንዳርጌ(ከኦስሎ) )

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 2 Second

እህህ አለች እማማ እህህ አለች ሃገሬ፣
ተብትቦ በያዛት በነከሳት አውሬ፡፡
ሴት እናት እህት ናት ሴት የሃገር እመቤት፣
የዘር ትብታብ ልቃቂት፣
የፍጡራን ሚስጥር እምብርት፣
ካስማ ማገር የአንድነት፡፡
ግና ዛሬ ውልሽ ጠፍቶ፣
ክብርሽ ዝናሽ ተቀምቶ፡፡
አሳር ግፍ ሲወርድብሽ፣
ቤት ማጀቱ ሲጎልብሽ፡፡
ተጥለሻል በየሃገሩ፣
ገረድ ልትሆኝ ለቱጃሩ፡፡
ሃገርንሽ እምነትሽን በዘረኞች ተቀምተሽ፣
ከንቱ ሆነሽ ያለ ቅሪት በሰው ሃገር ትኖሪያለሽ፡፡
ስደት ሆኖ ያንቺ እጣ፣
ሆነሽ ቀረሽ ከብሩን ያጣ፡፡
ግና ህልም አለኝ የእውነት፣
ሴት እናት ልትሆን ቃሏ የሚሰምርበት፡፡
ሲነሳ ምንሽር ሲወለወል አልቤን፣
ህዝባችን ሆ ሲል ሲቃረብ የድል ቀን፡፡
እናትም እህትም ሃገርም ነኝና፣
በቅርብ ይታየኛል የነጻነት ፋና፡፡
ህዝባችን ሃያል ነው ለድል መሰረት፣
ከፋፋይ ጉጅሌን የሚያስደፋ አንገት፡፡ህልም አለኝ ሃገሬ ቅርብ ነው ይነጋል፣
በህዝባችን ሃይል ጠላትሽ ይወድቃል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለወያኔ!!!
ለአስተያየቶ- Wueltaw@yahoo.no

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 8, 2013
  • By:
  • Last Modified: July 8, 2013 @ 11:50 pm
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar